በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሎሚ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው ዓሊ መስጂድ ውስጥ ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የተለያዩ ችግሮች ሲከሰቱና በሰላማዊ የኢባዳ(የአምልኮ) ስርዓቱ ላይ ችግር ሲፈጠር መቆየቱ የሚታወስ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የፌደራል መጅሊስ በአዋጅ ቁጥር 1207/2012 ሲቋቋም በተሰጠው ስልጣን መሠረት የከተማውን መስጂዶች የማስተዳደር ስልጣንና ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ የዓሊ መስጂድም በዚሁ ኃላፊነት መሰረት ያስተዳድራል።
በመሆኑም በዚህ መስጂድ ችግሮች ከመፈጠራቸውና ከተፈጠሩም በኋላ ሠላማዊ የኢባዳ ስርዓቱ እንዲቀጥል በተቋማዊ ኃላፊነቱና በአገልጋይነት መንፈስ ጉዳዮቹን ሲያስተካክል፣ ሲያርምና በሚደርስበትም ተገቢ ያልሆነ ወቀሳ ሁሉ በታጋሽነት ሲያልፍ ቆይቷል። በስካሁኑ የመስጂዱ ሂደቶች የችግሮቹ ዋነኛ መነሻ የጥቅምና የቡድንተኝነት አመለካከት እንዲሁም የኮሚቴ አወቃቀር ችግሮች መሆናቸውንም ለመገንዘብ ተችሏል።
በመሆኑም ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የኮሚቴ አወቃቀር ሂደት ተፈቶ ችግሮቹ እልባት ያገኙ ዘንድ ከፍተኛ ምክር ቤቱ መፍትሔ ያለውን የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል። ውሳኔው ተፈፃሚነት ይኖረው ዘንድም ለአስፈጻሚ አካላት ያሳወቀ ሲሆን ከኮሚቴ አወቃቀር ጋር በተያያዘ
ኡስታዝ አብራር ሷቢር ሰብሳቢ
አቶ ደመቀ ኢማም ም/ሰብሳቢ
አቶ ሀምዱ መሐመድ ፀሐፊ
አቶ ሪድዋን ሙዴ ገንዘብ ያዥ
አቶ ቶፊቅ ምኑታ ሒሳብ ሹም
አቶ ደምስ መሐመድ ንብረት ክፍል
አቶ ነስሩ ሁሴን አባል
አቶ ጀማል ሙዘይንና ሐጂ ሱልጣን ዓሊ ተጠባባቂ የኮሚቴ አባላት በመሆን እንዲያገለግሉ በከተማው መጅሊስ በኩል እውቅናና አደራ ተሰጥቷቸዋል።
እነዚህ የኮሚቴ አባላት የመስጂዱን ሠላምና ደህንነት እንዲያስጠብቁና ተጠሪነታቸው በጊዜያዊነት ለክፍለ ከተማው መጅሊስ እንዲሆንም ውሳኔ ተላልፏል።
በተላለፈው ውሳኔ መሠረትም ኮሚቴው፦
1ኛ. የሚሰበስበውን የሱቅ ኪራይ ወደ አዲስ አበባ መጅሊስ ገቢ ያደርጋል
2ኛ. የመስጂዱ መሠረታዊ ወጪዎች በከፍተኛ ምክር ቤቱ ይሸፈናል
3ኛ.ኮሚቴው በፀጥታ ጉዳይ ከወረዳና ክፍለ ከተማ መጅሊሶች ጋር በትብብር ይሰራል
4ኛ. አዲስ የሚጀመሩ የዳዕዋ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ከወረዳ መጅሊስ ጋር በመመካከር የሚወስን ይሆናል።
5ኛ. ኮሚቴው በጊዜያዊነት ተጠሪነቱ ለክፍለ ከተማው መጅሊስ ይሆናል።
6ኛ. የሴቶች መስጂድ በጊዜያዊነት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆምና ሴቶች በቤታቸው እንዲሰግዱ የተላለፈውን ውሳኔ ያስፈጽማል።
በመሆኑም ይህ የከፍተኛ ምክር ቤቱ ውሳኔ ሲተገበር የሚመለከተው አካል ሁሉ ለኮሚቴው ተገቢውን እገዛ እንዲያደርግ ምክር ቤቱ ያሳስባል።
©: የአዲስ አበባ መጅሊስ