የጋቲራ ሙስሊሞች ሰቆቃ አይበቃም ወይ⁉️
=============================
(መስለም ወንጀል የሆነባት ጋቲራ ከተማ– ጅማ ዞን!)
||
✍ ነገሩ እንዲህ ነው…
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ ጋቲራ በተሰኘች ከተማ ነዋሪ የሆነች ከታች በፎቶው ላይ የምትመለከቷት እህታችን ከነ ቤተሰቧ ወደ ተፈጥሯዊ እምነቷ ተመልሳ ኢስላምን ተቀበለች።
ከዚያ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ነን ያሉ ግለሰቦች መኖሪያ ቤቷ ድረስ ሂደው ደበደቧት። ሊገድሏት ሲሉ ከአላህ ቀጥሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ደረሰላት። ቶሎ ወደ ሆስፒታል በመሄድ በአላህ ፈቃድ ነፍሷ ተረፈች። ከዚያ በኋላ ጉዳዩ በርሷ ብቻ ሳይበቃ ሌሎችም እስልምናን የተቀበሉ 4 ሰዎቹ ነበሩና የነሱንም ቤት ሰብረው ገብተው ጽንፈኞቹ ድብደባ ለመፈፀም ሞከሩ።
ይህ ሁሉ ሲሆን የሚመለከታቸው የአካባቢው የመንግስት አካላት ተገቢውን እርምጃ በጽንፈኞቹ ላይ በመውሰድ ከውንብድናቸው ሊያስቆሟቸው አልሞከሩም። በዚህ የተደጋገመ እፍረት የለሽ ድርጊት የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ ተቆጣ። ግልብጥ ብሎ ወጣና ራሱን መከላከል ጀመረ።
በዚህ ወቅት ሙስሊሙ በየመኖሪያ ቤቱ ተሳዶ ሲደበደብና የግድያ ሙከራ ሲፈፀምበት ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥና ስልታዊ ድጋፍ ውስጥ የነበሩ የአካባቢው የህግ አካላት መንቃት ጀመሩ። በርካታ ሙስሊሞችንም በዚህ ሰበብ አሰሩ። ከጽንፈኞቹ ድብደባ ህይዎቷ የተረፈችውን እህታችንንና ወላጅ እናቷን ጨምሮ በድምሩ ወደ 45 ገደማ ሙስሊሞች እስካሁን ያለ ወንጀላቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።
ይህ የሙስሊሙ መብት፣ ህይዎት፣ ሃብትና ንብረት፣ እምነትና ክብር ሲነካ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሆነው ቢጠሩ እንኳ የማይሰሙና ለመስማት ፈቃደኛ የሆኑ የጸጥታና የህግ አካላት፤ ሁልጊዜ ሙስሊሙ ትዕግስቱ አልቆና በነርሱ ተስፋ ቆርጦ መብቱን በራሱ ሲያስከብር ከድንዝዝነታቸው እየተነሱ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ሌላ ዙር ጥቃትና ሴራ የሚፈፅሙ አካላት ሃግ ሊባሉ ይገባል። የሚመለከታችሁ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ይህ በየቦታው ሙስሊሙ ላይ የሚፈፀም አሳፋሪ ደባ እንዲያከትም ብታደርጉና ያለ ወንጀላቸው ሌሎች በለኮሱት እሳት የታሰሩ የጋተራ ሙስሊሞችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ልታደርጉ ይገባል።
||
t.me/MuradTadesse