🔥#አፈትላኪ_መረጃ‼️
እስከ ጥምቀት በዓል ድረስ በወልድያ ከተማ ዳርቻ አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች በጅምላ እየታፈሱ እንዲታሰሩ መመሪያ መተላለፉ ተሰማ!
በከተማዋ አይሴማ፣ አውራ ጎዳና፣ ጀነቶ በር፣ ዛመል፣ እንኮይ ሰፈር፣ ጉቦ ሰፈር፡ ጎማጣ ልዩ ቦታው ድሃ ወዲህ አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸው እስከ በዓሉ ድረስ ባለው ተከታታይ የሆነ ጥብቅ ፍተሻ እንዲካሄድበትና በአከባቢው የሚገኙ ወጣቶችም በጅምላ ታፍሰው እንዲታሰሩ ትዕዛዙ መተላለፉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ለዚህም ደግሞ በሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል ለሚመራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ወታደራዊ ቤዝ በሆኑት በሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ስታዲየምና በከተማዋ ጎንደር በር በሚገኘው የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ውስጥ ለማጎሪያ የሚሆን ቦታ መዘጋጀቱ ነው የታወቀው።
በከተማዋ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል አስመልክቶ ትናንት ጥር 06/2017 ዓ/ም ጧት ጀምሮ እስከ ምሽት የዘለቀ የከተማዋ ኮማንድ ፖስት ዝግ ስብሰባ አካሂዷል።
ዝግ ስብሰባው የተመራው በከተማዋ ኮማንድ ፖስት ኃላፊው ኮሎኔል ደሳለኝና በከተማ አስተዳደሩ ፀጥታ ኃላፊ ኮማንደር ደርበው መሆኑን ለጣቢያችን የገለፁት የመረብ ምንጮች፡ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች የዞኑ ፀጥታ ኃላፊዎች መታደማቸውን ጠቁመዋል።
ከከተማዋ ዳርቻማ አከባቢዎች በተጨማሪ በመሃል ከተማ የሚገኙ የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች ተከታታይ የሆነ ጥብቅ ፍተሻ እንዲካሄድባቸው ትዕዛዝ ወርዷል ነው የተባለው።
ከዚህ ቀደም በከተማዋ የጥምቀት በዓል ሲከበር ባህላዊ ጭፈራዎችን በመጨፈርና በማስጨፈር የሚታወቁ ሰዎች ተመርጠው አስቀድሞ አፈና እንዲካሄድባቸው ውሳኔ መተላለፉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በከተማዋ ከዚህ ቀደም በሚከበሩ የአደባባይ በዓላቶች ላይ በሚካሄዱ ባህላዊ ጭፈራዎች ወጣቶች የተለያዩ ግጥሞችን በማውጣት ስሜታቸውን ሲገልፁ ይስተዋላል።
በዘንድሮው ዓመት ጥር 11 እና ጥር 12/2017 ዓ/ም በሚከበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በሚካሄደው ባህላዊ ጭፈራ አሳምነው ፅጌን እና ፋኖን የሚያሞግሱ መልዕክቶች እንዳይተላለፉ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ መመሪያ የሰጠው ኮማንድ ፖስቱ፡ ከዚህ ቀደም ባህላዊ ጭፈራውን በመምራት የሚታወቁ ግለሰቦች ከበዓሉ ቀን አስቀድሞ ማደኛ እንዲወጣባቸው ነው መመሪያ ያስተላለፈው ሲሉ መረጃውን ለመረብ ሚዲያ ያደረሱን የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል።
ይሄንን አፈና እና ፍተሻ ለማሳለጥ ከፌደራል ፖሊስ 133 ከአድማ ብተና 235 ከሕዝባዊ ፖሊስ 129 እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ሚሊሻ አባላት እና መከላከያ ሰራዊት ጋር በድምሩ 600 ፀጥታ ኃይል ዝግጁ እንዲሆን ተደርጓል ነው የተባለው።
በከተማዋ ከዚህ ቀደም በስብሰባ መድረኮች ላይ መንግስትን የሚተች ሀሳብ ሰንዝራችኋል የተባሉ መምህራንን ጨምሮ ፋኖን ደግፋችሁ ይሆናል በሚል ጥርጣሬ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በጅምላ ታፍሰው በሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ስታዲየምና በከተማዋ ጎንደር በር በሚገኘው ማር ማቀነባበሪያ ካምፕ የታሰሩ ሲሆን፡ እነዚህ ታሳሪዎችን ለመፍታት እያንዳንዳቸው ከ10 ሺ ብር ጀምሮ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እና ከዛ በላይ እንደተጠየቀባቸው መረብ ሚዲያ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
ከነዚህ መካከል በርካቶች የተጠየቀባቸውን ገንዘብ ከፍለው ከእስር ሲለቀቁ፡ ነገር ግን ጥቂቶች የተጠየቁትን ገንዘብ መክፈል ሳይችሉ ቀርተው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ቀሪዎቹ ደግሞ "ከባድ ወንጀለኛ ናቸው" ተብለው ወደ ሌሎች ማጎሪያ ካምፖች እንዲዛወሩ ተደርገዋል።
© መረብ ሚዲያ
#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
07/05/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra