የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በፒያሳ መልሶ ማልማት አካል የሆኑ ዘመናዊ የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤት በ6 ወራት ለመገንባት ከኦቪድ ግሩፕ ጋር ተስማማ
የፒያሳ መልሶ ማልማት አካል በሆነው በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ግዙፍ የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤት በ6 ወራት በሆነ ጊዜ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሽን ዋና ሥራ አሰፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና የአቪድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ ስምምንቱን ፈርመዋል ።
በስምምነቱ የወርቅ ቤቶች የንግድ ሱቅ ሞል ( FHC Gold Plaza ) ፣ መዝቦልድ ሞል እና ጣይቱ የመኖሪያ አፓርትመንት በአልሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ ለ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ወደ አገልግሎት ለማስገባት የሚያስችል ነው፡ ፡
ግንባታውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁም ተገልጿል።
የአዲሲቷ ፒያሳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ጉልህ አስተዋጽዖ ያላቸው የንግድ ሞሎችና ኘላዛዎች በአጭር ጊዜ ተገንብተው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት ተናግረዋል ።
በተጨማሪም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤትም በዚሁ ስፍራ እንደሚገነባ ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።
ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር የዘረጋ በመሆኑ የሳይቶቹን ግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚያስችለውም ተናግረዋል።
በኮርፖሬሽኑ ታሪክም በብዛት እና በዘመናዊነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገነባ የመጀመሪያው የንግድ ሞሎችና ፕላዛ ግንብታ ፕሮጀክት እንደሆነም ክቡር ዋና ሥራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።
የአቪድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ከኮፖሬሽኑ ጋር በመሆን በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ገንብተው ማጠናቀቃቸውን አሰታወሰው ፣ ውለታ የገቡትን የንግድ ሞሎችን እና የመኖሪያ ቤቶችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቪድ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል።
ሳይቶችን በ6 ወራት ለማጠናቀቅ የሚያስችለው የአልሙኒየም ፎርምወርክ ቴክኖሎጂም ለግንባታ ዝግጁ ማድረጋቸውንም አቶ ዮናስ ታደሰ አስተውቀዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ምቹ እንደሆነም ገልፀዋል።
ሞሎቹ እና የመኖሪያ ቤቶቹ የሚገነቡት በፒያሳ መልሶ ማልማት ለልማት ዝግጁ በሆኑት የኮርፖሬሽኑ ይዞታዎች ላይ ነው፡ ፡