Good news : የኦሮሚያ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልልና አካባቢው ይንቀሳቀስ ከነበረው ቡድን መሪ ጃል ሠኚ ነጋሳና እሱ ከሚመራው ሀይል ጋር የሰላም ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርሟል። ይህ ውሳኔ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ዜና ነው። ሌሎቹም ሀይሎች የህዝባቸውን ድምፅ ሰምተው ባስቸኳይ ወደሰላም መድረክ ሊመጡ ይገባል።
በቦታው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተገኝተው የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ሃይሎችም ሆነ የሰላም ጥሪ ላቀረበው አካል ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎቹም አካባቢዎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።
በቦታው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተገኝተው የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ሃይሎችም ሆነ የሰላም ጥሪ ላቀረበው አካል ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎቹም አካባቢዎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።