ዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።
ከብድሩ 90 በመቶው የንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጧል።
ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።
ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚለቀቀው፣ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው። የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደኾነም ባንኩ ባሠራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።