የኢትዮጵያ መርህ....ሠላም ነው!
ሰሞኑን ሚዲያው ሁሉ ቅኝቱ የጦርነት ሆኗል። አንዳንድ ተስፈኞች ደግሞ ኢትዮጵያ ካሁን አሁን ወደጦርነት ገባችልን ብለው በተስፋ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ባለፈው "ከሶማሊያ ጎን ነን" ይሉ የነበሩት ዛሬ ጎን ቀይረው "ከኤርትራ ጎን ነን" ሲሉ ሰማን። ገዢ ይኑር እንጂ ራሳቸውን ለመሸጥ ታጥበውና ታጥነው እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ቁርጠኛ የኢትዮጵያ ልጆች ግን ጉዳዩን በጥሞና እየተከታተሉ ነው።
ለጠላትም ለወዳጅም ግልፅ ማድረግ የምንፈልገው ነገር....ኢትዮጵያ የጦርነት ፍላጎት የላትም። ጦርነትን ለማስቀረትም ትሰራለች።
ጦርነት ተገደህ የምትገባበት እንጂ "ለምን አየኸኝ" ብለህ የምትጀምረው የሰፈር ጠብ አይደለም። ጦርነትን አይተነዋል። እናውቀዋለን። በፍፁም የመጀመሪያ ምርጫችን ሊሆን አይችልም። በተለይ ድንበር፥ ታሪክ፥ ቋንቋ፥ ባህል፥ ከምትጋራው ጎረቤትህ ጋር የምትገባው ጦርነት ብታሸንፍም የማታሸንፍበት እንደሆነ እንረዳለን። የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊስ ግልፅ ነው። እሱም "በጋራ ተጠቃሚነት ላይ አብሮ መስራትና በጋራ ማደግ" ይባላል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውም ሐገር ላይ ወረራ ፈፅማ አታውቅም። ወረራ ሊፈፅም ያሰበን ቀጥተን መመለስ እንደምናውቅበት ሁሉ የሌላውን ድንበርና ሉአላዊነት ማክበርም እናውቅበታለን።
ኢትዮጵያ የትኛዋም ሐገር ልታነሳው የምትችለውን የባህር በርም ሆነ ተዛማጅ ጥያቄ ጠይቃለች። ይሄን ለማሳካትም ቀን ከሌት ትሰራለች። ነገር ግን ይሄን የምታደርገው የሌሎችን ሉአላዊነትና ጥቅም ረግጣ አይደለም። የምንኖረው በሰለጠነ ዘመን ነው። ውይይት፥ ድርድር፥ ሰጥቶ መቀበል፥ የማይፈታው ቋጠሮ የለም። ሐገር እየመራህ በደበረህ ቁጥር ህዝብን አፋፍሰህ ወደጦርነት የምትማግድበት ግዜ አልፏል። የፖለቲካ ችግር የሚፈታው በፖለቲካዊ መፍትሄ እንጂ በአፈሙዝ አይደለም።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን የሚባል ጦር የገነባችው በየአመቱ ጂኦግራፊ ያጣመረንን ጎረቤቶቻችንን ለመውጋት አይደለም። የኛ ጥያቄ የሚመነጨው ከህግ፥ ከታሪክና ሐገራችን ካለችበት አሁናዊ ሁኔታ እንዲሁም ከህዝባችን ዘላቂ ጥቅም አንፃር ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ባለፉት ስድስት ወይም ሰባት አመታት ለሰላም ስንል የሄድንባቸው ርቀቶች ምስክሮቻችን ናቸው።
አለም እስኪደነቅ ድረስ ከኤርትራ ጋር የነበረን የዘመናት ግጭት በሰላም ፈትተን አሳይተናል። ለአመታት የዘለቀ ጦርነትን በእርቅ ፈትተን አሳይተናል። በተለያየ ግዜ ሐገር ውስጥ ካሉ ታጣቂዎች ጋር ያለብንን ችግር በእርቅ ፈትተን አሳይተናል። ነገም ለሰላም ሲባል ብዙ ርቀት ለመጓዝ ዝግጁ ነን።
እኛ በሰበብ አስባቡ እየሳቅን ወደእሳት የምንማግደው ትርፍ ትውልድ የለንም። ለፖለቲካ ትርፍ ብለን ጦርነት ውስጥ የምንጨምረው ወጣት የለንም። የየአንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነፍስ የከበረ ዋጋ አላት። አጥራችን ሲታለፍ። መስመራችን ሲረገጥ የማንታገሰውን ያህል ለሰላም ስንል የመጨረሻዋን እድል ሁሉ እንደማናባክን አለም ያውቃል።
ስለዚህ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ኢትዮጵያ የምትዋጋውም ለመዋጋት ያቀደችው ጦርነት የለም። ይልቁኑ ጦርነትን የመጨረሻ መፍትሄ ያደረጉ ሀይሎች ካሉ "ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ" ይላልና ቃሉ በእብሪት ያበጠ ደረታቸውን መልሰው ለሰላምና ለዘላቂ ጥቅማችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመወያየት ቢዘጋጁ ለሁላችንም ይበጃል ባይ ነኝ።
የበሬ ቆ*ጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል እንደዋለችው ቀበሮ፥ ኢትዮጵያ ካሁን አሁን ወደጦርነት ገባች ብላችሁ ተስፋን ለሰነቃችሁ የቀበሮ ባህታውያንም ተስፋ ቆርጣችሁ ወደቀድሞ አሰልቺ ትንታኔያችሁ እንድትመለሱ እንመክራለን።
ሰላም ለሐገራችን!
ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር!