ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደሆነ ወደ አለመገረዝ አይመለስ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥19-20) (ቁ.18) ፦ ሳይገረዝ አምኖ የተጠመቀ ክርስቲያን ሳንገረዝ መኖር ይችላል ። የአንድምታው ተርጓምያን ሐዋርያው ይህን አሳብ ያነሣበትን ምክንያት ሲገልጹ"ግዙር ቆላፍ አምነዋል ግዙር ቆላፍነትን ተመኝቶ ነበር ቆላፍም ግዙርነትን ተመኝቶ ነበር " ይላሉ ። ሐዋርያው ያለገረዘም ባለመገዘሩ ፣ የተገረዘም በመገዘሩ እንዲጸኑ ጽፎላቸዋል ።
መገረዝም ቢሆን አለመገዘርም ቢሆን ከንቱ ነው ። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ(ቁ.19) ፦ ገላ 5፥6፣6፥15 ያነጻጽሩ ። ሰውን የሚያጸድቀው የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አያጸድቅም ።
እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር(ቁ.20) ፦ ተገርዞ የተጠራ ተገርዞ ይኑር ። ሳይገረዝ የተጠራ ሳይገረዝ ይኑር ። ("የሐዋርያው የቅዱሰሰ ጻውሎስ መልእክታት ከሮሜ እስከ ገላትያ" መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ ዳምጤ ገጽ-237)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ