+ ንስሐ ግቡ +
የጌታቻን የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ አሰቀድሞ በዮሐንስ ለሀጥያት ስርየት ማጥመቅ መንገድ ጠራጊነት የተጀመረ ነው እርሱም እኔስ ለጠጅ ፡ ቢረሌን ፡ ለልብስ ፡ ገላን ፡ እንዲያጥቡለት ፡ ለሱ ፡ ጥምቀት በሚያበቃ ጥምቀት አጠምቃቹሀለው ይል ነበር እንዲሁም እርሱ የሚያጠምቀው ጥምቀት ክርስቶስ ከሚያጠምቀው ጥምቀት ልዩ መሆኑን ሲገልፅ "በመንፈስ : ቅዱስ : እሳትነት" ክፍውን : ሕሊና : ከበጎው : ሕሊና የሚለይበት ስልጣነ ክህነት ገንዘቡ የሚሆንለት በማለት ይገልፃል ። ዮሐንስ ትንቢት የተነገረለት ያለነቀፌታ ይኖሩ ከነበሩ በእግዚአብሔር ፈት ጻድቃን ከነበሩ ከካህኑ ዘካርያስ እና ከኤልሳቤጥ የተወለደ ነው ። በሉቃ 8-11"
***
በእግዚአብሔር ፈት በቤተ መቅደስ ገብቶ የማጠን ተራ በመዓት አንድ ጊዜ የደረሰበት ካህኑ ዘካርያስ በመሰዊያው ቀኝ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት ታየው ። ይህም በዓመት አንዴ ሳይሆን አንድ ጊዜ በፈሰሰ ደሙ አለምን የሚያድን አምላክ ሊወለድ መሆኑን ሲነግረው ነው አንድም ካለመታዘዝ ወደ መታዘዝ የሚመልስ ከጣኦት አምላኪነት ወደ እግዚአብሔር አምላኪነት የሚመልስ ልጅ ትወልዳለህ ሲለው ነው በተጨመሪም በቀኝ እጁ አምላክን የሚያጠምቅ ልጅ ትወልዳለህ እያለ መንገሩ ነው ("ጸያሔ ፍኖት" ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ) ።
ለዚህም ነበር በሰፈው ፈት ፃድቃን መስለው ይታዩ ለነበሩት በእግዚአብሔር ፈት ፅድቃቸው ከተመሰከረላቸው ቤተሰብ የተገኘው ዮሐንስ እርሱ በጌታ ፈት ታላቅ የሆነ ሉቃ 1፡15 በህሊና የተሰወረውን ክፍ ግብራቸውን ሳይፈራ እግዚአብሔር ገልጦለት ይገስፃቸው ነበር ፈሪሳውያንን "መልካም ፍሬ የማያፈራ ይጣላል " ማቴ 3-10 እያለ የነብያት ልጆች መሆናቸው ብቻ ንስሃ ካለመግባታቸው የሚመጣባቸውን ቅጣት እንደማያስመልጣቸው ክቡዳነ አእምሮ ለሆኑት ለእነርሱ "ንስሀ ግቡ" እያለ ያስተምራቸው ነበር ። ምንመካባቸው ብዙ የተከማቹ ሀብት ይዘን ሊሆን ይቻላል በዘመንድ ብዛት የእከሌ ዘመድ የእከሌ ዘር እያልን ምንመፃደቅባቸው በሰው ፈት ከሁሉ የተሻልን ለመምሰል የምናቀርባቸው ቁሶች ከመቃብር አይሻገሩም ያለን ግዙፍ ቤት በሁሉ ፈት ለመመካት ይዘነው አንዞርም አንድ ቦታ እንደተተከለ ይቀራል የሰማይ መንግስት እንወርስ ዘንድ ዮሐንስ ዛሬም "እንግዲህ ለንስሐ የሚያበቃቹሁን በጎ ስራ ስሩ" ይለናል " ማቴ 3-8 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል " ጸጋስ ይሉሃል የኃጥያት ስርያት ማግኘት "
እንኳን አደረሳቹሁ ። !!!
(ዲያቆን ፍፁም ከበደ)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ