Habesha Beauty dan repost
🌹#እመቤታችንን ማመስገኛ ጸሎት ውዳሴ ዘረቡዕ🌹📗
💖🌹💖
📌•••የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ የሰማያት ሠራዊት(መላእክት)ንዕድ ነሽ ይላሉ ድንግል ማርያም የምስራቅ ደጅ ናት ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘምና አንድ ልጁን ላከው በአንችም ሰው ሆነ ቅድስት ሆይለምኝልን
፪ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ብቻ ያመሰግኑሻል ፫ *የእግዚአብሔር* ሀገር (ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ *ማርያም ሆይ* ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ካንቺ ለተወለደውም ይሰግዱለታል ያገኑታልም *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን ፬ የዝናም ውሃ የታየብሽ የዕውነት ደመና አንች ነሽ አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይል ጋረደሽ *ማርያም ሆይ* ለዘለዓለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን የወለድሽልን መጥቶም ከኃጢአት አዳነን ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምስራችን የተናገርክ መልአኩ *ገብርኤል ሆይ* የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርኽን ለድንግል *ማርያም* ጸጋን የተመላሽ ሆይ *እግዚአብሔር* ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርካት *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን ፭ ጸጋን አገኘሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይልም ጋረደሽ (ጸለለብሽ) *ማርያም ሆይ* በእውነት ቅዱሱን ወለድሽ ዓለምን ሁሉ የሚያድን መጥቶ አዳነን *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን ፮ አንደበታችን የድንግልን ሥራ ያመሰግናል ጌታችንና መድኃኒታችን *እየሱስ ክርስቶስ* በዳዊት አገር ከእርስዋ ስለተወለደ አምላክን የወለደች *ማርያምን* ዛሬ እናመስግናት አሕዛብ ኑ *ማርያምን* እናመስግናት እናትና ድንግልን ሁለቱንም ሆናለችና ርኩሰት የሌለብሽና የአብ ቃል መጥቶ ካንቺ ሰው የሆነ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ ነውር የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ ስለቀደመ ሰው አዳም ሁለተኛ አዳም የሆነ *የክርስቶስ* ማደሪያው የምትናገሪ ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ ከአባቱ ያልተለየ አንድ እሱን የተሸከምሽ ሆይ ደስ ይበልሽ በክብር ጌጥ ሁሉ ያጌጠ እርሱ መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንጽሕት የሠርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ የመለኮት እሳት (ባሕርይ) ያላቃጠለሽ ዕፀ ጳጦስ ሆይ ደስ ይበልሽ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊ መለኮትን በሥጋ የተሸከምሽ ገረድና እናት ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ ስለዚህ ንጹሓን ከሆኑ መላእክት ጋር በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተን እናመስግን በሰማይ *ለእግዚአብሔር* ምስጋና ይሁን በምድርም ዕርቅ ይሁን እንበል ክብርና ምስጋና ጌትነት ያለው እርሱ አንችን ውድዋልና *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን፯ ከቅዱሳን ክብር *የማርያም* ክብር ይበልጣል የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል *ማርያም* በማኅፀንዋ ተሸከመችው ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ላንዱ ማደሪያ ሆናለችና የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህች ናት ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው በቅዱሳን ላይ የሚያድር *እግዚአብሔር* እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ ስለ ተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኖዋልና ቃል ተዋህድዋልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው *እግዚአብሔር ልጅ* በርግጥ ሰው ሆነ ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው *እየሱስ ክርስቶስ* እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን ፰ ነብዩ ሕዝቅኤል ስለ እርስዋ መሰከረ ድንቅ በሆነ ታላቅ ቊልፍ የተዘጋች ደጅ ምሥራቅ አየሁ አለ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን ፱ ኆኅትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት እርሱን ከወለደች በኃላ እንደ ቀድሞው በድንግልና ኖራለችና መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለድሽ ሆይ የማኅፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው አንቺ ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ የዕውነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖሩ ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ላንቺ ይገባል የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ ከሰው ጋርም ተመላለሰ መሐሪ ይቅር ባይ ሰውን ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን *ቅድስት ሆይ* ለምኝልን።
https://t.me/Orthodox_Tewahedo23