📕#ቅዱስ_ላሊ_በላ🌹
📘☞ወር በገባ በ12 ታስቦ የሚውለው ቅድስናን ክንግስና ጋር ንግስና ከቅድስና ጋር አስተባብሮ የያዘ ቅዱስ ላሊበላ ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡
☞ከዕለታት በአንድ ቀን ቅዱስ ላሊበላ እራት ሊበላ ሲዘጋጅ እንዲህ ሆነ፡፡
☞ሦስት ሰዎች በቤተ መንግሥቱ አዳራሽ አቅራቢያ እርሱ ወደ ተቀመጠበት
መጡ፡፡ እነዚህ ሦስት ሰዎች አቤቱ ጌታችን ምንበላው ሥጠን ዛሬ የምንበላው
የለንምና ብለው ለመኑት አንዱ ይህን በአለው ጊዜ ቅዱስ ላሊበላ ሊጎርስ በእጁ
የያዘውን አንዱ ጉርሻ ሠጠው፡፡
☞ሁለተኛም እንደዚያ ለመነው፡፡ለእርሱም ሁለተኛውን ጉርሻ ሰጠው፡፡
ሦስተኛውም እንደዚያ ለመነው ሦስተኛውን ጉርሻ ለሦስተኛው እንዲሰጠው
ረዱን አዘዘው፡፡
☞ቅዱስ ላሊበላ ሲመገብ ያለ ሶስት ጉርሻዎች አይበላም ነበርና ሦስቱም
ፈጽሞ ተሠጠ ረዱ የቅድስ ላሊበላ ምግብ እንዳለቀ ባየ ጊዜ የእንጀራውን
ጠርዝ ወስዶ በጎመን ለውሶ እንዲበላ ሠጠው፡፡
☞ቅዱስ ላሊበላ የምበላው ሰሦስቱን ጎርሻ ለተቸገሩት ከሰጠሁ በኃላ ሌላ
ቁራሽ እመገባለሁ ብሎ እምቢ አለ፡፡ ይህንን የሰጠህኝንማ ከበላሁ ስለ ሰጠሁት
ፈንታ ሌላውን ብበላ እንዳልሰጠሁ መሆኔ ነው ብሎ፡፡ ይህን ተናግሮ ቅዱስ
ላሊበላ ጾሙን አደረ፡፡
☞ይኸውም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን ውደዱ
የምትለዋን በሐዋርያው አንደበት የተነገረችውን ቃል ፈጽሟታልና፡፡
☞ይህችው ቃል በቅዱስ ላሊበላ ተፈጸመች፡፡ራሱ ተርቦ ሌሎዎችን
እንዲያጠግብ፡፡ራሱ ተጠምቶ ሌሎችን እንዲያረካ፡፡ ጌታ በወንጌል ስለ ጽድቅ
የሚረቡ የሚጠሙ ንዑዳን ናቸው እነሱ ደስ ይሰኛሉ ይጠግቡማል እንዳለ፡፡ ማቴ
ም 5፡፡ ይህችንም ቃል ለመፈጸም ቅዱስ ላሊበላ እራሱ የሚመገባቸውን ሦስት
ጉርሻዎች ሰጠ፡፡
☞ ንጉሥ ሲሆን የሚሠጠው አጥቶ አይደለም በእግዚአብሔር ዘንድ ዎጋ
እንዲያገኝ ምግቡን ሠጠ እንጂ፡፡
☞ከዚህም በኃላ ለሦሥቱ ሰዎች ረዱን ሌላ የሚበላ የሚጠጣ ተራቁተውም
ሲያይ ልብስ እንዲሠጣቸው አዘዘው፡፡
☞አገልጋዩ ረዱም በወጣ ጊዜ እኒዚያ ሦስቱ ሰዎች ወደ ሰማይ ሲያርጉ
አያቸው፡፡
☞ወደ ገብረ መስቀል(ቅዱስ ላሊበለ) እንዲጎበኙትና ቸርነቱን ለመፈተን የመጡ
መላእክት ናቸውና፡፡
☞ጌታችንም እንግዳ ተቀባዮችን ራሱ እንግዳ ሆኖ ይጎበኛቸዋልና፡፡ ከአብርሃም
ቤት እንግዳ ሆኖ እንደገባ ዘሩንና እሱን እንደባረካቸው፡፡
☞ቅዱስ ላሊበላ በዘመነ መንግሥቱ ከሦስቱ ጉርሻ በስተቀር ሌላ
አልተመገበም፡፡ ከአንዲት ጽዋ ውሃ ሌላ አይጠጣም ነበርና፡፡
☞ጸሎት ልመናው ተራዳይነቱ በዚህ በቅዱስ እና በንጉሥ ላሊበላ በጸሎቱ
ለምታምኑ ይሁን፡፡
☞( ገድለ ቅዱስ ላሊበላ)
☞11-9-2014