"በዚች በኅዳር 12 ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሁል ጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኀይላት ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ ነው ::
እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ኑሮ ነጻ አውጥቶ መና አውርዶ ደመና ጋርዶ አለት ሰንጥቆ ውኃ አፍልቆ ጠላት ገድሎ ባሕር ከፍሎ እየመራ ምድረ ርስት ያስገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው በዚህም ‹‹ መጋቤ ብሉይ ›› የሚል ቅጽል ተሰጥቶታል ።
ቅዱስ ያሬድ ስለዚህ ገናና መልአክ ሲመሰክር ‹‹ ሚካኤል ቀን በደመና ሌሊት በብርሃነ እሳት መራቸው ፤ በእስራኤል በጎዳናቸው ፊት ፊት እየሔደ ሕዝቡን በደስታ አወጣቸው ! መልአኩን ላከ አዳናቸው ፡፡ ›› በማለት ታዳጊነቱን ዘምሯል ።
እንዲሁም በዚህ በኅዳር_12_ቀን የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ሚስቱ ቴዎብስታ ትባላለች ሁል ጊዜ ያለ ማቋረጥ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉ መታሰቢያ ያደርጉ ነበር በሚኖሩበትም በሀገር ውስጥ ችግር ሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚሆን የሚያደርጉበትንም ገንዘብ አጡ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ተመስሎ ለዱራታዎስ ተገለጠለት ።
የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም የበዓሉን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ታላቅ ቸርነትን አደረገላቸው ቅዱስ ሚካኤልም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ እኔ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምፅዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት የሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ ።እርሱ :ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መልአክ ነው ሥልጣኑም ታላቅ ነው በችግራችን ጊዜ ይለምንልን ዘንድ ረዳትም ይሆነን ዘንድ ክንፎቹንም ዘርግቶ : ይጋርድልን አሜን በእውነት🙏⛪😥