"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
☞ታህሳስ 13 የሴቶችን ማሕፀንን የሚፈታ የታላቁ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ
ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ነው፡፡ ይህ እንዴት ነው ቢሉ
☞ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ከሞት በኃላም የንጉሥ አርቃዴዎስ ታላቅ ወንድም
የመጀመሪያው ልጅ አኖሬዎስ በቁስጥንጥያ ነገሠ፡፡
☞ቀድሞ ለተወደዱ ኹለቱ ወንደሞች ለቴዎዶስዮስ ናዲዮስዮስ ማረፊያቸው
በነበረች ኃላም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል በቅድስት ሥዕሉ ላይ አድሮ ታላቅ
ተዐምራቱን በገለጸባት ሥፍራ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ለሰው ፈጥኖ
በሚደርስ አማላጅነቱ በከበረ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል ስም አባቱ
የጀመረውን የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ይፈጽም ዘንድ አሰበ፡፡
☞ይኸ ንጉሥ አኖሬዎስ የታላቁ መላዐክ የቅዱስ ሩፋኤል አምላክ የእግዚአብሔር
ቤት በሊቀመላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል ስም ይሰራ ዘንድ ጀመረ፡፡
☞ይኽቺን ቅድስት ቤተክርስቲያን ያንፅ ዘንድ በጀመረ ጊዜና ገና መቁፈር
ሲጀምር ወርቅ ሙሉ ጋኖችን አገኙ ጻድቁ አኖሬዎስ መሬቱን በሰፊው ይቆፍሩ
ዘንድ እንደገና አዘዛቸው፡፡
☞በሚቆሩም ጊዜ እየ አንድ አንዱ ዐሥራ አምስት ሚዛን የሚመዝን ሰማኒያ
አራት የወርቅ ጥምዝ አገኙ፡፡ ቁፋሪዎቹም የኸን ባገኙ ጊዜ የኾነው ኹሉ ያውቅ
ዘንድ የሚነግሩት መላክተኞችን ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ ላኩ፡፡
☞ንጉሥ አኖሬዎስ ሰምቶ በታላቅ ደስታ ከሠራዊቱ ጋር ወደ ቁፋሮው ሥፍራ ሔደ
የወርቁን ክሞችት ባየ ጊዜም ለዘለዓለሙ ክብር ምስጋና ይግባውና
የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደኾነ አስተዋለ፡፡
☞ቅዱስ ስሙ የሚመሰገንበት ቤቱን ያንፅ ዘንድ በሊቀ መላእክት ቅዱስ
ሩፋኤል አማላጅነት የመረጠው ልዑል እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነ፡፡
ስለዚህ በንጉሡና በሠራዊቱ ኹሉ በሕዝቡም ዘንድ እጅግ ታላቅ ደስታ ተደረገ፡፡
☞ያንጊዜም ንጉሥ አኖሬዎስ ወርቁን በእሳት ያጠሩት ዘንድ አዘዘ፡፡ አባቱ ንጉሥ
ቴዎዶስዮስና ንዑድ ክቡር የኾነ የተወደደ ጻድቅ አባ ዲዮናስዮስ ቀድሞ
በማረፊያቸው አኑረውት በነበረው ሥዕል ዐይነት ታላቅ ሥዕሎ በሠዐሊ ዐሣለ፡፡
☞የዐሣለውን የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል ታላቅ ሥዕልም በተገኘው ወርቅ
ያክንትና ጳዝየን ወራዉሬም የተሰኙ የከበሩ የአልማዝ ድንጋዮችን ጨምሮ
ዙሪያውን አሰጌጠው፡፡ ይኸን የሊቀመላዕከት ቅዱስ ሩፋኤልን ሥዕል የቤተ
ክርስቲያኗ ሕንፃ ሥራ እስኪ ፈጸም ድረስ በተለየ ንጹሕ ሥፍራ አኖረው፡፡
☞እጅግ በጸና ፍቅርና ሰላምም የቤተ ክርስቲያኗ ሥራ እንዲህ ተጀመረ፡፡
እግዚአብሔር የሚፈራ ይኸ ጽድቅ ንጉሥ አኖሬዎስ ከጠቢባኑ ጋር እየተማከረ
ከጠራቢዎች ጋር እየጠረበ ከሚቁፍሩት ጋር እየቁፈረ አብሯቸው በእጁ ይሠራ
ነበር፡፡
☞በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል ስም የሠራት የዚህቺን ቤተክርስቲያ
አሠራርም በብልሃተኛ ክንድ ልክ ስፋቷን ሰማኒያ ክንድ ወርዷንም ስድሳ ክንድ
አደረገ፡፡ ውስጧንም በተቀረፀ የእንጨት ጌጥ ሽለማት፡፡
☞በቅኔ ማኅሌቷ አንፃር ያለውን የቅኔ ኅሌቷን ቁመት ኅምሳ ክንድ አደረገ፡፡
ውስጡንም በዥንጉርጉር ቀለም አሳመረው በጠፊሯም የተሸረበ ገመድ ታታ፡፡
ረጃጅም ምሶሶዎችንም አንዱን በግራ አንዱንም በቀኝ ተከለ፡፡ ለገናናው ቅዱስ
ሩፋኤል ቤተክርስቲያንም ይኸን ከዳረገ በኃላ ሕንፃው አምሮ ተፈጸመ፡፡
☞የቅዱስት ቤተክርስቲያኗ ሕንፃ በተፈጸመ ጊዜም ንዑዳን ክቡራን አበው
ሊቀነጳጳሳትና ጳጳሳቱ ካህናት መዘምራኑ ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱ አሰከትለው
ከቅዱስ ሩፋኤል ታቦት ጋር ለቅዳሴም ስንዴና ዘቢቡን ጧፍና ዕጣኑን የወርቅ
ጽዋ ሞጉናጸፊያና መጋራጃዎችን የብርና የወርቅ ጽናዎችን የክህነት ልብሶችን
የብሉይና የሐዲስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይዘው መጡ፡፡
☞የቤተ ክርስቲያኗ ቅዳሴ ቤቷም በዝማሬና በማኅሌት በዚች በታህሳስ 13 ቀን
ከበረ፡፡ በቅዳሴ ጊዜም መንፈስቅዱስ ወርዶ ቤተ ክርስቲያኗን ቀደሳት፡፡
☞ጳጳሳትና ካህናት ከሕዝቡም መሐል ወደ ቅዱስ ሥጋውና ወደ ክቡር ደሙ
የቀረበውን ሥጋና ደሙን ተቀበሉ፡፡
☞የቅዳሴ ቤቱ በዓልም በተፈጸመ ጊዜ ታላቅ ግብዣ ተደረገ፡፡ ኹሉም ከድኾች
ጋር አንድነት በልተው ጠገቡ፡፡ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስምም ምጽዋትን
ለተቸገሩት ድኾችና ለሽማግሌዎች አባትና እናት ለሌላቸው ሰጡ፡፡ ቅዳሴ
ቤቱንም በዚህ መልኩ ተከበረ፡፡
☞የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ምልጃውና ጥበቃው አይለያችሁ፡፡
☞(ድርሳነ ሩፋኤል)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞