"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒 dan repost
✳"ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ" ዕዝ ሱቱ ፪÷፩
✥ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቀ መላእክት አንዱ ነው። መላእክት በስማቸው ቅጥያ ኤል የሚል ቃል አለ ይኸውም እግዚአብሔር ማለት ነው። ዑራኤል ማለት የብርሀን ጌታ፣ የብርሀን አምላክ ማለት ሲሆን "ዑር" ማለት ብርሃን፤ "ኤል" ማለትም እግዚአብሔር ማለት ነው።
✔️ቅዱስ ዑራኤል በመባርቅትና በነጎድጓድ የተሾመ መልአክ ነው። መ.ሄኖክ ፮፥፪
✥ የሰማይን ሚስጥር ለሄኖክ እውቀትን የገለጸለት መልአክ ነው። የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መ.ሄኖክ 28፥13
✥ ቅዱስ ዑራኤል ልቡናን የሚያበራ እውቀትን የሚገልጽ ርሑሩህ መልአክ ነው። ቅዱስ ዑራኤል ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋአ ልቡናን አጠጥቶት ሰማያዊ ሚስጥራትን ገልፆለታል። ነብዩ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን መጻሕፍት ደርሷል። በሰዓታቱም "ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል፡፡"/// "ነይ ወደ እኛ ድንግል ሆይ ከእስራኤል ነብያት ከኤልያስና ከኤልሳ እንዲሁም ዑራኤል ጽዋ ልቡናን ካጠጣው ከእዝራ ሱቱኤል ጋር።"
✥ ሌላኛው ቅዱስ ዑራኤል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእጸ መስቀል ላይ በቀራንዮ በአምስቱ ቅንዋት( ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ) ተቸንክሮ ሳለ ይህ ብርሃናዊ መልአክ ነው ከጎኑ የክርስቶስን ደም በጽዋ ቀድቶ በዓለም ሁሉ ረጭቶታል።
✥" እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ። ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ። ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።" በዚህ የጭንቅ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እየተራዳ መንገድን እየመራት በብርሃን ወደ ሀገረ ግብፅ ቀጥሎም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ወደ ሆነቻት ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራት መጥቷል። ማቴ 2÷13-15
✥ " ሰላም ለአእጋሪከ ወለሰኰናከ እለ ሖራ። ፍና ተራድኦ ግሙራ። ዑራኤል ለድንግል ፍኖተ ምድረ ግብፅ አመራ። ሠለስተ ዓመተ በስደት እንዘ ታስቅቁ ነቢራ። ከመ በፍስሓ ትትመየጥ ለበዊእ ሀገራ።"///" ዑራኤል ሆይ ለእርዳታ ፈጽመው ለሚፈጥኑት እግሮችህና ሰኰናህ ሰላም እላለሁ። ዑራኤል ሆይ በስደት ወራት ለድንግል የምድረ ግብፅን መንገድ ያመለከትካት አንተ ነህ። ሦስት ዓመት እያለቀሰችና እያዘነች በስደት ከቆየች በኋላ ተመልሳ ወደ ሀገሯ እንድትገባ የደስታ የምስራች ያበሰርካት አንተ ነህና።" መልክአ ዑራኤል
✥ ሌላው የእውቀትን ብርሃን የገለጸላቸው የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ለሊቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው። እኚም አባታችን በመልአኩ ተራዳኢነት ብዙ ድርሰቶችን ደርሰዋል። እመቤታችንም በምልጃዋ ቅዱስ ዑራኤል የእውቀትን ጽዋ ያጠጣቸው ዘንድ አድርጋለች። አባ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ይወዷት ስለነበረ አርጋኖን ሌሎችንም ደርሰዋል።
ዑራኤል ማለት የብርሃን ጌታ ማለት ነው
✔️ ቅዱስ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው። እርሱም መባርቅትን ለጥጋብና ለበረከት እንዲሁም ነጎድጓድን ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መ.ሄኖክ ፮፥፪
➕ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል።
🙏🙏🙏
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ዑራኤል/2/
ሰዓል ወጸሊ በእንቲአ ነአዕርግ ፀሎተነ ቅደመ መንበሩ ለመድኃኒዓለም/2/
🙏🙏🙏
ቅዱስ ዑራኤል ሆይ እኛም ተቸግረናልና እንድትረዳን ወደ እኛ ና??? ለዕዝራ ያጠጣኸውን ጽዋ እንሻለን
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
ለበለጠ መረጃ👉 "" ፔጁን ላይክ በማድረግ ዕለት ዕለት የቅዱሳኑን፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታትን፣ የነብያትን፣ የሐዋርያትን ገድል ተአምራት ይከታተላሉ እንዲሁም ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ እንወያይ መልዕክት ይላኩ......ስለጎበኙን እግዚአብሔር አምላክ በረድኤት ይጎብኝልን፤ የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት፤የጻድቃን የሰማዕታት ተራዳኝነት አይለየን አሜን።✟