እንኳን አደረሳችሁ የአብይ ፆም ሁለተኛ ሳምንት #ለቅድስት!!!
#ሁለተኛ_ሳምንት_ቅድስት
ቅድስት ማለት ልዩ፣ ጽኑዕ፣ ክቡር ማለት ነው፡፡ የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ሲሆን ለጌታ ጾም/ጾመ አርባ/ የመጀመሪያ ሳምንት ነው፡፡ ያለትናንት ቀዳማዊ፤ ያለዛሬ ማዕከላዊ፤ ያለነገ ደሃራዊ፤ ለዘመኑ ጥንትና ፍጻሜ ለግዛቱ ዳርና ድንበር የሌለበት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ ጾሙን የጀመረበት የመጀመሪያው ሳምንት ቅድስት ተብሎ የመጠራቱ ምክነያት ከዚሁ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ የአምላካችንን ቅድስና እና ሰንበት ቀድሶ በፈቃዱ እንደሰጠን እያነሣሣ ስለሚዘምር ነው፡፡
ጾመ ድጓውም እንዲህ ይለዋል፡-
“ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ - ይህች ቀን የተቀደሰች ናት
ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አዕረፍኩ - ያረፍኩባት ቅድስት ሰንበት ናት
ቅዱሳነ ኩኑ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ - እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ
አብ ቀደሳ ለሰንበት - አብ ሰንበትን አከበራት ቀደሳት”
ስያሜው ሰንበት የዕረፍት ቀን እንድትሆን በኦሪትም በሐዲስም እግዚአብሔር የባረካት የቀደሳት ዕለት መሆኑዋን የሚናገርና እግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆነ የፈጠረውም ሰውም ቅድስናን መያዝ የሚገባው መሆኑን የሚያሳስብ ነው፡፡ /ዘፍ ፪፥፫ ፤ ዘፀ ፳፥፰-፲፩ ፤ ዘሌ ፲፱፥፪-፫ ፤ ፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፭-፲፮/
⛪️መልካም እለተ ሰንበት🌷🦋🤲