ቅዱሳት አንስት (ቅዳሜ)
ከትንሳኤ ሳምንት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" (የተቀደሱ ሴቶች) ተብላ ትጠራለች::
በወቅቱ በኢየሩሳሌምና ዙሪያዋ ከተከተሉት ሴቶች ጌታችን 36ቱን መርጧል:: እነዚህ እናቶች ከዋለበት ውለው : ካደረበት አድረው : የቃሉን ትምሕርት ሰምተዋል:: የእጁንም ተአምራት አይተዋል:: ፈጽመውም አገልግለውታል::
መጽሐፍ "አንስተ ገሊላ ኩሎን::
አዋልዲሃ ለጽዮን:: አስቆቀዋሁ ለመድኅን:: ከመ ዖፈ መንጢጥ እንዘ ይሤጽራ ገጾን::" ይላልና በዕለተ ዐርብ ፊታቸወውን እየነጩ : ደረታቸውን እየደቁ : እንባቸውም እንደ ጐርፍ እየፈሰሰ አብረውት ውለዋል::
ጌታም ፍጹም ፍቅራቸውን ተመልክቷልና ከሁሉ አስቀድሞ ትንሳኤውን ለእነሱ ገለጠላቸው:: እነርሱም ትንሳኤውን በመፋጠን አብሥረዋል:: "ሰበካ ትንሳኤ፡ አዋልዲሃ ለጽዮን" እንዳለ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" ተብላ ትከበራለች::
አምላካችን በፍቅርና በቅድስና ጌጥ ካጌጡ እናቶቻችን በረከትን ያድለን::
መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው:- 'እናንተስ አትፍሩ:: የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና:: እንደተናገረ ተነስቷልና በዚሕ የለም:: የተኛበትን ሥፍራ ኑና እዩ:: ፈጥናችሁም ሒዱና ከሙታን ተነሣ: እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማቹሃል:: በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሯቸው' . . . እነሆም ኢየሱስ አገኛቸውና ደስ ይበላችሁ አላቸው:: እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት:: (ማቴ. 28:5-10)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን! †