‹‹በአንቺም ምሰሶዎች ቆሙ ሕንፃዋም ባንቺ ጸና ግድግዳዋም ባንቺ ተሠራ፡፡ ጠፈርዋም ባንቺ ተፈጠረ ፣ ዋልታዋም ባንቺ ተዋቀረ ጭምጭምታዋም ባንቺ ተጨመጨመ፡፡ ደጆቿም ባንቺ ተከፈቱ ፣ መቃን መድረኳም በልጅሽ ደም ተረጨ ፡፡ በአንድ ልጅሽ መስቀል ፍሬ ያፈራችው ቅድትስ ቤ/ክ ታመሰግንሻለች ፤ ከርኩሰቷም በሆድሽ ፍሬ ደም የነጻችው ፣ ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው ፣ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤ/ክ ታመሰግንሻለች፡፡ ቅድስት ድንግል ሆይ ምስጋናሽ በሁሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዳርቻ ሁሉ ሰፈፈ የውቅያኖስ ባሕር በመደቡ የተወሰነ ነው ፣ የሐኖስም ባሕር እንደ መጠኑ ልክ አለው ያንቺ ምሥጋና ግን ልክ፣ወሰን፣ሥፍር፣ቁጥር፣ማለቂያ የለውም ፤ አዕምሮ ሊወስነው፣አንደበት ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም፡፡ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ሁሉ ላንቺ ሆነ ፣ ሁሉ ስላንቺ ተፈጠረ፡፡ አዳም ከኅቱም ምድር የተፈጠረ አንቺን ያፈራ ዘንድ ነው፡፡ ሔዋንም ከአዳም ጎን የተፈጠረች አንቺን ትወልድ ዘንድ ነውና›› ፡፡ (አርጋኖን ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲✝
ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲✝