#ጥቆማ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም ያስቀመጠውን የዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ ያመጡና በፖሊስ ሙያ ዘርፍ ለማገልገል የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአራት ዓመታት
በፖሊስ ሳይንስ በዲግሪ ፕሮግራም አስተምሮ በረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ በማስመረቅ በፌደራል ፖሊስ የሥራ ክፍሎች በማስመደብ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
መስፈርቶች፦
➻ በፖሊስ መኮንንነት ሀገሩን ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ያላት፣
➻ ከወንጀል ነጻ ስለመሆናቸው ከሚኖሩበት አካባቢ ፖሊስ ጽ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
➻ ለፖሊስ ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና የአዕምሮ ጤንነት ያለው/ያላት፣
➻ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/የሆነች፣
➻ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣
➻ ከተመረቁ በኋላ ለሰባት ዓመታት በተማሩበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ተመድቦ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ፣
➻ ሴት አመልካቾች ከእርግዝና ነጻ መሆን አለባቸው፣
➻ ከዚህ በፊት የፖሊስ/የመከላከያ ስልጠና ያልወሰዱ፣
➻ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጥን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ።
በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ መቁረጫ ውጤት ያላቸው ወይም በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት የማለፊያ ውጤት ያመጡ ማስረጃ በማቅረብ ማመልከት ይችላሉ።
➻ ቁመት፦ ለወንድ 1.65 ሜ. እና ከዚያ በላይ ፤ ለሴት 1.55 ሜትር እና ከዚያ በላይ
➻ ዕድሜ፦ ከ18 እስከ 28 ዓመት
በትምህርት ወቅት ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ፣ የምግብ እና የጤና አገልግሎት በተቋሙ ይሸፈናል።
የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://forms.gle/cPBiWRzUDx4KFRiq9https://t.me/ParoEdu