#ጓጉቻለሁ_ፍቅሬ
ጓጉቻለሁ የምር
ሽክ ብለህ እምር
ስትመጣ ወደ'ኔ
ባንተ ድምቀት ምክንያት
ሲፈካልኝ ቀኔ
እንደ ወጣቶቹ እስካይህ ዘንጠህ፣
በሱሪ በሸሚዝ በካፖርት አጊጠህ፣
ወይ እንደ አባቶችህ ጋቢና ከዘራ፣
ሰው ሰው እስክትሸተኝ ነብስ እስክትዘራ፣
ጓጉቻለሁ በጣም....
ልክ እንደ ክርስቶስ....
ባይኖርህ ትንሳኤ በሶስተኛዋ ቀን፣
ትመጣለህ በሚል እየዎዘዎዘኝ
የናፍቆት ሰቀቀን፣
መቃብር ፈንቅለህ
እስካገኝህ ባካል፣
ስንት አመት ይፈጃል መቼላይ ይሳካል፣
እላለሁ...
ሁልጊዜ እብሰለሰላለሁ...
ግን እባክህ ፍቅሬ...
ባቆሰልኩት ፊቴ በደራረብኩት ማቅ፣
ንገረኝ መምጫህን ትንሳኤህን እንዳቅ፣
በቅርቡ ከመጣህ ሳይደክም ጉልበቴ ፣
እቀበልሀለሁ ደግሼ ከበቴ፣
ምናልባት ከሆነ ...
ለመምጣት ያሰብከው...
አመታት ተቆጥሮ ዘመንን ሲገፋ፣
እንዳንጠፋፋ...
እኔው እመጣለሁ ጠብቀኝ አትልፋ።
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot
ጓጉቻለሁ የምር
ሽክ ብለህ እምር
ስትመጣ ወደ'ኔ
ባንተ ድምቀት ምክንያት
ሲፈካልኝ ቀኔ
እንደ ወጣቶቹ እስካይህ ዘንጠህ፣
በሱሪ በሸሚዝ በካፖርት አጊጠህ፣
ወይ እንደ አባቶችህ ጋቢና ከዘራ፣
ሰው ሰው እስክትሸተኝ ነብስ እስክትዘራ፣
ጓጉቻለሁ በጣም....
ልክ እንደ ክርስቶስ....
ባይኖርህ ትንሳኤ በሶስተኛዋ ቀን፣
ትመጣለህ በሚል እየዎዘዎዘኝ
የናፍቆት ሰቀቀን፣
መቃብር ፈንቅለህ
እስካገኝህ ባካል፣
ስንት አመት ይፈጃል መቼላይ ይሳካል፣
እላለሁ...
ሁልጊዜ እብሰለሰላለሁ...
ግን እባክህ ፍቅሬ...
ባቆሰልኩት ፊቴ በደራረብኩት ማቅ፣
ንገረኝ መምጫህን ትንሳኤህን እንዳቅ፣
በቅርቡ ከመጣህ ሳይደክም ጉልበቴ ፣
እቀበልሀለሁ ደግሼ ከበቴ፣
ምናልባት ከሆነ ...
ለመምጣት ያሰብከው...
አመታት ተቆጥሮ ዘመንን ሲገፋ፣
እንዳንጠፋፋ...
እኔው እመጣለሁ ጠብቀኝ አትልፋ።
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot