በትግራይ ክልል በመጀመሪያው ምዕራፍ 75 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ያለው ስራ ትልቅ እመርታ ነው ‼️
በመርሃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የቦርድ ሰብሳቢ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር)፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌተናል ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዚሁ ጊዜ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እንደገለጹት፥ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽንና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እየሰሩት የሚገኘው የመልሶ ማቋቋም ስራ ከጦር መሳሪያ ማስፈታት ባለፈ የትግራይ ክልልን ሰላምና ደኅንነት ግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የሚከናወን ነው ብለዋል።
የቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ የሚገኘው ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አዎንታዊ ውጤቶች እያመጡ መሆኑን ጠቅሰው ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ጉዳይ ቀሪ ስራ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችም ከፌደራል መንግስት ጋር በመተባበር የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በቅርበት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅትም በመጀመሪያው ምዕራፍ 75 ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶ ስልጠና መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ የሚገኘው ጥረት ትልቅ እመርታዊ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ትክክለኛውን የሪፖርተር የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ✅
📢🔴
https://t.me/ReporterET📢🔴
https://t.me/ReporterET