አድዋ
የይቻላል እና የአሸናፊነት ተምሳሌት፣
የጥቁር ህዝቦች ኩራት ድምቀትና የነጻነት ግርማ፣
የማንነታችን ጥንካሬ ተምሳሌት፣
የኢትዮጵያውያን የአንድነት አርማ፣ የማይደበዝዝ ደማቅ ታሪክ!
ቀን:- የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም.
ቦታ :- አድዋ፤ ኢትዮጵያ
ውጤት: የኢትዮጵያ ድል
አድዋ ምናልባትም አሁን የምኖርባትን አለም ቅርጽ ከቀየሩ አበይት ክስተቶች አንዱ ነዉ። ከአድዋ በፊት አለም ሁሉ የተስማማበት አንድ ነገር ነበር ነጭ ከጥቁር የበላይ ነው፤ ይሄን እንዴት ያለ እና የጠየቀ ወይም የተሟገተ የለም ቢኖርም ህዝቡ ሁሉ ዉስጡ ዘልቆ የገባ እምነት ስለሆነ ከመስማት ዉጭ የተንቀሳቀሰ የለም ያኔ እንዲ ነበራ የፈረንጅ መአት ይመጣል ይወርሀል ያስተዳድርሀል መብታቸዉ ነዉ ለምን?ነጭ ናቸዋ፤ እንዴት ነጭ ላስተዳድርህ የኔን ስም ያዝ የኔን ባህል ተቀበል ሲልህ ትመክተዋለህ።
እና በዚህ አይነቱ ማን አለብኝነት አፍሪካን የተቀራመተዉ ነጭ አንድን ሀገር ይመኛል እቺ የተከበረች ህዝቦቿ ጨዋ እንግዳ አክባሪ ሀገር። ግን እነሱም ማንነቷን ያዉቃሉ ህዝቡአን አዲስ ባህል ልስጣቹ ማለት አትችልም ባህሉን ለሺ አመታት የጠበቀ ነዉና ሀይማኖቶ ላስተምር ማለት አልቻሉም ሀይማኖተኛ ህዝብ ሀይማኖተኛ ንጉስ ተስፋዉ መድፍ ሳይሆን አምላኩ የሆነ ንጉሰ ነገስት አላት እኚ ልበቢስ ጣላኖችም ይሄን ልብ ብለዋል፤ አይችሉአትም ዘመናዊ ጦር መሳሪያ እንደሌላት አይተዋል ግን ለመዉረር ፈርተዋል አዎ ያስፈራላ ስርዓት ያለዉ ህዝብ ፈገግታ ከፊቱ ማይለየዉ ሰዉ አክባሪ ሰላምተኛ ህዝብ ላይ ያዩት አንዳች ነገር አስፈርቱአቸዋል እናም መዉረሩ እንደማያዋጣቸዉ አዉቀዋል። ከዛም የሞኝ ጨዋታ ጀመሩ በdiplomacy መጡ ይሄ የዋህ ህዝብ ሰዉ አማኝ ነበር እናም የሞኝ ስራ ሰሩ ትንሽ መሆናቸዉን ሚያሳይ ስራ ሰሩ ዋሹ አጭበረበሩ።