ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በበደሌ ከተማ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ አስተማማኙ የቴሌኮም ትስስራችን ከጋምቤላ እስከ በደሌ አገልግሎቱን ጀምሯል።
በከተማው 2 ሱቆችን የከፈትን ሲሆን ደንበኞች ወደ አገልግሎት ማዕከላት በመሔድ አገልግሎቶቻችንን ማግኘት ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ 50 የሥራ ዕድሎችን ለከተማዋ ወጣቶች የፈጠርን በመሆኑ ደስተኞች ነን።
በዚሁ ሳምንት በከተማዋ ለሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 10 ላፕቶፖችን፣ 2 ራውተሮችን እና የ6 ወር ያልተገደበ ኢንተርኔት በመስጠት ዲጂታል ትምህርትን ለማገዝ የበኩላችንን አስተዋጽኦ አድርገናል።
በአብሮነት ወደፊት!