♻️ሞገሳችንና ክብራችን፥ የመድኃኒታችን ቀንድ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
🔰በእርሱ የምናምንበት የሰላማችን ምልክት' የምንጠጋበት የድኅነታችን ግድግዳ፣ የሕይወት ደንጊያ እና የማዕዘን ራስ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
⚜የተከማቸ ወርቅ እና የተሰወረ ዕንቊ፤ የበዛ ወቄት እና የተትረፈረፈ መክሊት እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::
📍ያልተሠራ ልብስ፣ ያልተፈተለ መጎናጸፊያ፤ ዱቄቱን ያበቃው እርሾ እና አልጫውን ያጣፈጠው ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::
♻️መልካም ቀንበርና ቀላል ሽክም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::
ወደ አባቱ ለመሄድ መንገድ፣ ወደወለደው ለመግባት በር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
📍ማዕበል የማይቀርበው መርከባችን፣ ሌባ የማያገኘው ብል ነቀዝ የማያበላሸው ሣጥናችን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በንጹሐን ሥጋ ውስጥ የሚያፈራ ንጹሕ ዘር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
📍እግዚአብሔር በተከላት የምስክር ድንኳን ለንጹሐን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
💫ከምሥራቅ የወጣ ብርሃናዊ ኮከብ፣ በሰማይ የሚታይ የእውነት ፀሐይ፣ ንጹሕ የሆነ ሙሽራ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
📍በአብ ዘንድ ልጅ፤ በመንፈስ ቅዱስ ዘንድ መንፈስ፣ በድንግልም ዘንድ ሕፃን' በነቢያት ዘንድ ነቢይ፣ በሐዋርያትም ዘንድ ሐዋርያ፣ በሰማዕታት ዘንድ አክሊል (ዘውድ) የሚሆን መምህር እና የማኅበር አለቃ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ጸሎተ ሰዓታት)
@SewaswMedia