ሰዋስው ሚዲያ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ሰዋስው

# ሰዋስው ማለት መሰላል ነው።
መሰላል የማይደርሱበት ነገር ተጠቅመው እንዲቻል እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ቻናል ችግር የሚባል ነገርን አስወግዳችሁ ወደ መልካም ነገር የምትወጡበትን ትምህርት ታገኛላችሁ።
Telegram @zsewasw
መልዕክት ብቻ ያስቀምጡ

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




ኦርቶዶክሳዊ ቻናል dan repost
የአቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ የማይጠገቡ ትምህርቶች ለማግኘት ተቀላቀሉ ታተርፉበታላችሁ 🙏

https://t.me/Father_advices






📍ውዳሴ ማርያም ከመጸለያችን በፊት ደግሞ ይህን እንበል

በአማርኛ

የብርሃን ልጅ የምትሆኝ የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ
ከሰይጣን ማሰሪያ ፊችኝ።
አገልጋይሽ ቅዱስ ኤፍሬም እንደባረክሽው ባርኪኝ ቀድሽኝ።

ግዕዙ

ባርክኒ ቀድስኒ ወአንጽህኒ በከመ ባርኪዮ ለቅዱስ ኤፍሬም ፍቁርኪ እግዝእትየ ፍትህኒ እማእሰሩ ለሰይጣን እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።

የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከተ ጸሎቷ ሃብተ ረድኤቷ አይለየን።

YouTube
  @sewaswmedi1
Telegram @zsewasw
Tiktok @zsewasw
Facebook @Sewasw2


ብዙኃን ማርያም 📍

እንኳን አደረሳችሁ።

@SewaswMedia


እንኳን ደስ አላችሁ ጥበበኛው መምህር ተጠናቆ በህትመት ላይ ነው። ይህን መፅሀፍ እንድጨርሰው ዘወትር ጫና ስታደርጉብኝ የነበራችሁ ልጆች ዘወትር የምትጠይቁኝ እነሆ ጊዜው  ደርሶ ተጠናቋል። አሁኑኑ ማንም ሳይቀድማችሁ ባላችሁበት በቤታችሁ ሁናችሁ አንቡት። ወላጆችና መምህራኖች ይህን መፅሀፍ ለተማሪዎቻችሁ ተረኩላቸው። መሳጭ እና አስተማሪ ታሪኮችን እንዲሁም እራስን ማያ መጠይቆች ያሉትን መፅሀፍ በእጅዎ ያስገቡ።

መፅሀፉን በቤትዎ ሁነው ለማግኘት 👇
https://ye-buna.com/gebiawkefale?ref=product_detail&product=6ab54221e858c_gebiawkefale


📍ኢየሱስን በፍጹም ፍቅር የሚወደውና በቅን ልቦና የሚከተለው ሰው ቢኖር፣ በፍቅሩም እስከ ፍጻሜው ቢጸና፥ ቸር እግዚአብሔርአስቀድሞ ለዚያች ነፍስ የክብር አክሊልን ያዘጋጅላታል፡፡

አባ መቃርስ

@SewaswMedia


📍"ሌባ ሰብሮ የሚገባው ባዶ ቤት ውስጥ ሳይሆን በሀብት በተሞላ ቤት ውስጥ ነው ።

📍እንዲሁ ጠላት ሰይጣንም አስቀድማ በኃጢአት የፈረሰችን ነፍስ ብዙ አይዋጋትም ፣ ይልቁንም በቅድስና ለመኖር የምትጋደለውን ነፍስ ግን አጥብቆ ይዋጋታል።

📍ስለዚህ ፈተናው የበረታብህ መስሎ ሲታይህ በውስጥህ መንፈሳዊ ሀብት እንዳለ አውቀህ ይበልጥ ንቃ።"


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@SewaswMedia


መስ🀄ል

📍ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።

ገላትያ 6:14

እንኳን አደረሳችሁ

@SewaswMedia


‼️150ው መዝሙረ ዳዊት ጥቅም


‼️እስከ መስከረም 17 ድረስ በ31% ቅናሽ ይህን መጽሐፍ ይግዙ።✅

⚠️መጽሐፉ በውስጡ 150 የዳዊት መዝሙራት ጥቅም የያዘና ለስጋዊም ለመንፈሳዊ ችግራችን መፍትሔ የሚሰጠን ነው።

💰መጽሐፉን ለመግዛት
https://ye-buna.com/zsewasw
በዚህ ሊንክ ገብታችሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።🔗

🔴ይህ የመጨረሻ ቅናሽ ነው ተጠቀሙበት።

⚠️ያስታውሱ⚠️
መጽሐፉ eBook ነው።

©Dn_Sewasw

@SewaswMedia


♻️ሞገሳችንና ክብራችን፥ የመድኃኒታችን ቀንድ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

🔰በእርሱ የምናምንበት የሰላማችን ምልክት' የምንጠጋበት የድኅነታችን ግድግዳ፣ የሕይወት ደንጊያ እና የማዕዘን ራስ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

⚜የተከማቸ ወርቅ እና የተሰወረ ዕንቊ፤ የበዛ ወቄት እና የተትረፈረፈ መክሊት እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::

📍ያልተሠራ ልብስ፣ ያልተፈተለ መጎናጸፊያ፤ ዱቄቱን ያበቃው እርሾ እና አልጫውን ያጣፈጠው ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::

♻️መልካም ቀንበርና ቀላል ሽክም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::
ወደ አባቱ ለመሄድ መንገድ፣ ወደወለደው ለመግባት በር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

📍ማዕበል የማይቀርበው መርከባችን፣ ሌባ የማያገኘው ብል ነቀዝ የማያበላሸው ሣጥናችን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በንጹሐን ሥጋ ውስጥ የሚያፈራ ንጹሕ ዘር እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

📍እግዚአብሔር በተከላት የምስክር ድንኳን ለንጹሐን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

💫ከምሥራቅ የወጣ ብርሃናዊ ኮከብ፣ በሰማይ የሚታይ የእውነት ፀሐይ፣ ንጹሕ የሆነ ሙሽራ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

📍በአብ ዘንድ ልጅ፤ በመንፈስ ቅዱስ ዘንድ መንፈስ፣ በድንግልም ዘንድ ሕፃን' በነቢያት ዘንድ ነቢይ፣ በሐዋርያትም ዘንድ ሐዋርያ፣ በሰማዕታት ዘንድ አክሊል (ዘውድ) የሚሆን መምህር እና የማኅበር አለቃ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ጸሎተ ሰዓታት)

@SewaswMedia


አዲሰ ዘመን📍

💫ከዘመን ዘመን የሚያሸጋግር የዘመናት ሁሉ ባለቤት፣ዘመናት የእርሱ የሆኑ ዘመን የማይቆጠርለት መድኃኔዓለም ክርስቶስ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገረን።

📍መቀደስ የእርሱ ነውና አዲሱን ዘመን ይባርክልን

መልካም አዲስ ዘመን

©Dn_Sewasw

@SewaswMedia


‼️3 ቀናት ብቻ ቀሩት


‼️እስከ መስከረም ፩ ድረስ በ50% ቅናሽ ይህን መጽሐፍ ይግዙ።✅

⚠️መጽሐፉ በውስጡ 150 የዳዊት መዝሙራት ጥቅም የያዘና ለስጋዊም ለመንፈሳዊ ችግራችን መፍትሔ የሚሰጠን ነው።

💰መጽሐፉን ለመግዛት
https://ye-buna.com/zsewasw
በዚህ ሊንክ ገብታችሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።🔗

🔴ይህ የመጨረሻ ቅናሽ ነው ተጠቀሙበት።

⚠️ያስታውሱ⚠️
መጽሐፉ eBook ነው።

©Dn_Sewasw

@SewaswMedia


📍ቅዱስ ሩፋኤል📍

የእኔም ስሜ ሩፋኤል ነው ይህም ደስ የሚያሰኝ ቸር መሐሪ ቅን የዋህ ማለት ነው። እኔም ኃጢአተኞችን በእግዚአብሔር ዘንድ አልከሳቸውም ከኃጢያታቸው በንስሐ እስኪመለሱ ቅንነቴ በእነሱ ላይ እታገሳለሁ እንጂ።

📍እንኳን አደረሳችሁ

@SewaswMedia


📍መዝሙረ ዳዊት📍

የምትፈልጉ ከሆነ በትልቁና በትንሹ በዚህ መንገድ ተሰርቶ ነው የሚደርሳችሁ።

📍የምልከው በፖስታ ስለሆነ ፖስታ የሌለበት ቦታ ከሆናችሁ መላክ አልችልም።🙏

📍ትልቁ አማርኛና ግዕዝ አለው
📍ትንሹ ግዕዝ ብቻ

📍ለማዘዝ በዚህ ይጻፉልኝ @zsewasw

@SewaswMedia


👀የመዝሙረ ዳዊት ጥቅም

‼️እስከ መስከረም ፩ ድረስ በ50% ቅናሽ ይህን መጽሐፍ ይግዙ።✅

⚠️መጽሐፉ በውስጡ 150 የዳዊት መዝሙራት ጥቅም የያዘና ለስጋዊም ለመንፈሳዊ ችግራችን መፍትሔ የሚሰጠን ነው።

💰መጽሐፉን ለመግዛት
https://ye-buna.com/zsewasw
በዚህ ሊንክ ገብታችሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።🔗

🔴ይህ የመጨረሻ ቅናሽ ነው ተጠቀሙበት።

⚠️ያስታውሱ⚠️
መጽሐፉ eBook ነው።

©Dn_Sewasw

@SewaswMedia


🫥 ጸልዩ 🫥

♻️ጸሎት ልባችን የዓመፃ ሥራን ከመመኘት ይገታዋል። እግራችን በኃጢአት ጎዳና እንዳይባዝን፣ አንደበታችን ከሽንገላ ከሐሰት እንዲጠበቅ ያደርጋል::

♻️ጸሎት ጥልቅ የኾነ መንፈሳዊ ማስተዋልን ይሰጠናል:: በዚህም ከክፋት ሥራ እንድንርቅ፣ ተገቢ ያልኾነ ጠባይን እንዳንደግፍ፣ የጠማሞችንና የኃጥአንን መንገድ እንዳናወድስ ይረዳናል።

♻️በዚህ ዓለም ከሚገጥሙን ትንኮሳዎችና በደሎች የተነሣ ለምናጣው ሰላም፥ ጸሎት በየቀኑ አዲስና ልባዊ የኾነ ዕረፍትን መልሶ ይሰጠናል:: የእግዚአብሔር ጸጋ ባይደግፈን ኖሮ፥ በጭንቀትና በሥነ ልቦናዊ ሕመም እንጠቃ ነበርና፡፡

♻️ጸሎት፥ የዕለት ተዕለት አካሔዳችንን እንከንና ጉድለት ገልጦ የሚያሳይ የውስጥ ብርሃን ነው:: ይህም ወደ ጥልቁ ገሃነም እንዳንነዳ ይጠብቀናል።

ጸልዩ በእንተ ሰላምነ ኢትዮጵያ


©Dn_Sewasw

@SewaswMedia


ኢትዮጵያን በወንጌል ብርሃን ያረሳት
ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለሃይማኖት
የእረፍት መታሰቢያ ነው።

እንኳን አደረሳችሁ።

@SewaswMedia


👀የመዝሙረ ዳዊት ጥቅም

🛑 ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም ፩ ድረስ በ50% ቅናሽ ይህን መጽሐፍ ይግዙ ።

🛑መጽሐፉ በውስጡ 150 የዳዊት መዝሙራት ጥቅም የያዘና ለስጋዊም ለመንፈሳዊ ችግራችን መፍትሔ የሚሰጠን ነው።

🌜መጽሐፉን ለመግዛት
https://ye-buna.com/zsewasw

በዚህ ሊንክ ገብታችሁ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።

🔴 ይህ የመጨረሻ ቅናሽ ነው ተጠቀሙበት።

©Dn_Sewasw

@SewaswMedia

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.