👉🏽👉🏽👉🏽 የ #ገና #ጾም (የ #ነቢያት ጾም) #ወቅት በ #ቤተክርስቲያን እንዴት ይገለጻል?
(ክፍል 2)
✍የዘመነ አስተምህሮ ሰንበታት (እሑዶች) ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ስያሜ ጋር ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ልዩነታቸውን ለማነጻጸርና ለመረዳት እንዲያመቸንም በእነዚህ ሰንበታት የሚነገረውን ቃለ እግዚአብሔር ይዘት እንደሚከተለው በአጭሩ እንመለከታለን፦
1. አስተምሕሮ፦ የመጀመሪያው የዘመነ አስተምሕሮ ሳምንት "አስተምሕሮ" ይባላል፣ ይህም ከኅዳር 6 – 12 ያሉትን ሰባት ቀናት ያካትታል፡፡
✍በዕለቱ (እሑድ) የሚቀርበው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር፦
👉"ኢተዘኪሮ አበሳ ዚአነ ኢኀደገነ ፍጹመ ንማስን ….(ኀጢአታችንን አላሰበብንም፤ እንጠፋ ዘንድም ፈጽሞ አልተወንም ….)" የሚለው ሲሆን፣ በተጨማሪም
👉"ፈጽም ለነ ሠናይተከ እንተ እምኀቤነ ….፣ (በአንተ ዘንድ ያለችውን በጎነት ፈጽምልን ….)" የሚለውም እንደ አማራጭ ሊቀርብ ይችላል፡፡
👉ምስባኩ "ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ (የቀደመውን በደላችንን አታስብብን አቤቱ ምሕረትህ በቶሎ ያግኘን እጅግ ተቸግረናልና )" መዝ.78፥8 የሚለው የዳዊት መዝሙር ነው
👉ወንጌሉ ማቴ.6፥5-16 ሲሆን፣ ቅዳሴውም ቅዳሴ እግዚእ ነው፡፡
✍በዚህ ሳምንት እግዚአብሔር አምላካችን ከአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዓመት የመርገምና የጨለማ ዘመን ዓለምን ማውጣቱ፣ ቸርነቱ፣ ርኅራኄውና ትዕግሥቱ እንደዚሁም ምእመናንን ከሞተ ሥጋ ከሞተ ነፍስ ማውጣቱ ይነገርበታል፡፡
2. ቅድስት፦ ከኅዳር 13 – 19 ያሉትን ሰባት ቀናት የሚያካትተው የዘመነ አስተምሕሮ ሁለተኛው ሳምንት "ቅድስት" ይባላል።
✍ቅድስት የተባለበት ምክንያትም ሰንበትን ለቀደሰ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ እንደሚገባ የሚነግርበት ሳምንት መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ዕለት (እሑድ)
👉"ሎቱ ስብሐት ወሎቱ አኰቴት ለዘቀደሳ ለሰንበት …. (ሰንበትን ላከበራት ለእርሱ ክብር ምስጋና ይኹን (ይድረሰው፣ ይገባዋል) ….)" የሚለው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ይቀርባል።
👉በቅዳሴ ጊዜም "ኩሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር በሰማይኒ ወበምድርኒ በባሕርኒ ወበኩሉ ቀላያት፤ (በሰማይና በምድር፣ በባሕርና በጥልቆችም ሁሉ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ)" መዝ.134፥6 የሚለው ምስባክ ይሰበካል
👉ወንጌሉ ዮሐ.5፥16-28 ሲሆን ቅዳሴው ደግሞ አትናቴዎስ ነው፡፡
✍በዚህ ሳምንት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስትነት እና ሰንበትን ስለቀደሰ ስለ እግዚአብሔር ቅድስና ሰፊ ትምህርት ይቀርባል፡፡
✍በአንጻሩ በዓቢይ ጾሙ ቅድስት፦
👉 መዝሙሩ፡- ግነዩ ለእግዚአብሔር"
👉ምስባኩ፡- "እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ (እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ እምነትና በጎነት በፊቱ፣ ቅድስናና የክብር ገናናነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው)"
መዝ.95፥5-6
👉ወንጌሉ፡- ማቴ.6፥16-25 ቅዳሴው ደግሞ ኤጲፋንዮስ ነው፡፡
✍በዚህ ሳምንት የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር ይቅር ባይነትና ለእርሱ ስለ መገዛት፣ ስለ ቅድስና እና ስለ ክብረ ሰንበት የሚያስረዳ ነው፡፡
3. ምኩራብ፦ ሦስተኛው የዘመነ አስተምሕሮ ሳምንት "ምኩራብ" የሚባል ሲሆን ይህም ከኅዳር 20 – 26 ያሉትን ሰባት ቀናት የሚያካትት ሳምንት ነው፡፡
👉በዕለቱ (እሑድ) የሚቀርበው መዝሙር፡- "አምላክ ፍጹም በህላዌሁ ዘሀሎ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ….፤ (ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረው አምላክ (እግዚአብሔር) በህልውናው (አነዋወሩ) ፍጹም ነው ….)" የሚለው ሲሆን፣
👉ምስባኩም፡- "ቅረቡ ኀቤሁ ወያበርህ ለክሙ ወኢይትኀፈር ገጽክሙ ዝንቱ ነዳይ ጸርሐ እግዚአብሔር ሰምዖ (ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማልፊታችሁም አያፍርም ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔርም ሰማው)" መዝ.33፥5-6 የሚል ነው።
👉ወንጌሉም ማቴ. 8፥28 እስከ መጨረሻው ድረስ ነው፡፡ ቅዳሴው ደግሞ እግዚእ፡፡
✍በዚህ ሳምንት ጌታችን፣ አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራበ አይሁድ ሕዝቡን እየሰበሰበ ማስተማሩ፣ ባሕርና ነፋሳትን መገሠፁ፣ አጋንንትን ከሰዎች ማውጣቱ ይነገራል፡፡
✍በዓቢይ ጾሙ ምኵራብ መዝሙሩ፡- "ቦአ ኢየሱስ ምኩራቦሙ ለአይሁድ"
👉ምስባኩ፡- "እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀፃዕክዋ በጾም ለነፍስየ (የቤትህ ቅናት በልቶኛልና፣ የሚሰድቡህ ስድብም በላዬ ወድቋልና ሰውነቴን በጾም አደከምኋት)"
መዝ.68፥9-10
👉ወንጌሉ፡- ዮሐ.2፥12 እስከ ፍጻሜው ሲሆን ቅዳሴው ግን ተመሳሳይ (ቅዳሴ እግዚእ) ነው፡፡
✍በሳምንቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራበ አይሁድ ማስተማሩንና በቤተ መቅደሱ ዓለማዊ ሸቀጥ ይለውጡ የነበሩ ገበያተኞችን ማስወጣቱን የሚመለከት ትምህርት ይቀርባል፡፡
ይቀጥላል (ክፍል 3)
👇
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወለዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!
@Sewsinor @Sewsinor