በጭንቀት ላይ ለሰነበታችሁ ዘመድ ወዳጆቸ እና የትግል አጋሮቸ በሙሉ።
ለገጠመኝ የጤና ችግር ከአንድ ቀን በፊት የተካሄደልኝ የቀዶ ጥገና ህክምና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ አሁን ላይ ጤናየ በጥሩ ሁኔታ ስለሚገኝም ከሆስፒታል ወጥቸ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ። ስለ ደህንነቴ ተጨንቃችሁ በፀሎትና በሀሳብ ስታግዙኝ ለሰነበታችሁ ወዳጅ ዘመዶቸ በሙሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። አሁን ረዥም ጊዜ የፈጀው የህክምናየ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ስለሆነም ወደ አገሬ ተመልሸ ለመሄድ የነበረኝ ከፍተኛ ፍላጐትና ጉጉት ዕውን ሊሆን በመቃረቡ ደስ ብሎኛል።
ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው
ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም
@Showapress