ይነበብ😁🫴
ሁለት ባለ ትዳሮች ነበሩ እና ከለታት አንድ ቀን አባወራው ምሳ ለመብላት ወደ ቤት በመምጣት ሚስቱ ምሳ እንድታቀርብለት ይጠይቃል ሚስትየውም እንዲህ በማለት ትመልሳለች "ጌታው ምሳ የለም እኮ" በማለት መልስ ትሰጣለች ከዛም እሱ "እንዴት ነው ምሳ የለም የምትይኝ" ብሎ በንዴት እና በቁጣ ይናገራት ጀመር ከዛም ስላልሰራሁኝ ነው የሚል ምክንያት በማቅረብ በፍርሃቻ መለሰች ባልም እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በጩኸት ወደሷ መጠጋት ሲጀምር እሷም እሮጣ ለማምለጥ በር ከፍታ ከቤቱ ወጣች ባልም እየተከተለ ያባርራት ጀመር ከዛም ትንሽ ከተሯሯጡ ቡሃላ በአከባቢያቸው በሚገኝ አንድ ወንዝ አጠገብ ቆማ "ከዚህ ቡሃላ የምትጠጋኝ ከሆነ እዚህ ወንዝ ውስጥ ነው ምገባው" ብላ ስትናገር እሱም "ወንድ ነሽ እሰራልሻለው" ብሎ ሲጠጋት ከያዘኝ አይለቀኝም ብላ ወንዙ ውስጥ ዘላ ገባች እሱም በንዴት "ያመለጥሽኝ አይምሰልሽ" ብሎ ድንጋይ በማንሳት በገባችበት አቅጣጫ ወደ ውስጥ ሲወረውር የተወረወረው ድንጋይ ጭንቅላቷን በማግኘቱ ደሟ ፍልቅ ብሎ ወደላይ ሲወጣ ባል ተብዬው "ለራስሽ በበርበሬ እየበላሽ ነው" ብሎ ዘሎ ገባና ሰምጦ ቀረ ይባላል።
ግም ለግም ተያይዘህ አዝግም 🗿
✍ @Infinity_0A 🩹🖤