ብዙዎቻችን ነፃ የሆንን ይመስለናል እንጂ ታስረናል
~
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እስር ቤት ውስጥ ሳሉ እንዲህ ይሉ ነበር፦
المحبوس، من حُبِسَ قلبه عن ربه.
"እስረኛ ማለት ልቡ ከጌታው የታሰረ ነው።" [አልዋቢሉ ሶዪብ፡ 48]
ወደ ጌታው እንዳይቀርብ፣ ትእዛዛቱን እንዳይፈፅም፣ ከክልከላዎቹ እንዳይርቅ በሸይጧን፣ በነፍሲያ፣ በክፉ ጓደኛ የተፈተነና የተሸነፈ ሰው እስረኛ እንጂ ነፃ አይደለም። አዎ ዛሬ ብዙዎቻችን በስልካችን ታስረናል። በሸይጧን ታስረናል። በነፍሲያ ታስረናል። በወዳጅ ታስረናል። በቲቪ ታስረናል። በገንዘባችን ታስረናል። በዱንያዊ ቁሶች ወደ አላህ መቃረብን ከመነፈግ በላይ እስራት አለ? ቁርኣን መቼ ነው የቀራነው? ዚክርስ ትዝ ይለናል? ምላስን መቆጣጠርስ አለ? ሶላታችን ጣእም አለው? ለተቸገረ እጃችን ይፈታል? ገንዘባችን ለአልባሌ ጉዳይ አይወጣም? ለዲናችን አስተዋፅዖ አለን? እኮ እስከመቼ?! አላህ ልብ ይስጠን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor