ቻይና 83 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የወርቅ ክምችት አገኘች!!
ቻይና ወርቅ በማምረት በዓለማችን ቁጥር አንድ ሀገር ሆናለች
ቻይና 83 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የወርቅ ክምችት አገኘች፡፡
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና አዲስ የወርቅ ማዕድን በሁናን ግዛት አግኝታለች፡፡
እንደ ሽንዋ ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ የሁና ጂኦሎጂ ማዕከል ባደረገው የማዕድን ፍለጋ ከ300 በላይ ቶን መጠን ያለው ወርቅ አግኝቷል፡፡
ማዕከሉ ባካሄዳቸው 40 የወርቅ ማእድን ፍለጋ ጣቢያዎች ውስጥ ያደረገው ጥረት ስኬታማ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡
አዲስ የተገኘው ወርቅ አሁን ባለው ዋጋ መሰረት ሲሰላ 600 ቢሊዮን ዩዋን ወይም 83 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ነውም ተብሏል፡፡
በ2023 ላይ ባለው የዓለም ወርቅ ግብይት መረጃ መሰረት ቻይና ቁጥር አንድ የዓለማችን ወርቅ አምራች ሀገር ነበረች፡፡
በተያዘው ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 741 ሜትሪክ ቶን ወርቅ የተጠቀመች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 268 ሜትሪክ ቶን ወርቅ በሀገሯ የተመረተ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የዓለማችን 10 በመቶ ወርቅ አምራች የሆነችው ቻይና በዓለም ገበያ ውስጥ ወርቅ ሸማች ከሆኑ ቀዳሚ ሀገራት መካከልም ዋነኛዋ ናት፡፡
https://t.me/Tamrinmedia