መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስር ተፈረደባት፡፡
“ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት መስከረም አበራ ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባት።
የቅጣት ውሳኔው በፍርድ ቤት ሲገለጽ፤ መስከረም አበራ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በመስከረም አበራ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች ችሎት ነው።
ፍርድ ቤቱ መስከረምን ጥፋተኛ ያላት “በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ክስ ነው።
መስከረም ጥፋተኛ የተባለችው በባለቤትነት በምታስተዳደረው ‘ኢትዮ ንቃት’ የዩቱዩብ ገጽ ላይ በተላለፉ ሁለት ፕሮግራሞች ምክንያት ነው።
ከተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮዎች በኋላ ዛሬ ሰኞ ኅዳር 16/2017 ዓ.ም የዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉን ጠበቃ ሄኖክ ገልጸዋል።
ጠበቃ ሄኖክ አክለውም “ይህ ውሳኔ የተላለፈው መስከረም አበራ ቅሬታ አለኝ ብላ ችሎት ባልቀረበችበት ሁኔታ ነው” ብለዋል።
አቶ ሄኖክ “ከዚህ ቀደም ያቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮቹ በአግባቡ ያልታዩልኝ ስለሆነ ከዚህ ችሎት ፍትህ አልጠብቅም፤ እናንተ ተገቢ ነው የምትሉትን ቅጣት ወስኑ፤ ከዚህ በኋላ በችሎት አልገኝም ብላ ገልጻለች ይሄንንም ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አሳውቃለች” ሲሉ የደንበኛቸውን ቅሬታ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
https://t.me/Tamrinmedia