ስማቸውን ወደ “ትራምፕ” የቀየሩት ፖለቲከኛ
ቤን ዳውኪንስ የተባሉ የአውስትራሊያ ፖለቲከኛ ስማቸውን ወደ ኦሲ ትራምፕ ቀይረዋል።
ፖለቲካኛው ስማቸውን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ስም መሰየሙ ትኩረት ለማግኘት እና የትራምፕ የፖለቲካ አቋም ደጋፊ መሆናቸውን ለመግለጽ ነው ብለዋል።
በአዲሱ ስማቸው ኦሲ ትራምፕ የተባሉት ግለሰብ የምዕራብ አውስትራሊያ የላይኛው ምክር ቤት አባል ሲሆኑ የዶናልድ ትራምፕ ጸረ ግራ ዘመም ፖለቲካ አቋም አድናቂ እንደሆኑ ተናግረዋል።
ሰውዬው እንደ ዶናልድ ትራምፕ ሁሉ ነዳጅ እና ጋዝ በብዛት ማውጣትን የሚደግፉ ሲሆን “ዶናልድን ቢሮው ደውላችሁ አግኙት” ሲሉ “ክቡር ኦሲ ትራምፕ ኤምኤልሲ” በሚል በአዲሱ ስም በከፈቱት የኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።
ፖለቲከኛው ስማቸውን የቀየሩበት ምክንያት ለአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ያለውን ተቃውሞ ለማሳየት ነውም ተብሏል።
ይህንንም ተከትሎ የምዕራብ አውስትራሊያ ገዢው ፓርቲ መሪ የሆኑት ሮጀር ኩክ የፖለቲከኛው ተግባር ትኩረት ፍለጋ የተደረገ አትርሱኝ ባይነት ነው ሲሉ ተችተውታል።
የምዕራብ አውስታራሊያ ግዛት በቀጣዩ ወር ምርጫ እንደምታካሂድም ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
https://t.me/Tamrinmedia