የዲጂታል ስክሪን ማስታወቂያ ባለቤቶች ከነገ ጀምሮ የብልፅግና ፓርቲ ማስታወቂያን በግዴታ እንዲያሳዩ ሊደረጉ መሆኑ ታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የዲጂታል ስክሪን ማስታወቂያ ባለቤቶች እና ህንፃዎቻቸው ላይ የማስታወቂያ ስክሪን የገጠሙ ባለሀብቶች ከነገ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ መልእክት የሆኑ ምስሎችን እና ጽሁፎችን በአስገዳጅነት እንዲያሰራጩ ጥብቅ ትዕዛዝ እንደተላለፈላቸው ታውቋል።
በራሳቸው ወጪ አውጥተው የሰሩትን የዲጂታል ስክሪን ለፖለቲካ ፓርቲ መልዕክት ማስተላለፊያ መደረጉ በህዝብ ዘንድ ለአንድ ወገን ያደሉ ወይም የፓርቲ አባል እንደሆኑ እንዳይወሰድባቸው የሰጉት ግለሰቦቹ አማራጭ እንዳጡ እና አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ተናግረዋል።
የብልጽግና ሹሞች ቁጣ በተቀላቀለበት መልዕክት በአስገዳጅነት ማስታወቂያውን ከነገ ጀምሮ ለማሰራጨት እንዳስገደዷቸው ጨምረው ተናግረዋል።
"ከሳምንት በፊት ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መሪዎች ሲመጡ 'እንኳን ደህና መጣችሁ' የሚልና ስለ አፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተመሳሳይ ትዕዛዝ ተላልፎ ያስተላለፍነው የፖለቲካ ይዘት የሌለው በመሆኑ ነበር" የሚሉት የማስታወቂያ ድርጅቶቹ "አሁን የታዘዝነው የፖለቲካ ፓርቲ መልእክት ገበያው በተዳከመበት መሀል ከህዝቡ ጋር እንዳያቃቅረን ስጋት አለን" ብለዋል።
በሌላ በኩል በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ወቅት በርካታ የመኪና ኪራይ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎቻቸውን በነፃ ለስብሰባው አገልግሎት እንዲሰጡ ተገደው እንደነበር ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
"ቢዝነስ በተዳከመበት በዚህ ወቅትም ይሁን ድሮ በአመት አንዴ ጥሩ ስራ የምንሰራው እንደ አፍሪካ ህብረት ያሉ ስብሰባዎች ሲመጡ ነበር" የሚሉት የመኪና አከራዮቹ አሁን ግን እሱንም በግዴታ እንደተነጠቁ እና መኪናዎቻቸው የተመለሱላቸው ስብሰባው ካለቀ በኋላ መሆኑን አስረድተዋል።
via# መሠረትሚዲያ !
https://t.me/Tamrinmedia