የሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ጉዳይ
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በትምህርት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጻም ላይ በሕ/ተ/ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ፣ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ አንዲሁም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሂጃብ ጋር በተያያዘ ችግሮች መከሰታቸውን ያነሱት አባላቱ፤ በጉዳዩ ላይ መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ምን አሉ?
"የኢትዮጵያ ሕግና ደንቦች፥ በዚህ ጉዳይ ላይ የወጡት ደንቦች ሂጃብ ለብሶ ትምህርት መማርን የሚከለክል የኢትዮጵያ ሕግ የለም፡፡ በሂጃብ ምክንያት፥ ማንም ሂጃብ ለበሰ ተብሎ ትምህርት ቤት መከልከል አይችልም፡፡"
"ኒቃብ ግን የተለየ ነው፡፡ ህጻናቶች፣ ልጆች ባሉበት ትምህርት ቤት የአንድ ሰው ፊት ተሸፍኖ በሚገባ ጊዜ የsecurity risk (የደኅንነት ስጋት) አለው፡፡"
"ከመጅሊስ ሰዎች ጋር ተሰብስበን፣ ተወያይተን፣ ተማምነናል፡፡ በኒቃብ ላይ ሕግ ማስቀየር ካለባችሁ እዚሁ ፓርላማ በማምጣት ማስቀር ነው እንጂ፣ በየጊዜው Issue እየሆነ የግጭት ምክንያት መሆን የለበትም፡፡" "አሁን ያለው ሕግ ግን ሂጃብ በምንም ምክንያት የትም ቦታ መከልከል የለበትም፡፡"
@tikvahuniversity