የ'ግዜርን ነፍስ ሴጣን ልብን አድሏታል
ላይዋ ታቦት ታቿ ጣዖት ተዋርሷታል
ልጅ እያለች ስትድህ ገና ያወቀችዉ
አፏን ገና ስትፈታ በቀል የሚል ቃላቶች ነዉ ያወጣችዉ
በ።ቀ።ል
እልል...............
በእናቷ እቅፍ ገብታ በአንቀልባ ዉስጥ እያለች
ስለአባቷ መርዛማነት በጡጦ አርጋ ጠብተዋለች
ጥ።ላ።ቻ
እልል..................
እሹሩሩ አታዉቅ እናት
አባቷን ነዉ ምጠራላት
ህ።መ።ም
እልል...................
እልል
ዛሬ
ነፍስ አወቀች
ፍቅርን ሻተች
ምን ታደርገዉ ሴጣን ልብን ተዋርሳለች
የአዳም ፍጥረት ትጠላለች።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizitawolde_poems@Tizitawolde_poems