የረመዷንን ሌቦች ተጠንቀቁ!|•|
አንደኛው ሌባ፦ቴሌቭዥን ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ ከፍታ አጋዥ ካልሆኑ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ነው። በተለይ ደሞ የረመዷን ሙሰልሰላቶችን እና አዘናጊ ድራማዎችን ተጠንቀቁ፤ የረመዷን ዉድ ጊዜያት ለዉድ ነገሮች መዋል አለባቸው፡፡
ሁለተኛው ሌባ፦
ስልክ ብዙ ማውራት ለብዙ ስህተት ያጋልጣል፣ ትርፍ ንግግር ወደ ሀሜትና ያልታሰቡ ወንጀሎች ይመራል፤ለተሻለ ምንዳ በረመዷን በንግግር ጭምር ቁጥብ መሆን ያስፈልጋል፡፡
ሦስተኛ ሌባ፦ወጣ ገባ ማብዛት/መዞር፡፡ በረመዷን ከመስጊድ እና ከቤት የበለጠ ማረፊያ የለም፡፡ ወደ ከተማም ይሁን ወደ ገበያ ያለበቂ ምክንያት ወጣገባ ማብዛት ዐይንንም ሆነ ጆሮን ያልሆነ ነገር ይጥላል፡፡ፆምን ይሰርቃል፤ ምንዳዉንም ያጓድላል፡፡
አራተኛ ሌባ፦ማምሸት፡ ያለምክንያት ማምሸት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለዉም፡፡ የረመዷን ምሽቶች ምርጥና ዉብ ናቸው፡፡ በቁርኣን፣ ዚክር እና በተለያዩ ዒባዳዎች መዋብ አለባቸው፡፡
አምስተኛ ሌባ፦ኩሽና:በተለይ ለሴቶች፡፡ሙሉዉን ረመዷን ማዕድ ቤት የሚያሳልፉ ቁርኣንን፣ ሶላትና ዚክርን የረሱ ብዙ ናቸው፡፡ ረመዷን የፆም ወር ነው፡፡ ትልቁን ትኩረት ለሆድ መስጠት ዓላማዉን መሳት ነው የሚሆነው፡፡
ስድስተኛው ሌባ፦ሶሻል ሚዲያ፡፡ ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ችግር ሆኗል፡፡በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ነው፡፡ በዚህም ከዚክር፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ እንዳንጠቀም ሆነናል፡፡ እንጠንቀቅ፡፡
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan