የሀገር ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት ማስከበር የሚቻለው ሁለንተናዊ ብሔራዊ አቅምን በመገንባት ነው- ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
ጥቅምት 23/2017 (አዲስ ዋልታ) የሀገር ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት ማስከበር የሚቻለው ሁለንተናዊ ብሔራዊ አቅምን በመገንባት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ መርሐ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችበዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ሚኒስትሮችና እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ም/ጠ/ሚ ተመስገን በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት ማስጠበቅ ላይ እንዲያውሉት ማሳሰባቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል