ኢትዮ ቴሌኮም ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህትመት መስጠት ጀመረ
ኅዳር 11/2017 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ደንበኞች የህትመት ጥያቄ በቴሌ ብር ሱፐርአፕ በኦንላይን ክፍያ በመፈጸም መታወቂያ ካርዳቸውን መረከብ የሚችሉበትን አሰራር በይፋ አስጀምሯል፡፡
አገልግሎቱን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 63 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የካርድ መቀበያ ቦታዎች ካርዳቸውን እንደምርጫቸው በሚቀርባቸው ቦታ መረከብ ያስችላል።
አገልግሎት ደህንነቱ አስተማማኝ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው ካርድ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ደንበኞች በድረገጽ https://teleprint.fayda.et/ በመግባት የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (FAN) በማስገባት በአጭር ጽሑፍ የሚላከውን የማረጋገጫ መለያ ኮድ በማስገባት የአገልግሎት ፍጥነት፣ ካርድ የመረከቢያ ቀን እና ቦታ እንደፍላጎታቸው መምረጥ ያስችላል።
የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ደንበኞች በተለያየ የህትመት ማድረሻ ፍጥነት አማራጮች (delivery time) ማለትም ለመደበኛ በ7 የሥራ ቀናት 345፣ ለፕሪሚየም በ2 የስራ ቀናት 600 ብር እና ለኤክስፕረስ አስቸኳይ 800 ብር በቀላሉ በቴሌ ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ለአዲስ ዋልታ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
የመታወቂያ ህትመቱ አገልግሎቱ ዘመናችን በደረሰበት የመጨረሻ የህትመት ቴክኖሎጂ በላቀ የህትመት ጥራት ደረጃ የሚከናወን ሲሆን በቀላሉ የማይጫጫር፣ ቀለሙ የማይለቅ እና ሳይበላሽ እስከ 10 አመታት የሚደርስ የአገልግሎት እድሜ ያለው ነው ተብሏል፡፡