ፓትሪስ ቪዬራ የጀኖዋ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
ኅዳር 11/2017 (አዲስ ዋልታ) የቀድሞው የአርሰናልና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመሃል ሜዳ ተጫዋች ፓትሪስ ቪዬራ የጀኖዋ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።
ቪዬራ ከፈረንሳይ ጋር የዓለም ዋንጫን ያነሳ ሲሆን ከአርሰናል ጋር ደግሞ ሶስት የፕሪምየር ሊግ እና አራት የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን አንስቷል።
በኒው ዮርክ ሲቲ እግር ኳስ ቡድን የአሰልጣኝነት ስራውን የጀመረው ቪዬራ ክሪስታል ፓላስን፣ ኒስን እና ስትራስበርግን ያሰለጠነ ሲሆን አሁን ደግሞ አልቤርቶ ጅላርዲኖን በመተካት በሊጉ 17ኛ ደረጃ ላይ ያለውን ጀኖዋን ለማሰልጠን መስማማቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቪዬራ በማንችስተር ሲቲና በኢንተር ሚላን አብሮት ከጫወተው ማሪዮ ባላቶሊ ጋር ዳግም ይገናኛሉ።
ጣሊያናዊው አጥቂ ማሪዮ ባላቶሊ ባለፈው ወር ለጀኖዋ ለመጫወት መፈረሙ ይታወሳል።