አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ዝግጅትን ለመመልከት አርባምንጭ ከተማ ገቡ
ኅዳር 12/2017 (አዲስ ዋልታ) በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ቡድን 19ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራን ለመመልከት አርባምንጭ ከተማ ገባ።
አፈ ጉባኤው አርባምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የጋሞ አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ቡድኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት እንግዶችን ለመቀበልና በዓሉን ለማክበር እያደረገ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ እንደሚጠበቅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።
19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል "ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ይከበራል።