አጋእዝተ ዓለም
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
6፥164 በላቸው «እርሱ አሏህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا
"እግዚእ" ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የእግዚእ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አጋእዝት" ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው፦
ራእይ 22፥9 ወይቤለኒ፦ “ኢትስግድ ሊተ ዑቅ ዮጊ ገብረ አጋእዝቲከ አነ ወዘአኀዊከ ነቢያት ወዘእለ የዐቅቡ ቃለ ዝንቱ መጽሐፍ። ወአንተሰ ለእግዚአብሔር ስግድ።
በግዕዙ ባይብል "አጋእዝቲከ" የሚል ቃል ያለ ሲሆን "ጌቶችህ" ማለት ነው፥ በግዕዙ ባይብል ላይ መልአኩ ለዮሐንስ "ጌቶችህ" ሲለው በግሪኩ፣ በእንግሊዝኛው እና በዐማርኛው "ጌቶችህ"Your Lods" የሚለው ቃል ይቅርና "ጌታህ"Your Lod" የሚል ቃል የለም። አንድምታው ደግሞ እንደዚህ ይላል፦
ራእይ 22፥9 አንድምታ፦ "ገብረ አጋእዝቲከ አነ"
"የጌቶችህ የሥላሴ ተገዥ ነኝና" "የሐዋርያት ጌቶች የሆኑ የሥላሴ ተገዥ ነኝና"
እዚህ ላይ "አጋእዝት" የተባሉት "ሥላሴ" መሆናቸውን ለማሳየት ዳክረዋል። ለመሆኑ በኦርቶዶክሳዊ ሥላሴ ትምህርት ጽንፈ ዓለምን የሚገዙ ሦስት ጌቶች እንደሆኑ ያውቃሉን? "አጋእዝተ ዓለም" ማለት "የዓለም ጌቶች" ማለት ነው፥ ሐምሌ 7 ቀን አብርሃም ቤት የገቡት ሦስት ሰዎች "የአብርሃሙ ሥላሴ" ተብለው ይታመናሉ፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘእሑድ ምዕራፍ 8 ቁጥር 24
"በሦስተኛው ቀን "አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ" የአብርሃምን የልቡን ቆራጥነት እና የሰይጣንን ተንኮል ተመልክተው ወደ አብርሃም ቤት ሄዱ"።
"አጋእዝተ ዓለም" የሚለው ይሰመርበት! እውን ዓለም የሚገዛው ጌታ አንድ ነው ወይስ ሦስት? በእርግጥ በኦርቶዶክሳዊ ሥላሴ ትምህርት አብርሃም ቤት የገቡት ሥላሴ ሦስት ጌቶች ናቸው፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 11 ቁጥር 69 “በአንቺ "ሦስቱ ጌቶች" የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ”
"ሦስቱ ጌቶች" የሚለው ይሰመርበት! አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእንዚራ ስብሐት መድብሉ የአብርሃም ድንኳን የማርያም ምሳሌ በማድረግ አስቀምጧል። ታዲያ "ሥላሴ "አንድ ጌታ" ናቸው" ብላችሁ ሕዝቡን ታጃጅሉት ይሆን? በእርግጥም ሥላሴ ሦስት ልዑላን ገዢዎች፥ ሦስት ጌቶች ናቸው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22-23
“ሦስት ልዑላን ገዢዎች፥ "ሦስት ጌቶች" ናቸው”።
ዓለምን የሚገዙ ሥላሴ ልዑላን ገዢዎች "ሦስት ጌቶች" መሆናቸው የሚያጅብ ነው፦
ገድለ እስጢፋኖስ ዘወርኃ መጋቢት 6፥2
"ያለ አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ቅጠል እንኳን ከግንዱ ተለይቶ አይረግፍምና"።
በኦርቶዶክሳዊ ሥላሴ ትምህርት ስንት እግዚአብሔር አለ? አብርሃም ቤት የገቡት አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ሦስት እግዚአብሔሮች ናቸው፥ እነዚህም ፦
፨ እግዚአብሔር አብ አንዱ እግዚአብሔር
፨ እግዚአብሔር አብ ሁለተኛው እግዚአብሔር
፨ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሦስተኛው እግዚአብሔር ናቸው።
ሐምሌ 7 ለሚከበረው የሥላሴ ዓመታዊ በዓለ ዋዜማ ሐምሌ 6 ላይ እንዲህ የሚል ዜማ አለ፦
1. "ነአምን ወናመልክ በአሐዱ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ"
ትርጉም፦ "ከዓለም በፊት በነበረው በአንዱ እግዚአብሔር እናምናለን እናመልካለን"
2. "ወነአምን በካልኡ እግዚአብሔር ዘበምልክናሁ ለአብ ይመስሎ"
ትርጉም፦ "በአምላክነቱ አብን በሚመስለው በሁለተኛው እግዚአብሔር እናምናለን።
3. "ወነአምን በሣልሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘይመልዕ ኲሎ"
ትርጉም፦ "ሁሉን በሚመላ መንፈስ ቅዱስ በሦስተኛው እግዚአብሔር እናምናለን"
"አንድ እግዚአብሔር" "አንድ ጌታ" ብላችሁ ሕዝቡን ትሸውዱት ይሆን? በእርግጥ ነቢያት እና ሐዋርያት "አንድ እግዚአብሔር" "አንድ ጌታ" ብለው እንጂ "ሦስት ጌቶች" "ሁሉተኛው እግዚአብሔር" "ሦስተኛው እግዚአብሔር" ብለው አላስተማሩም፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ ‘እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው።
ሕዝቤ ሆይ! ነቢያትም ሐዋርያትም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት "እናምልክ" ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፦
ዘዳግም 13፥7 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ፡ ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው።
ሥላሴ መድብለ አጋእዝት ነው። አምላካችን አሏህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአሏህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? እረ በፍጹም፦

ሥሉሳውያን ክርስቲያኖች ሆይ! ከአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አምልኮ ነጻ ወጥታችሁ በአንድነቱ ሁለትነት ሦስትነት የሌለበትን አንዱን ጌታ አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም