“ነቅተሽ፣ በገናዬ፣ የማርያምን ድንግልን ለማመስገን በሽቦዎችሽ ላይ ቃኝ። ድምጽሽን ከፍ አድርገሽ፣ ይህች ድንግል፣ የዳዊት ልጅ፣ ለዓለም ሕይወትን ያመጣችው እጅግ ድንቅ ትውልድ ዘምሪ… በፍቅር የሚደነቅ በፍርሃት ይመለከታታል፤ የማወቅ ጉጉት ያለው ፈላጊ በኀፍረት ይዋጣል፣ ጆሮውም ይደፈናል፣ ድንግልናዋ ሳይጣስ የወለደችውን እናት ለመመርመር እንዳይደፍር… በማርያም ማኅፀን ውስጥ ሕፃን ሆነ። ከዘላለም ከአብ ጋር እኩል የሆነው እርሱ ነው። ከራሱ ግርማ ሞገስ አካልን ሰጠን፣ የራሳችንንም ድካም አገኘ። በውስጣችን ሕይወትን በማስገባት ዳግመኛ እንዳንሞት ከእኛ ጋር ሞተ… ማርያም ከአብ የበረከት ዝናብ የወረደባት ገነት ናት። ከዚያ ዝናብ እራሷ የአዳምን ፊት ረጨችው። በዚህም ከሞት ተነሳ፣ በሲኦል በጠላቶቹ የተቀበረው ከመቃብር ተነሳ… እነሆ፣ ድንግል እናት ሆነች፣ ድንግልናዋን ሳይሰበር ጠበቀች… የእግዚአብሔር እናትና በተመሳሳይ ጊዜ አገልጋይ፣ የጥበቡም ሥራ ሆነች… በኤደን ሔዋን ዕዳ ውስጥ ገባች፣ ዘሯም በትውልዳቸው ለሞት የተፈረደበት ዕዳ በትልልቅ ፊደላት ተጻፈ። ክፉ ጸሐፊ የሆነው እባቡ ጻፈው፣ ፈርሞ በሽንገላው ማኅተም አጸደቀው… ሔዋን ለኃጢአት ዕዳ ነበረባት። ገር ግን ዕዳው ለማርያም ቀርቶ ነበር፣ ሴት ልጅ የእናቷን ዕዳ እንድትከፍል፣ በእናቷ እንባ ለትውልድ ሁሉ እንደ ርስት የተላለፈውን የሞት ጽሑፍ እንድትሽር… ማርያም ንጽሕት ድንግል ስለነበረች – ምድር ገና ከመታረስ፣ በኤደን በረከት ምድር አስቀድሞ እንደተመሰለች – ከደረቷ የሕይወት ዛፍ በቅላለች፤ ጣዕሙም… ለነፍሳት ሕይወትን ይሰጣል።…” ቅዱስ ኤፍሬም Hymns on the Blessed Mary, 18