የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የአሜሪካው ተራድኦ ተቋም (USAID) እርዳታ ማቆሙን ተከትሎ የሚሽነሪ ተቋማት ክፉኛ ተጎድተዋል። በኢትዮጵያ ፕሮጀክታቸውን ካቋረጠባቸው ተቋማት መካከል ከፊሎቹ የሚሽነሪ ተቋማት ናቸው። ተቋማቱ እነዚህን ስራዎች የሚሰሩት ከኛው ሀገር ቸርቾች ጋር በመተባበር በመሆኑ የነሱ ድጋፍ መቆም ለቸርቾቹ ያልታሰበ ዱብእዳ ሁኗል። ለአብነት አይነ ስውራን ላይ እሰራለሁ የሚለው "Christian Blind Mission" የሚደርሰው ድጋፍ መቋረጡን ገልጾ ድጋፉን በሌላ መንገድ መተካት የማይቻል ከሆነ ስራዎቹ አደጋ ውስጥ እንዳሉ ገልጿል።

ከሰሞኑ ወደ ሀገሪቱ የመጣውና በአብዮት አደባባይ ለሁለት ቀን ሰበካውን ያቀረበው የትራንፕ የቅርብ ሰው ፍራንክሊን ግርሀም ይህንን ጭንቀት ከፈታ በሚል በካውንስሉ በኩል ተስፋ ተጥሎበታል። ብዙዎቹ ፈንድ የሚደረጉ ቸርቾቹ ካለቅጥ ገንዘብ ከመልመዳቸው ጋር የሚሽነሪ ስራውን በጥቂት የኪስ ገንዘብ ለመስራት የሚቸገሩ መሆኑ ግልጽ ነው። ተስፋ ያደረጉት ሰው ተስፋ ይሆናቸው ይሆን? የሚለውን የምናየው ይሆናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe


የዛሬውን የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ ቀድመው ያደረሱን ኢስላማዊ ሚዲያዎች ነበሩ። የሚዲያውን ሙሉ ይዘት ከማቅረብ ጀምሮ ዜና ፍሬሚንጉን አስቀድመው የለቀቁት የኛ ሚዲያዎች ናቸው። በግሌ ስለጉዳዩ መረጃውን ቀድሜ ያገኘሁት ከሀሩን ሚዲያ ከዚያም ከሚንበር ቲቪ ነበር። አከታትለው መረጃውን በፍጥነት ስለለቀቁት ለወትሮው እያጣመሙ መረጃን በራሳቸው መቃን/Framing ሲቃኙን የነበሩ ሌሎች ሚዲያዎችን ማብሸቁ አልቀረም። መረጃው በስርኣቱ ከደረሰን በኃላ ሆነና የተለመደውን የማጣመም ስራቸውን ከረፈደ ቢሞክሩም ልፋታቸው ቆረፈደ።

ለዘመናት በገነቡት መዋቅራዊ ሰንሰለት ሳቢያ መሠል ስስ ተቋማትን በስራቸው አድርገው ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት ስንገደል "ገደሉ" እያሉን ስንበደል "በደሉ" እያሉ በለቅሷችን ሲዘባበቱና ህመማችንን ሲደብቁ ከርመዋል። በዚህ ሰአት ይህንን ሁሉ ሴራቸውን የነቃና የቀደሙ የኛ አካላት ስናይ "እንኳንም ሚዲያ ኖረን!" ያስብላል።

በግሌ በዜናና ወቅታዊ ስራዎች በኩል ሀሩን ሚዲያ ከአመታት ጀምሮ ለሙስሊሙ በሚሰራው ስራ ሁሉ ከጎን ለመሆን አመንትቼ አላውቅም። ከዚህ በኃላ ደግሞ በየወሩ በሚደረግ መዋጮ ላይ አባል በመሆንም በአላህ ﷻ ፍቃድ የትግላቸው አንዱ አካል እሆናለሁ። የሚዲያውን አመራሮች ጠይቄ የተቀበልኩትን የአባልነት ቅጽ ኮሜንት ላይ አስቀምጣለሁ። የሚዲያን ጉልበት በተለይም የራስ ሚዲያን ማጠናከር ያለውን ትልቅ ኃይል የተረዳ ሁሉ በአቅሙ አባል እንዲሆን ወንድማዊ ጥሪየንም አቀርባለሁ።

https://bit.ly/41X7cmD


ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ከብሮድካስት ባለስልጣን ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ህጋዊ ሚዲያ ነው። ይህ ሚዲያ ከተራ ዩቲዩበር እንኳን የማይጠበቅ የበሬ ወለደ ትርክት ዩቲዩቡ ላይ ለጥፏል። ከሰሞኑ በነበሩ ጉዳዮች ቤተ ክርስቲያን ላይ ፍለጠው ቁረጠው ያለ ግለሰብም የለም። የብሮድካስት ባለስልጣን በዚህ አይነት ግጭት ቀስቃሽ ተግባር ላይ እርምጃ እንደሚወስድ እጠብቃለሁ። ዋናው ጉዳይ ግን ነውረኛ ተግባር የፈጸመውን ልጅ ለመከላከል የሚሄዱበት ርቀት ምክንያቱ ምንድን ነው? የሚለው ነው። የተወሰነውን ልንገራችሁ፦

ሚዲያውን ከመመስረት ጀምሮ በበላይ ጠባቂነት እየመሩ የሚገኙት ከሲኖዶሱ ሊቀጳጳሳት መካከል የሆኑት አቡነ ሄኖክ ናቸው። አቡነ ሄኖክ ደግሞ የምዕራብ አርሲ ሀገር ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩ ሰው ናቸው። ታዲያ ይህ ነውረኛ ግለሰብ (እፎይ) ከየት መጣ ብለው ከጠየቁ ደግሞ መልሱ "ከአርሲ" የሚል ነው። ነውሩን ለመከላከል በሚያደርጉት ግብታዊ ጥረት ሳቢያ ብልግናውን መዋቅራዊ እያደረጉት ነው፥ ያሳዝናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe


የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ለጊዜው ወደጎን እናድርገውና የሚያስገርመውን ክፍል ግን እንየው። ሚዲያው ጥሪ ካደረገላቸው የሀይማኖት ሚዲያዎች ውስጥ በሚገርም ሁኔታ ሁሉም የኦርቶዶክስ ሚዲያዎች አልተገኙም። ከሳምንታት በፊት የአምቦ ተማሪዎችን አስመልክቶ ጥሪ ሲያቀርብ ግን የማይመለከታቸው የእስልምናም ሆነ የፕሮቴስታንት ሚዲያዎች ጥሪውን አክብረው ተገኝተዋል።

ጉባኤው በመግለጫው የልጁን ነውር ተቋማዊ ለማድረግ የሚሞክሩ እንዳሉ ጠቅሶ አውግዟል። የኦርቶዶክስ ሚዲያዎች የልጁን ነውር ይጋራሉ? መገኘት ያልፈለጉበትስ ምክንያት ምንድን ነው? ይህ ያለምንም ጥርጥር ለልጁ የተሰጠ አጋርነት/Solidarity እና ቅቡልነት/Endorsment ነው። የሚያሳዝን ክስተት ነው፣ ከዚህ ጀርባ ምንም ነገር የለም ቢባል ከዚህ በኃላ ማመን ይከብዳል።

📷 Harun Media

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe


ለበርካታ አመታት የንጽጽሩ ዳዕዋ በአላህ ፍቃድ ጥሩ ፍሬ አፍርቷል። በዚህ ስራ ውስጥ ከኦርቶዶክስም ከፕሮቴስታንትም የበቀሉ አማኞች ሊያሸነፉን የሚችሉበትን የትኛውንም አመክኗዊ መንገድ ተጠቅመው ሊታገሉ ሞክረው አልተሳካላቸውም። የመጨረሻ የተጠቀሙት ስልት የስድብ መንገድ ነበርና በሱ መንገድ ሲመጡ ተገዳዳሪ ባለማግኘታቸው ያሸነፉ መሰላቸው..! በስድብ ለመወዳደር የትኛውንም ጠቃሚ እውቀት መቅሰም አያስፈልግም። በስደብ ለመወዳደር የለየለት ባለጌ መሆን ብቻ በቂ ነው። እነዚሁ ሰዎች ሙስሊሙን የሚሉት "በብልግና ተገዳድራችሁ ለምን አላሸነፋችሁንም?" ነው። ማርክ ትዌይን እንደሚናገረው በብልግና ልምድ ያለው ሰው ጋር መከራከር ከባድ ነው። በፊናችን ፈትተን የምንለቅባችሁ መሠላችሁን ባለጌ ከኛው ወገን እንዳናሰለጥንም እምነታችን አይፈቅድም። እምነታችሁን የሚከላከል ጨዋ ምሁር ጠፍቶ ባለጌ ቅጥራችሁን እንደታደገላችሁ የምታምኑ ከሆነ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም..!


የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

3k 0 4 2 250

በየሰንበት ትምህርት ቤቶች ሳይቀር መዋቅሩን ጠብቆ ስለ እስልምና ትምህርት ለመስጠት ፕሮፓዛል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መግባቱን ሲያወሩ ሰማሁ። በእርግጥ አሁን ስድቡን ፎርማላይዝ ለማድረግ ካላሰቡ በቀር ድሮም በአቃቤ እምነት ዘርፍ እስልምናን የተመለከቱ ትምህርቶችን ይሰጣሉ። ይህ ተግባር የኦርቶዶክሱ ብቻ ሳይሆን የፕሮቴስታንቱም ኮሌጆች "Muslim christian relation" በሚል የዳቦ ስም እስከ ማስተርስ ዲግሪ ድረስ ይሰጡበታል። ለአብነት የኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅን (ETC) ኮርስ አውትላይን ብትመለከቱት ይህ ኮርስ ቁርኣንና ሐዲስ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ በግልጽ ይዘረዝራል።

በሙስሊሙስ በኩል ሌላውን እንተወውና የሚመጡ ትችቶችንና ጥያቄዎችን መልስ መስጠት የሚያስችል መዋቅራዊ ድጋፍ/ስራ አለ ወይ? ከተባለ፥ ጠላትም ወዳጅም ይወቀው "የለም" ነው። የንጽጽር ወንድሞች በግል ተነሳሽነት ከሚያደርጉት ትግል ውጭ የሚጠቀስ ምንም ነገር የለም። በአባት ተቋሙም በኩል ከጥቂት ሰዎች የግል ተቆርቋሪነትና ፍላጎት ውጭ ካሪክለምን ያማከለና ነገን የተመለከተ ይህ ነው የሚባል መዋቅራዊ ስራ የለም።

በሌላው እምነት በኩል የሚሰራው ስራ አንገብግቧቸው ያላቸውን ጊዜና ጉልበት ሁሉ ሰጥተው ይህንን ታሪካዊ ስራ መስመር አስምረው ለማለፍ የለፉ ጥቂት ወንድሞች ግን ጉዳያቸው ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በሌላው በኩል የሚሰራውንና መጭውን ፈተናችንን ላየ ግን ዛሬ ችላ ላልነው ድክመታችን ሁሉ አላህ እድሉን በሰጠን መጠን ነገ እሱ ፊት ምን ብለን እንደምንመልስ አላህ ይወቅ። በዚህ በኩል ያለው ጉዳይ አስጨንቆት የሚታገል አዲስ ትውልድ ከመጣ ቢያንስ መስመሩን ገር በማድረግ እናግዘው..!

© የሕያ ኢብኑ ኑህ


⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe


"እስልምና የሰይጣን ሀይማኖት ነው" "ሙስሊሙ ሁሉ አሸባሪ ነው" ወዘተ በሚሉና መሠል እስልምናን እንዲሁም ሙስሊሞችን በከፍተኛ የጥላቻ ቃላት በመወረፍ የሚታወቁት ሰባኪ ፍራንክሊን ግራሀም ዛሬ ሀገራችን ናቸው። አዲስ አበባ ሲገቡ በመንግስት ደረጃ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸውም "ሰበካቸውን" አቅርበዋል። ይህንን ጉዳይ በዋናነት ኃላፊነት ወስዶ ፕሮግራሙን ያሰናዳው ደግሞ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስሉ ነው። በእርግጥም ካውንስሉ ይህንን ሁሉ ነውራቸውን እያወቀ ነው የጋበዛቸው? በዚህ መልኩ የሚታወቁ የጥላቻን መምህር የጋበዘውስ ምን እንዲያስተምሩለት ነው? ይህ ሲርየስሊ የሚታይ በጣም አደገኛ ነገር ነው..!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

4.2k 1 6 85 176

በዚህ የዳዕዋ ስራ ላይ ጥሩ እየታገሉ ያሉ ወንድሞች ቲክቶክ ላይ አሉ። እነዚህን ወንድሞች መከታተል፣ ማበረታታት በጣም ጠቃሚ ተግባር ነው። ብዙ ሰው እዚህ ዳዕዋ ላይ ብቅ ብሎ ጠፍቷል፣ ሰው ከአቅሙ በላይ ሲሆን አይገደድምና ትዝታቸው የቀረን ብዙ ወንድሞች ተለይተውናል። አቅም ያላቸው ሰዎች መድረኩን መያዝ ካልቻሉ እንደ ሌላው ቤተ እምነት ተሳዳቢው ብቻ ቀርቶን በሰው ድርቅ እንመታ እና እነሱን ከማጀገን ውጭ የሚቀረን ነገር አይኖርም። ስለዚህም በተቻለ መጠን እዚህ ዳዕዋ ያሉትን ወንድሞች ከሜዳው ሳይርቁ መስራት የሚችሉበትን መንገድ እየፈጠርን ማበረታታት ከእኛ ይጠበቃል።

በቲክቶክ ልትከታሏቸው የምትችሏቸውን ወንድሞች ከዚህ በታች አስቀምጨላችኃለው፦

🎸ንፅፅር ላይ የሚሰሩ ወንድሞች አካውንት✔

1- ኡስታዝ ሁሴን ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeUow6h/

2- ወንድም ሳላህ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpkQVA/

3- ኡስታዝ አቡ ዩስራ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetphg3t/

4- ኡስታዝ ኢልያህ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpUX4r/

5- ወንድም ኢምራን ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpAp6G/
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpYL6G/

6- ኡስታዝ አቡ-ሙዓዊያህ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetp8CH8/

7- አብዱልከሪም ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpdLhw/

8- ወንድም አህመድ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeUoLAj/

9- ወንድም ትሪፕል ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpFAjr/

10- ወንድም ማሩ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpNSmb/

11- ወንድም ኢብሮ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetp139s/

12- ወንድም ማሒር ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpUVc8/

13- ኡስታዝ አሚር ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdey145p/

14- ወንድም ስሚዝ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetgoPtT/

15- ወንድም አቡ ሩመይሳ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpPVSx/

16- ወንድም ሙሐመድ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetp9vby/

17- ወንድም ካንስል ☑️
🎸:-
https://vm.tiktok.com/ZNdeUKEe8/

18- ወንድም ኢስሚዝ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpabAu/

19- ወንድም ዊስፐር ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZGetpmw4y/

20- ወንድም ሐይከል ☑️
🎸:- https://www.tiktok.com/@nooralano0r?_t=ZN-8uW4lUo42Ks&_r=1

21- ወንድም ፋሩቅ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeyJVTa/

22- ወንድም ዐነስ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeUEoNb/

23- ወንድም ዑመር ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeUtAWU/

24- ወንድም ኤሊያስ ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeUK42j/

25- ወንድም ሀይሰም ☑️
🎸:- https://www.tiktok.com/@haitham_truth1?_t=ZN-8uW5545vgdr&_r=1

26:- ወንድም አቡበከር ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeyeCKu/

27- ወንድም ታላቁ አብርሃም ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeyeNmU/

28- ወንድም ጃቢር ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeyLwod/

29- ወንድም ኑረይን ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeydn1s/

30- ወንድም ጀማል ☑️
🎸:- https://vm.tiktok.com/ZNdeyRd6f/

3.9k 0 72 16 97

ሙስሊም ሴቶች በሒጃብና በኒቃባቸው ሳቢያ መከራ በሚበሉበት ሀገር እህቶቻችን ፈተናዎችን ተሻግረው በዚህ መልኩ በስኬት ሲመረቁ ማየት እጅግ ያስደስታል። እንኳን ደስ አለሽ፣ አላህ መሠሎችሽን ያብዛ..!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe


▣ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፦

በቅርቡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስርኣት ላይ የተሳለቁ የአምቦ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን በተመለከተ በከፍተኛ ትኩረት ጉዳዮን ወደ ህግ የወሰደው ይህ ተቋም ነበር። ለዚህም ጉዳዩ የፍርድ ሒደት ካገኘ በኃላ ሚዲያ በመጥራት መግለጫ ሰጥቷል። ተቋሙ በወቅቱ "እምነት የሚሳደቡና፣ ጀለብያ ለብሰው ትንኮሳ የሚፈጽሙት የፕሮቴስታንት አካላት ላይም እርምጃ እወስዳለሁ" ያለ ቢሆንም እስካሁን ግን የውሀ ሽታ ሁኗል። ምናልባት "ለሁሉም እኩል እሰራለሁ" የሚል ሽንገላ ታስቦበት የተጨመረ የመግለጫ ባላንስ መፍጠሪያም ይሆናል። ለማንኛውም የትኛውም ቦታ የሚፈጸም ነውርን እኩል የማይዳኝ ከሆነ ፍትሐዊነቱ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። የመጅሊሱ አባልነትም ከቁጥር ማሟያነት የዘለለ ሚና አይኖረውም።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

3k 0 10 13 114

📌 መፍትሄው ምንድን ነው?

1/ ሲኖዶስ፦

ንጽጽር ውስጥ በክርስትናው በኩል የእሱን ጥያቄ ከተመሳሳይ ምንጭ እያገኙ የሚጠይቁ ብዙ ሰዎች አሉ። በተገቢው መልኩ ከእነሱ ጋር መወያየትም መልስ መስጠትም ተገቢና ትክክለኛ ስራ ነው። በዚህ መልኩ ጸያፍ ቃላትንና ምልክቶችን እየተጠቀሙ መሳደብን ግን ከማንም በላይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልታወግዘውና ልታስቆመው የሚገባ ጉዳይ ነበር። መሠል ጉዳዮች ምንጊዜም ችላ ሲባሉ በሌላውም ወገን አጸፋ የሚሰጡ ተመሳሳይ ስብእናዎች ማቆጥቆጣቸው አይቀርም። ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም። ስለዚህ ሰዎች በስርኣት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ማድረግ የእምነቱ መሪ ተቋም ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው። ይህንን የሚያደርጉትንም በይፋ አውግዞ መገሰጽ ይገባል።

▣ መጅሊሱ፦

መጅሊሱ የህዝበ ሙስሊሙ ላዕላይ ተቋም ነው። መሠል ጉዳዮችን በህግ ስርኣት የማስያዝ ኃላፊነት በዋናነት የመጅሊሱ ተግባር ነው። መሠል ስብእናዎች ችላ በተባሉ ቁጥር ታዋቂነትን የሚሹ በርካታ አረሞች ማቆጥቆጣቸው አይቀርም። ይህ ለአብሮ መኖርም ትልቅ ጋሬጣ በመሆኑ በጊዜ እልባት መስጠት ከመጅሊሱ የሚጠበቅ ነው። መጅሊስ ከነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ስብእና በላይ ሊገደው የሚገባ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም። መጅሊሱ የህግ ክፍል አለው፣ መሠል ጥሰቶችን ማስቆም የዚህ ክፍል ኃላፊነት ይመስለኛል። እንዲህ አይነት ጉዳዮች በኦርቶዶክስም በፕሮቴስታንት በኩል ተፈጽመው ቢሆን ፈጻሚዎቹ አንድ ቀንም እንደማያድሩ የአምቦ ተማሪዎች ተግባር ማሳያ ነው።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

2.9k 0 14 14 106

በቅርቡ አንድ "እፎይ" ለሚባል ሰው መልስ መስጠት ጀምሬ ነበር። ግለሰቡን የእውነትም ተከታትየው ካለማወቄ አንጻር ሰዎች ባስቀመጥኩት የቴሌግራም ቡት በኩል መልስ እንዲሰጠው አብዝተው ቪዲዮ ሲልኩልኝ ነው በደንብ ማየት የጀመርኩት። መጀመሪያ ሳየው ጤነኛ/Stable/ አልመሰለኝም ነበር። እንደመጣለት የሚሰነዝራቸው ጸያፍ ቃላት፣ የጤነኛ የማይመስሉ አካላዊ ተግባራቱ አንድ ላይ ተደማምረው ይህ ሰው በምን ተአምር በብዙ ኦርቶዶክስ ምዕመን ዘንድ እንደ "ቅዱስ" እንደታየ ደንቆኝ ነበር። ከበርካታ አመታት በፊት የሚታወቁና የተመለሱ የነዴቭድ ውድና ሳም ሻምኦን ያረጁ ጥቂት አርጊውመንቶችን እጅግ አስቀያሚ የዱርየ ቃላት በመጨማመር ከማምጣት በዘለለ የፈጠረው አዲስ ነገር አልነበረም። ለተርታው ህዝብ ካልሆነ በስተቀር ለንጽጽር ሰው "ኑ በብልግና እንፎካከር" ከሚል የዘለለ ጠንካራ ጥሪና ሙግቶችም አልነበሩም።

የኦርቶዶክስ ምዕመኑን ድጋፍ ስመለከት ግን ቸርቿ በዚህ ልክ "እስልምናን በጸያፍ ቃል የሚሰድብላት ዱርየ" አጥታ ተቸግራ እንደነበር ያስባሉ ወይ?የሚለው ግርምቴ ማቆሚያ አልነበረውም። ይህንን ይዛችሁ ስለ ክርስትና ያለውን መረዳት ለማየት የተወሰነ ቪዲዮዎቹን ስትመለከቱ ግን በክርስትናው ዙሪያ መሠረታዊ የሚባል እውቀት እንኳን እንደሌለው በቀላሉ ትገነዘባላችሁ። ታዲያ በዚህ ደረጃ እጅግ የወረዱ የቃላት አገላለጾችን መጠቀም ለምን አስፈለገው?ለሚለው መልሱ ግልጽ ነው። በዚህ መልኩ ካልሆነ የራሱንም ሆነ የኛን ሰው ትኩረት ማግኘት እንደማይችል ስለተረዳ ነው። ይህ ግለሰብ ጨዋነት ግብሩ ካልሆነ በራሱ ሜዳ መባለጉ የራሱ ምርጫ ነበር። ግን እሱ ስለማይጠቅመው በዚህ አለም ላይ አንድ ተወዳጅ ስብእና መረጠ፣ እሳቸውንም መስደብ ከዚህ በፊት ስለ ባህል መድሀኒት ሲያወራ ካጣው አጀንዳ በላይ የተሻለ እይታ አመጣለት።

ሁሉም ነገር ድንበር እንዳለው ማሳየት ግን ተገቢ ነው። በዚህ ዙሪያ ምን መደረግ ይኖርበታል? የሚለውን በዝርዝር ከዚህ በኃላ በአላህ ፍቃድ አከታትየ የምዳስስ ይሆናል።

https://t.me/Yahyanuhe

3.3k 0 13 10 127





በቅርበት ከማውቃቸውና በዳዕዋ ስልጠና ላይ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ወንድሞቻችን መካከል አንዱ የሆነውን ወንድማችንን በሙያው ጉዳይ ሲኖራችሁ እንድትደውሉለት ላስተዋቃችሁ።

ለመኖሪያ ቤታችሁ ለካፌ፣ ለሱቅ እንዲሁም ለቢሮ Interior design ማሠራት ለምትፈልጉ፤ በተጨማሪም ለድርጅታችሁ ሎጎ ባነር ስቲከር ብሮቸር እና ቢዝነስ ካርድ ማሠራት ለምትፈልጉ ሁሉ ጥራት ያለው ስራ እና ነፃ የማማከር አገልግሎት ከ line design solution ጋር ያገኛሉ።

📌 ለአርክቴቸራል ቢሮዎች የተለየ የዲዛይን ጥቅልም አዘጋጅተዋል። ለማማከርም ሆነ ዲዛይን ለማሰራት ከታች ባለው ስልክ ያገኙታል፦

Unique design package for architectural offices.

0910373510 / 0909363500


"ብዙ በልታችሁ ስለምትጾሙ አይርባችሁምና ጾም አይባልም" የሚለውን የወገኖቻችንን ክርክር በጾም አንጀት ከመስማት የበለጠ ደግሞ የሚያደክም የለም። አንዳንዱ እንደሞከረ ሰው የምሩን ሁሉ ነው የሚከራከራው፣ ተከራካሪው ፕሮቴስታንት ሲሆን ደግሞ ግርምቴ እጥፍ ይሆናል። የረሀቡ ጉዳይ ካሳሰባችሁ ሞክራችሁ ከማየት በዘለለ በየትኛው ሎጂክ እንድናስረዳችሁ ነው የምታደክሙን?

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe


ከአመታት በፊት ወደ አኼራ የሄደ አንድ ቃሪዕ ቁርኣን ሲቀራ ተከፍቷል። ሰው ያዳምጣል፣ ከሞተ በኃላም ቢሆን መልካም አሻራው ቀጥሏል። በየትኛው የኸይር ስራ ዘርፍ፣ እድሜን እንደ ተሻገረ ሰደቃ አትራፊ ስራ የለም።

https://t.me/Qurantilawas/65


የክርስቲያን ጸሀፍት የሚፈጽሟቸው ማጭበርበሮች/Academic Dishonesty/ ወደር የላቸውም። ከአውድ ውጭ የሙሉ ሀዲስን መልዕክት ቆርጦ የተንሻፈፈ ትርጉም መስጠት ከነዚህ ውስጥ የሚጠቀስ ነው። በዛሬው ማብራሪያችን በዚህ ዙሪያ የቀረበውን ማምታቻ እንመለከታለን፦

https://vm.tiktok.com/ZMBJyd1nK/


ከምግብ በኃላ ጣት መላስን አስመልክቶ የነብዩ መሐመድን "ﷺ" ንግግር በመጥቀስ ዴቪድ ውድ ጥያቄ ያነሳል፣ ጉዳዩን ከነብይነታቸው ጋር በማያያዝም "አሳሳቢ" አድርጎ ሲደነቅበትም ይስተዋላል። በዚህ አጭር ቪዲዮ ሀሳቡና ምላሹ ተዳሷል።

https://vm.tiktok.com/ZMB1qbpSe/


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ቪዲዮውን ማን እንዳዘጋጀው አላውቅም፤ የግለሰቡ ግልጸኝነት እንዳለ ሁኖ ግን አሁን ላይ የፕሮቴስታንት ቸርቹን የወረሰውን የአረም መጠን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። እነዚህን የሚቃወሙ የራሳቸው ሰዎችም በአብዛኛው ከተመለከታችኃቸው ይህንኑ ስራ "አራዳ ቅርጽ" አስይዘው የሚሰሩ ሌላ ቨርዥኖች ናቸው። ከነዚህ የሚለዩት ፈጣጣ አለመሆናቸው ብቻ ነው። ሰው ወደዚህ እምነት ለመሄድ አእምሮውን ቅድሚያ ሌላ ቦታ ማስቀመጥ ይኖርበታል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

5.9k 0 45 12 124
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.