በየሰንበት ትምህርት ቤቶች ሳይቀር መዋቅሩን ጠብቆ ስለ እስልምና ትምህርት ለመስጠት ፕሮፓዛል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መግባቱን ሲያወሩ ሰማሁ። በእርግጥ አሁን ስድቡን ፎርማላይዝ ለማድረግ ካላሰቡ በቀር ድሮም በአቃቤ እምነት ዘርፍ እስልምናን የተመለከቱ ትምህርቶችን ይሰጣሉ። ይህ ተግባር የኦርቶዶክሱ ብቻ ሳይሆን የፕሮቴስታንቱም ኮሌጆች "Muslim christian relation" በሚል የዳቦ ስም እስከ ማስተርስ ዲግሪ ድረስ ይሰጡበታል። ለአብነት የኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅን (ETC) ኮርስ አውትላይን ብትመለከቱት ይህ ኮርስ ቁርኣንና ሐዲስ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ በግልጽ ይዘረዝራል።
በሙስሊሙስ በኩል ሌላውን እንተወውና የሚመጡ ትችቶችንና ጥያቄዎችን መልስ መስጠት የሚያስችል መዋቅራዊ ድጋፍ/ስራ አለ ወይ? ከተባለ፥ ጠላትም ወዳጅም ይወቀው "የለም" ነው። የንጽጽር ወንድሞች በግል ተነሳሽነት ከሚያደርጉት ትግል ውጭ የሚጠቀስ ምንም ነገር የለም። በአባት ተቋሙም በኩል ከጥቂት ሰዎች የግል ተቆርቋሪነትና ፍላጎት ውጭ ካሪክለምን ያማከለና ነገን የተመለከተ ይህ ነው የሚባል መዋቅራዊ ስራ የለም።
በሌላው እምነት በኩል የሚሰራው ስራ አንገብግቧቸው ያላቸውን ጊዜና ጉልበት ሁሉ ሰጥተው ይህንን ታሪካዊ ስራ መስመር አስምረው ለማለፍ የለፉ ጥቂት ወንድሞች ግን ጉዳያቸው ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በሌላው በኩል የሚሰራውንና መጭውን ፈተናችንን ላየ ግን ዛሬ ችላ ላልነው ድክመታችን ሁሉ አላህ እድሉን በሰጠን መጠን ነገ እሱ ፊት ምን ብለን እንደምንመልስ አላህ ይወቅ። በዚህ በኩል ያለው ጉዳይ አስጨንቆት የሚታገል አዲስ ትውልድ ከመጣ ቢያንስ መስመሩን ገር በማድረግ እናግዘው..!
© የሕያ ኢብኑ ኑህ
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe