Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ስለ ክብርህ ስትል ተዋቸው
~
የሰው ልጅ አመል እንደ መልኩ ብዙ አይነት ነው። ብዙ ደግ የመኖሩን ያህል በየትኛውም ሁኔታ መጥፎህን ብቻ ለማውራት ያሰፈሰፈ አለ። ልቡ በክፋት የተሞላ። በጎህን ሲያይ ይከፋዋል። ሰዎች በመልካም ቢያነሱህ ያመዋል። ያለ ስምህ ስም ይሰጥሃል። ያለ ግብርህ ያሸክምሃል። በሌለህበት ያውልሃል። ያለህን መልካም ይገፍሃል። ክፉህን ቢያይ ይቦርቃል። ሰዎች ቢያወግዙህ አታሞ ይመታል። ይቅርታህ አይዋጠውም። ዝምታህ አይጥመውም። ምላሽህም አይመቸውም። የቱንም ብታደርግ አታስደስተውም። ስህተት ቢያገኝ ጭራና ቀንድ አውጥቶለት ቆርጦ፣ ቀጣጥሎ ጭራቅ ያደርግሃል። ንግግርህን ፈፅሞ ባላሰብከው መልኩ ተርጉሞ ራሱ አጣሞ በተረዳው ላይ ተመርኩዞ ነብር ግስላ ሆኖ ይነሳብሃል።
በቃ! አንዳንዱ ባህሪው የውሻ አይነት ነው። ባለፍክ ባገደምክ ቁጥር ይጮሃል። "ዋው!" ማለትን የመተንፈስ ያህል ኖርማል አድርጎታል። ብትነካውም ይጮሃል። ብትተውም ይጮሃል። እንዲያውም ውሻ ሲያይህ ነው የሚጮኸው። ይሄኛው ሳያይህም ይጮሃል። "አትርሱኝ" ባይ ነገር ነው። በሌለህበትም፣ ሳታስታውሰውም ይጮሃል። በየትኛውም ሁኔታ ሊነድፍህ ስለተዘጋጀ ተያያዥ ጉዳይ እስከሚያገኝ አይታገስም። ይበላዋል። ያሳከዋል። ስለ ጦሃራ ስታወራ "ዋው!" ስለ ተውሒድ ስትናገር "ዋው!" ስለ ራስህ ብታነሳ "ዋው!" ራሱ የሚደግፈውን ሃሳብ ብታነሳም "ዋው!" ከማለት አይመለስም። ብትመልስለት አገር በጩኸት ያቀጣጥላል። ዝም ስትለውም ወይ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ወይ "አሸነፍኩ" ብሎ ይጮሃል።
እና ምን ይሻላል? ጩኸቱን ላታስቆመው ነገር አትጨነቅ። እርሳው። ሰላምህ ያለው እሱን ከመርሳት ነው። ሊፈትንህ ይችላል። ከዚህ ውጭ ያለው ምርጫ ግን የበለጠ ፈታኝ ነው። አሕመድ ሻኪር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"የማያውቅ ሁሉ ይወቅ! ምድር ላይ ሞኞች ብዙ ናቸው። እና አንድ ሰው ከሞኝ ለሚንፀባረቅ ሞኝነት ሁሉ የሚበሳጭ ከሆነ በብስጭቱ ሰበብ ብሶት መከፋቱ ይራዘማል። ሞኞችን ያሻቸውን ይበሉ ተዋቸው። ለክብርህ ስስት ይኑርህ። ክብርህ ለሞኞች ምላስ ተብሎ የሚመነዘር ከመሆን በላይ ውድ ነውና።"
[መጅሙዑል መቃላት፡ 1/579]
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor