TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
  • flag Uzbek
    Sayt tili
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Saytga kirish
  • Katalog
    Kanal va guruhlar katalogi Kanallar qidiruvi
    Kanal/guruh qo‘shish
  • Reytinglar
    Kanallar reytingi Guruhlar reytingi Postlar reytingi
    Brendlar va shaxslar reytingi
  • Analitika
  • Postlarda qidiruv
  • Telegram'ni kuzatish
Zehabesha

14 Mar 2024, 13:58

Telegram'da ochish Ulashish Shikoyat qilish

ባለፉት ስድስት ወራት ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 205 ሠራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል-የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2016(ኢዜአ)፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 205 ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

የደንበኞችን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ የፓስፖርት ህትመት መከናወኑንም ነው አገልግሎቱ የገለጸው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የአገልግሎቱን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ባለፋት ስድስት ወራት ተከማችቶ የነበረውን የፓስፖርት ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ መፍታት የሚችል ህትመት መከናወኑን ገልፀዋል።

በዚህም ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት የታተመ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 640 ሺህ የሚሆነው ለደንበኞች መሰራጨቱን ተናግረዋል።

ይህም የፖስፖርት ህትመት ክፍሉ ሌት ተቀን በትጋት በመስራት ያመጣው ዉጤት መሆኑን ጠቅሰው ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ ዜጎች በተሰጣቸው የቀን ቀጠሮ መሰረት ፓስፖርታቸውን መረከብ ይችላሉ ብለዋል።

ባለፋት ስድስት ወራት 205 ከውጭ አገር ደላሎች ጋር ተመሳጥረው በህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ የአገልግሎቱ ሰራተኞች ከስራ እስከማባረር የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ገልጸዋል።

ባለፋት ስድስት ወራት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸውና ባልተፈቀደላቸው ስራ ላይ የተሰማሩ ከ10 ሺህ በላይ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ምርመራ በማድረግ እንደ ጥፋት መጠናቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉንም አንስተዋል።

ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ሰነድ አሟልተው እንዲመዘገቡ መደረጉንም ነው ያነሱት።

@ኢ.ዜ.አ

14.8k 0 11 5 57
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi Kanallar to‘plamlari Kanallar qidiruvi Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Telegram-kanallar reytingi Telegram-guruhlar reytingi Postlar reytingi Brendlar va shaxslar reytingi
API
Statistika API'si Postlar qidiruvi API'si API Callback
Kanallarimiz
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
O‘qish
Академия TGStat Telegram tadqiqoti 2019 Telegram tadqiqoti 2021 Telegram tadqiqoti 2023
Kontaktlar
Справочный центр Qo‘llab-quvvatlash Email Vakansiyalar
Har xil narsalar
Foydalanuvchi shartnomasi Maxfiylik siyosati Ommaviy oferta
Botlarimiz
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot