👆③✍✍✍ …ስለሌለው ብዙ ነገር የሚያጣም ሰው አለ። ሰው የሚያጣው ደሀ ብቻ አይደለም። በሽተኛ ብቻ አይደለም። ህመምተኛ ብቻ አይደለም። ዲግሪ፣ ዶክትሬት፣ ኢንቨስተር፣ ውብ፣ አትሌት፣ አርቲስት፣ ሚንስተር ሆኖም ሰው የሚታጣበት ጊዜ አለ። ሰው የለኝም አለው ህመምተኛው ለጌታ። መድኃኒት የሆነ ሰው ይስጣችሁ። አሜን በሉ።
"…የ30 ቤቱ ወጣት ውቡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ከእርሱም ጋር ያሉት ጎበዛዝቱ ሐዋርያቱ አንጠልጥለው ውኃው ውስጥ እንዲከቱት ጠብቆም ሊሆን ይችላል ህመምተኛው፣ በሽተኛው ሰውዬ። ወይ ደግሞ እንዴዴኤኤ ይሄን ሰው የዛሬ ዓመት፣ ስምንት ዓመት፣ አስራ ዘጠኝ ዓመት፣ ሠላሳ ሁለት ዓመት፣ ሠላሳ ሰባት ዓመት እዚሁ ጋር እዚሁ አልጋው ላይ ተኝቼ አይቼው ነበር እያሉ እንደሚጠይቁት እንደ አንዳንድ ሰዎችም መስሎት ሊሆን ይችላል። የስንቱን የድኅነት፣ የፈውስ ታሪክ እያየ እሱ ሰው ስለሌለው ብቻ መዳን አቅቶት የሚማቅቅ ሰው። አያሳዝንም በማርያም። ዛሬ ግን ከፊቱ የቆመው እግዚአብሔር ወልድ ነው። ወልደ አብ ወልደ ማርያም። ከሦስቱ አካል አንዱ አካል። ዓለማትን በቃሉ የፈጠረ የእግዚአብሔር ቃሉ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ከፊቱ የቆመው። እናም ተናገረ ጌታ። "ኢየሱስ፡— ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው።" አለቀ። የጠበሉ ጌታ አዘዘ፣ ተናገረ። አስቀድሞ በዘፍጥረት ብርሃን ይሁን ብሎ ቃል አውጥቶ ብርሃናትን፣ ሰማይና ምድርን፣ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረው ጌታ አሁን ደግሞ 38 ዓመት ሙሉ በሰው እጦት ምክንያት ድህነተ ሥጋ ያጣውን ምስኪን ሰው ራሱ ከዙፋኑ ወርዶ መጥቶ ከፊቱም ቆሞ "ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው። 38 ዓመት አልጋ ላይ የተኛን ሰው አልጋህን ተሸከም ሊል የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ቆይ ወገቡ ይጽና፣ ሙቅና ቅልጥም በልቶ ይጠገን፣ ይጠንክር እንጂ፣ የዲስክ መንሸራተት ቢገጥመውስ ሊል የሚችለው ሰው ብቻ ነው። እግዚአብሔር ግን ሲሠራ ሠራ ነው ትክክል ሆኖ ነው የሚሠራው" በቃ አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይለናል "ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።" አለቀ። ፋይሉ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት። ጌታ እኮ ነው።
"…የዛሬ ዓመት አካባቢ ይመስለኛል ዘመዴ ይለኛል አንድ ዲያቆን። አቤት እለዋለሁ። ዲቪ ደረሰኝ። እኔ ገጠር ነው የምኖር። ቤተሰቦቼም፣ ዘመዶቼም ገጠር ነው ያሉት። አማሪካ ዘመድ የለኝም። ድሆች ነነ። ዲቪው ደርሶኝ ሰው ግን አጣሁ። በትምህርቴም ጥሩ ነኝ። ዲቪ እንደደረሰኝ የሰሙ ብዙ ሰዎች አግብተንህ እንሂድ፣ እህቴን አግብተህ ና የሚሉኝ በዙ ይለኛል። ታዲያ እላለሁ በልቤ አግብቶ አይሄድም እኔ ጋር ምን አለፋደደው እላለሁ። ታዲያ ለምን አግብተህ አትሄድም ብዬ ጠየቅኩት። መለሰልኝም። "…አሃ ክህነቴን ማስቀጠል፣ ድንግልዬን መጠበቅ እፈልጋለሁኣ! ወንድምዓለም አንተ ባታውቀኝም አታውቀኝም እባክህ እርዳኝ። ክህነቴን አስጠብቅልኝ። ካልሆነም ይቀራታል እንጂ ክህኔቴንማ አላቆሽሻትም ይልኛል። የአስረዳኝ የዚህ ዓይነት ሺ ጥያቄዎች በየጊዜው ይቀርቡልኝ ዐውቃለሁ። እኔም ለአንዱም መልሼ አላውቅም። የዚህ ሰው ግን ዲቪ ደርሶት "ክህነቴን አላቆሽሻትም" ማለት ቀልቤን ሳበው። እንዲህ የሚል ወጣት ታዳጊ ልጅ ቀልቤን ገዛው። ደወልኩለት። አወራኝ። ጸልይበት ሰው ልፈልግ አልኩት። ወዲያው ለሱሬ ነገርኩት። ሱሬን ተማጸንኩት። ሱሬ ለቀሲስ ንዋይ ነገረው። ቀሲስ ነዋይ ካሳሁንም ለወንድሙ ለቀሲስ ጌትነት ነገረው። እርሱም ስፖንሰር ሆነው። ያ የማላውቀው ልጅም "የከበረች፣ ቅድስት ክህነቱን" ሳያቆሽሽ ጠብቆ ሁሉ ነገር ተከፍሎለት፣ ወጪም ተችሎት አሜሪካ በሰላም ገባ። አሁን ሁሉ ነገር አልቆለት ቤተ ክርስቲያንን በክብር እያገለገለ ይኖራል። እስከ አሁን የልጁን መልክ አላየሁትም። ቦታውን ከማልጠቅሰው ከአንደኛው ከዐማራ ክልል የመጣ ልጅ ነው። አያችሁ ሰው አንዳንዴ እንዴት መድኃኒት እንደሚሆን። ቀሲስ ነዋይን የቀሲስ ጌትነትን ስልክ ስጠኝ ብዬ ልደውል ከፎከርኩ ይኸው መንፈቅ ሆነ። እባክህ ቀሲስ ጌትነት አንተ ደውልልኝና እኔ ላመስግንህ አባቴ። አያችሁ ጥጋቤን። ጉድ እኮ ነው።
"…ከገንዘብ ይልቅ የሰው ሀብት ያለው ሰው ዕድለኛ ነው። የእግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር የሚገለጠው በሰዎች በኩል ነው። እግዚአብሔር ሲጣላም አርጩሜ አድርጎ ሊቀጣህ ሲፈልግ ሰውን ነው የሚያስነሣው። ዲዮቅልጥያኖስን፣ ፈርኦንን፣ ዮዲት ጉዲትንና ግራኝ አህመድን፣ ደርግንና ወያኔን አቢይ አሕመድን ያስነሣና ዱቄት ያደርገናል። ይዠልጠናል። ሲታረቀንም፣ ከውርደት ሲታደገንም። ከፍ ከፍ ቀና ብለን እንድንሄድ ሲያደርገንም ልክ እንደ እምዬ ምኒልክ ዓይነቶቹን አስነሥቶ ነው የሚያኮራህ የሚያስከብርህ። ሰው ለሰው መድኃኒቱ ነው። ሞቱም መጥፊያውም ነው። ጤና ዕድሜ ሀብት ያለው ሰው ሦስቱም ኑረውት የሰው ሀብት ከሌለው አለቀ። ይሾቃል። ሰው እንዲወድህ ብለህ ጥገኛ አትሁን። ልጥፍ አትሁን። አስመሳይ መስሎ አዳሪ አትሁን። ተለማማጭ፣ ተልመጥማጭም አትሁን፣ አድርባይ፣ እስስትም አትሁን። እንደ ክረምት አየር ፀሐይ ሲሉህ ደመና፣ ዝናብ አትሁን። ሜካፓም አትሁን። አፈ ቅቤ ልበ ጩቤም አትሁን። እወደድ ብለህ ከእውነት አትራቅ፣ አታፈግፍግ። የሚወድህ ሰው ከነ ንፍጥህ፣ ከነ ለሃጭህ ይውደድህ እንጂ አጣጥቦ እንዲስምህ አትፍቀድለት። ፍቅር ንፍጥና ለሃጭን አያይም። ፍቅር ለአፍቃሪው እውር ነው። ካፈቀርክ አፈቀርክ ነው። ያፈቀርከው መልአክ፣ ውብ ጽጌሬዳ፣ ደማቅ ፀሐይ፣ የንጋት ጮራ፣ የሌሊት ጨረቃ መስላ የምትታየው ለአንተ እንጂ ሌላው አይደለም። ምኗን አይቶ ነው የወደዳት? ያፈቀራት? ያገባት? እንዴት ከዚህ መሸጦ ጋር ትኖራለች? መስተፋቅር አስደርጎባት፣ ጠንቋይ ጋር ውሎባት ነው እንጂ፣ ገንዘቡን አይታ ሀብቷን ተመልክቶና ፈልጎ ነው እንጂ ያለ አንዳች ምክንያት እንዲህና እንዲያ አልሆነም እያለ አዳሜ ሲያወራ ይውል ያድር እንጂ ምንም አይፈይድም። ይሄን ግትር፣ ጯሂ፣ ደረቅ እንዴት አገባችው? ይህቺን ክችች ያለች ወይ አትበላ አታስበላ እንዴት አገባት? እያለ አዳሜና ሔዋኔ ከጀርባህ ሲፈተፍት ንቅንቅ የማትለው አንተ በእውነት ያለ ሀሰት ያፈቀርክ፣ እሷም ያፈቀረችህ እንደሆነ ብቻ ነው። ቤተሰብ ተሰብስቦ በቅሎ ናት ፍታት፣ ከዘራችን አይገጥምም ፍቺው ቢል መስሚያችሁ ጥጥ የሚሆነው እናንተ በእውነት ስለ እውነት በሃቅ ከተፋቀራችሁ ብቻ ነው። ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ቢል በእግዚአብሔር ፍቅር የተባረከ፣ የተጣመረን ሰው ማንም አይለየውም። ፍቅር እስከ መቃብር አለቀ።
"…የእኔም ሀብት ይሄ ይመስለኛል። የሰው ፍቅር ሀብትማ አለኝ። እንደ እኔ በዚህ የከበረ ያለም አይመስለኝ። ብዙዎች በድርቅናዬ ይጠሉኛል፣ በጩኸቴ ይጠየፉኛል፣ በመራር እውነቴ ይቀየሙኛል፣ በግግምናዬ ይበሳጩብኛል። ይሰድቡኛል፣ ይዝቱብኛል፣ ይበሳጩብኛል እያነቡ እስክስታ ነው የምሆንባቸው። ወደድነው ባሉኝ ማግስት፣ ታቦት ይቀረጽለት፣ ብርጌድ ይሰየምለት ባሉኝ ማግስት እሪሪ እንዲሉብኝ ባደርጋቸውም ግን ሲሰድቡኝ ከርመው ስጠፋ ግን እናፍቃቸዋለሁ። እሰይ ጠፋ ተገላገልነው አይሉም። አይናቸውን በጨው ታጥበው መጥተው ይጽፉልኛል። አንተ እኮ ይሄን ይሄን ብታስተካክል በጣም ጥሩ ነበር ብለው መናፈቃቸውን ሳይሰስቱ ይጽፉልኛል። በስድባቸው ከፔጄ የቀስፍኳቸው ሁላ ቆይተው አንተ ልክ ነበርክ ዘመዴ ይሉኛል። ሲሰድቡኝ እንኳ ዘመዴ እያሉ እስከ ዶቃ ማሰሪያዬ የሚያስታጥቁኝ የትየለሌ ናቸው። ከእውነት ሚዛኔ ግን ዝቅ አልላትም። ሰውን ለማስደሰት ብዬ አንዳች የውሸት ቅመም ለማጣፈጫነት ለመጠቀም…👇③ ✍✍✍