Zemedkun Bekele (ዘመዴ)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


“…መድኃኒት ከኅጥኣን ሩቅ ነው…።” መዝ 119፥155 “…በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ኛ ጴጥ 3፥15 …“…ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።” 2ኛ ጢሞ 2፥5

"…በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለ ምን ታያለህ፥ በራስህ ዓይን ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን፡— ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ። ማቴ 7 ፥ 41-42

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

16k 0 10 1.1k 925

"…በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለ ምን ታያለህ፥ በራስህ ዓይን ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም? በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን፡— ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ። ሉቃ 6፥ 41-42

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

43.1k 0 27 1.2k 2.4k

"…ቲክቶክ መንደር ገብቻለሁ… ግቡልኝማ…!

• እፎኦኦኦይ…!

50.6k 0 8 261 1.7k

ልመጣ ነኝ…!

"…የዘመነ ፌስቡኩ የቤተ ዐማራው ዐማራ ሳይንቴው መራዴ ታደሰ ከስንት ዓመት በኋላ ዳግም ከወንድም እፎይ ጋር ደብሎ ስሜን ደንቢጥ አድርጎ አሳንሶ አንሥቶኛል፣ ባለሁበት ስፍራም ስቅ፣ ህቅ እስኪለኝ ድረስ ለኡማው ከሶኛልና በዚያውም እግረመንገዴን ልመጣለት እና እሪሪ ቁቁ ላስብለው ነኝ። ምንትላላችሁ?

"…በተጠራሁበት የእፎይ ጉዳይና ስለ መለኮታዊው የኢትዮጵያ ጉብኝት የሆነች ነገር ልተነፍስ ለአጭር ሰዓት በቲክቶክ ብቅ ልል ነኝ።

~ በላሌ ዴምጣ… ልምጣ አይደል…? 😂

50.4k 1 10 117 1.4k

ጠያቂው ተጠየቅ እንጂ…!

"…ክርስቶስ ማነው…? በሚል 303 ጥያቄዎች አሉኝ ብሎ እሱ በማያምንበት ለእኔ ግን ጌታዬ አምላኬና መድኃኒቴ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጥያቄ አቅርቧል። በመጽሐፍ መልክም አሳትሟል። መልካም መብቱ ነው። አሕመዲን ጀበል በጌታ ላይ ተሳልቋል፣ በምስጢረ ሥላሴ ላይ አሹፏል፣ ቀልዷል ብለን ሰልፍ አልወጣንም። ይገደልም አላልንም።

"…አሕመዲን ጀበል በኢየሱስ ክርስቶስ ስለማያምን የፈለገውን የመጻፍ መብት አለው ከተባለ እፎይም ሆነ እኔ ስለማላምንበት ስለ መሀመድ ብጽፍ ለምን ትናደዳለህ? አንተ የእኔን በመናቅህ ዝም እንዳልኩህ እኔም የአንተን ስንቅ ዝም ማለት ነው እኮ ያለብህ። አንተ የእኔን ድንበር አልፈህ ለማዋረድ ስትሞክር እኔ በድንበሬ ላይ ቆሜ የአንተን ባዋርድ ለምንድነው ጎረቤት ሁላ እስኪረበሽ የምትንጫጫው። አንተ "ለነቢይህ" ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውዴታ አለኝ ካልክ እኔ ለአምላኬና ለመድኃኒቴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ዓይነት ፍቅር፣ መስዋዕትነት የማልከፍል ይመስልሃል?

"…ንጽጽር ብለህ ያለ አቅምህ መጽሐፍ ቅዱስ ትንተና የጀመርከው አንተው ራስህ ነህ። አንተ የማታውቀውን መጽሐፍ ቅዱስ ገልጠህ ስትዳክር ዝም ብለን ቆይተን፣ መልስም ከዚያው ከመጽሐፍ ቅዱስ ስንሰጥህ ከርመን፣ አይ ቆይ እስኪ ለምን ደግሞ ከቁርዓኑና ከሐዲሱ መልስ አንጠይቃቸውም ብለን ስንነሣ ቆንጨራ ይዞ መፎከር ምን የሚሉት ነው? ወይ አስቀድሞ አለመፎከር፣ አቅምን ዐውቆ መኖርም ጥሩ ነው። ግጠመኝ ካልክ በኋላ አንተ በእኔ መጽሐፍ ቅዱስ ልትሞግተኝ ስትመጣ፣ እኔ ደግሞ በአንተው ቁርዓን ልሞግትህ ስነሣ የምን መነጫነጭ ነው?

"…በመስታወት ቤት የሚኖር ሰው የድንጋይ ውርወራ ጠብ ውስጥ ፈጽሞ አይገባም። ባለጊዜ ነን ተብሎ እንደ ሕጻን በልቅሶ፣ በጩኸት ፍላጎትን ለማሳካት መሯሯጥ ያስገምታል።

• እፎይ…!

50.3k 2 45 376 2.7k

"…የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12… “…ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6። “…ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።” መዝ 65፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

49.4k 0 2 1.2k 1.5k

"…የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12… “…ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6። “…ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።” መዝ 65፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

49.6k 0 5 694 1.2k

• እፎኦኦኦኦይ…

"…ደኅና እደሩልኝ። የነገ ሰው ይበለን። 🙏🙏🙏

51.4k 1 9 75 1.7k

"…እኔ የምለው የሆነ አጀንዳ መጀመሪያ ላይ እኔ ሳነሣው አዳሜና ሔዋኔ ከያለበት እንደ ግሪሳ ወፍ ግርር ብሎ መጥቶ ያለ የሌለ ክፍት አፉን ይከፍትብኝና መጨረሻ ላይ እኔ አጀንዳውን ልክ አግብቼ መስመርም አስይዤ ወደሌላ ትኩስ አጀንዳ ከገባሁ በኋላ ያ ሲሰድበኝ ክፍት አፉንም ሲከፍትብኝ የነበረው መንጋ ሁላ እኔ የተውኩትን አጀንዳ እንደ አዲስ አንሥቶ የሚንበጫበጨው ሙንኡኖኖ…?

"…ለማንኛውም ዘመድ ሚዲያ እየመጣ ነው። እመኑኝ የኢትዮጵያን ቦለጢቃ ልክ እናስገባዋለን። ምድረ ሌባ ሁላ መግቢያ መውጪያ፣ መደበቂያ እስኪያጣ ድረስ ይመረመራል። እመኑኝ ውሸት በኢትዮጵያ ቦታ አይኖራትም።

• የኢትዮጵያን ትንሣኤ፣ የዐማራን ድል የማበሥረው እኔ ነኝ። ዋጠው።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ተቀበሉ…

"…እስቲ ከዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ምን እንማራለን…?

• በገባችሁ በተረዳችሁት መጠን ጻፉ እስቲ…✍✍✍

• እኔ ዝም ብሎ በብላሽ አለመበላትን ተምሬአለሁ።
• እስከመጨረሻው ደም ጠብታ ድረስ እጅ አለመስጠትንና ቢያንስ እሪሪ ኡኡ ድረሱልኝ እያሉም ቢሆን ወገንን እየጠሩ መወራጨትን፣
• ከዚያም ሰብሰብ ብሎ ሰባሪን በመስበር፣ አሳዳጅን በማሳደድ፣ አኬሩን መገልበጥን ተምሬበታለሁ። የኅልውና ትግል ማለት እንዲህ ነው።

"…ተወው እባክህ ይጩህ፣ የአርባ ቀን ዕድሉ ነው። እኔን እስካልነካኝ፣ ከድንበሬም እስካልደረሰብኝ ድረስ ምን ቸገረኝ? አለማለትን ተምሬበታለሁ።

• እናንተስ…?

~ በነገራችን ላይ ዘመዴ ሚዲያ እየመጣ ነው።

51.1k 0 16 150 1.6k

"…በመጨረሻም እንደፈራነው አቤም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ። ተቀላቀለን። ይሞታል ይሞታል ወይ ታዲያ? ይሞታል ወይ፣ ይሞታል ወይ እንዴ?

• ታብታብ፣ ሼር ኮፒሊንክ …😁😁

• ዘመድ ሚዲያ እየመጣ ነው።

51k 1 5 86 1.5k

ዘገባው የፍሬሰንበት ገ/ዮሐንስ አድኃኖም ነው

"…በገዛ ርስቱ በጃንሆይ ሜዳም፣ በመስቀል አደባባይም መዘመር አትችልም የተባለው የጀንደረባው የአእላፋት ዝማሬ ወደ ቦሌ መድኃኔዓለም ተዘዋውሯል።

• ዛሬ ግን በእነ ትራምፕ የንስሐ አባት መለኮታዊ ጉብኝት በመስቀል አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው።

• እዋይ ተከስተ አለ ክበበው ገዳ

52k 1 18 89 1.4k

መለኮት…?

"…አልገባኝም…🙏  …ማናቸው መለኮት…? ሎቱ ስብሐት🙏 … የትራምፕ ንስሐ አባት ናቸው መለኮቱ ሎቱ ስብሐት… የመድኃኔዓለም ያለህ…🙏

በገዛ ርስት ላይ
በጃንሜዳም ሆነ በመስቀል አደባባይ
መዘመር ማሸብሸብ የተከለከልከው
እንዴት ነህ ሄኖኬ እንዴት ነህ ጀንደርባው?

ባንዲራም አልይዝም
አላውለበልብም
በጃኖ በጥለት በራሴም አላስርም
ብለህ ብትገረድ
ብትወጣ ብትወርድ
የጠሉትን ጠልተህ የወደዱትን ብትወድ
አልዳንክም ነበረ በግልፅ ከመዋረድ

የት ሄዱ ጀንደርቦች
የአእላፋት ዝማሬ የቀን በቀቀኖች
የታሉ ጀንደርቦች
ፌስቡክ ቲክታከሮች

ዝም ጭጭ አሉሳ ዝም ጭጭ ጮጋ
ያ አለብላቢ ትንታግ ልሳናቸውም በአንዴ ተዘጋ?

እንዴት ነህ ሄኖኬ እንዴት ነህ ጀንደርባው?
በገዛ ርስት ላይ
በጃንሜዳም ሆነ በመስቀል አደባባይ
መዘመር ማሸብሸብ የተከለከልከው
እንዴት ነህ ሄኖኬ እንዴት ነህ ጀንደርባው?

"…በአድካሚው የዘመድ ቴቪ የሙከራ ሥርጭት ዝግጅት ለማስጀመር በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ሆኜ ወደ ቴሌግራም ፔጄ ቶሎ ቶሎ ለመምጣት አልሆነልኝም። ይገባችኋል አይደል?

• ጸናጽል፣ ከበሮ፣ መቋሚያም አየሁ ልበል…? 😂

51.3k 1 17 72 1.5k

“…ነገሩ ተገለበጠ።” አስ 9፥1 "…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። ሉቃ 8፥17 …ገና…"…እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል። መዝ 58፥6

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

53k 1 13 1.6k 1.7k

• እንጠይቅ…?

፩፥ ሁሉም ክልሎች በበጀት ዕጥረት ምክንያት ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል አቅቷቸው ሳለ ኦሮሚያ በጀቱ ተርፎት በሁሉም ክልሎች በመቶ ቢልዮኖች እየመደበ የኦሮሞ ትምህርት ቤት የሚከፍተው ከየት በመጣ በጀት ነው?

፪፥ ቀደም ሲል በህወሓት ኢህአዴግ፣ ቀጥሎ ደግሞ በጁንታውና በብልጽግናው፣ አሁን ደግሞ በኦሮሙማው አገዛዝ ከ6 መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች ወድመው ሳለ እንዴት ነው ነገሩ?

፫፥ ሰቆጣ ዋግ ኽምራ ሕዝቡ በራብ እየረገፈ፣ ተሰድዶ እያለቀ ባዶ ሜዳ ላይ ሰው በሌለበት ትምህርት ቤት መገንባት ማለት ስላቅ አይሆንም…?

፬፦ ሰቆጣም ይሠራ፣ ሽሬም፣ ጉራጌ፣ አፋር ጋምቤላም ይሠራ፣ ቤኒሻንጉልም ይሠራ ችግር የለውም። ሸንጎ…?

፭፥ ልፋ ቢለኝ እኮ ነው። ለማንኛውም ዘመድ ሚዲያ እየመጣ ነው…

55.7k 1 11 55 1.6k

"ርእሰ አንቀጽ"

• ሦስት ነገር

፩፥

"…ጥቁር ካልሲ፣ በጥቁር ጫማ፣ ጥቁር ሱሪ፣ በጥቁር ቡታንታ ግልገል ሱሪ፣ ጥቁር ሸሚዝ፣ ጥቁር ኮፍያ፣ በጥቁር መነጽር ያጠለቀው መልአከ ሞቱ አቢይ አሕመድ ካልጠፋ ሰዓት በጥቁር ድቅድቅ ጨለማ ቀድሞ የነበረን የኖረ የጥይት ፋብሪካ ታሪኩን ደምስሶ፣ ክዶም 30 ሚልዮን ዶላር ትርፍ እንዳገኘንበት የነገረንን የጥይት ፋብሪካ መርቆ እንደሱው ጥቁር የኀዘን ልብስ ከለበሰው ከምክትሉ ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሆን ጦቢያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

፪፥

"…የጥይት ፋብሪካው ምርት እየተነገረ ባለበት ዕለት በሌላ ዜና ደግሞ በራያ አላማጣ ጥሙጋ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያንን ከ40 ዓመት በላይ ያገለገሉና የድጓ መምህር የሆኑትን መሪጌታ ገብረ መድኅን የተባሉ ደካማ ዓይነ ስውር አባት ዕድሜያቸው ከ10-14 ከሚሆናቸው 3 ዲያቆናት ጋር የካቲት 27ለ28/2017 አጥቢያ ንጋት ላይ ራያ አላማጣ ሰፍሮ በሚገኘው ቀይ ለባሹ ኮማንዶ ክፍለጦር መጨፍጨፋቸው ተሰምቷል። ከግድያው በኋላ ከሞት የተረፉት የአብነት ተማሪዎቹ በሙሉ ተበታትነዋል።

፫፥

"…በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማለትም በብፁዕ አቡነ አብርሃም እና በብፁዕ አቡነ ሄኖክ መካከል በሠራተኛ ቅጥርና በሙስና ጉዳይ በመካከላቸው የተፈጠረውን ያለመግባባት ለመፍታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመደባቸው ኮሚቴዎችም በትናንትናው ዕለት ጋዜጠኞች ሰብስበው መግለጫ መስጠታቸው ተዘግቧል።

"…የብልጽግናው መንደር ሐዋርያት "ሃሌ ሉያ ኢትዮጵያ አድጋለች፣ አዲስ አበባም አውሮጳ መስላለች" የሚለው ሰበካቸው ከዚህ ዜና ጋር ባለመሄዱ አዝናለሁ።

• እየሞትነ…

• ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
የካቲት 28/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

51.5k 1 14 87 1.8k


17 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.