እንኳን አደረሰን
"…የዛሬ 129 ዓመት ልክ በዛሬው ዕለት የካቲት 23/1888 ዓም በዕለተ እሑድ በዓድዋ ሥላሴ ግብጻዊው ሊቀጳጳስ አቡነ ማቴዎስ በመሩት ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ንጉሠ ነግሥት ዳግማዊ ዐፄ ምንልክ እና ንግሥቲቱ እቴጌ ጣይቱ በተገኙበት ከሥርዓተ ከቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ተአምረ ማርያም ተነብቦ፣ የሊቀ ጳጳሱ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ተሰምቶ፣ በጦርነቱ ላይ የሚሰዉ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችም እግዚአብሔር ይፍታህ ተብለው፣ ቁጥራቸውም ከሰማእታት ወገን እንደሆነ ተነግሮአቸው፣ በሁዳዴ በዐቢይ ጾም እህል እንኳ በአፋቸው ሳይቀምሱ ነው በቀጥታ በባዶ አንጀታቸው ወደ ጦርነቱ ሥፍራ ሄደው በግማሽ ቀን ያን ግዙፍ የአውሮጳ ጦር ድል ያደረጉት።
"…በዚህ ድል ዓለም በሙሉ ይደመማል፣ ይኮራልም። በዚህ ድል የማይኮሩት የእንቁላል ቀቃይ ልጅ የጠላት አድራሽ ፈረስ እስከ አምባላጄ ድረስ መንገድ መሪ የነበሩ ፀረ ኢትዮጵያ ባንዳ የባንዳ የልጅ ልጆች ብቻ ናቸው።
"…ዓድዋ ፀሐይ ነው። ፀሐይ የምትጋረደው ለጥቂት ጊዜ በደመና ብቻ ነው። ደመና ደግሞ ስስ ነው። ሲያዩት ተራራ፣ ባዘቶ ጥጥ ይመስላል እንጂ ይተንናል። ይበንናል። ፀሐይን የሚጋርድ፣ የሚደብቅ ምድራዊ ኃይል የለም። ወደፊትም አይኖርም። የክረምት ደመና ጥቂት ጊዜ ዊኒጥ ዊኒጥ ይላል ፀሐይን ለመጋረድ። በክረምት የደመናን ፀሐይን መጋረድ ያየ ሰው ፀሐይ መቼም የምትወጣ ላይመስለው ይችል ይሆናል። የክረምት ደመና የፀሐይን ሙቀት እንጂ ብርሃኗን መጋረድ አይቻለውም። ፀሐይ አዲስ አበባ ላይ ብትጋረድ ሌላ ቦታ አለች። መንጋቱ፣ ቀን መሆኑን ከደመናው ጀርባ በማትታየው ፀሐይ ብርሃን ይታወቃል።
"…ዓድዋም ፀሐይ ነው። ለጊዜው መቀሌና ሸገር፣ ትግራይና ኦሮሚያ እንደ ፀሐይ ደምቆ ላይገለጥ ይችላል። ደመና ወያኔ፣ ደመና ኦነግ ኦህዴድ ሲተንኑ ፀሐይ ዓድዋ በድምቀት ይከበራል።