ዘዋጅ ሠኢድ ፍቅር በኢስላም ✍


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


=>አላማችን ከዝሙት የፀዳን🍂

=>ማህበረሰብ መፍጠር ነዉ🍂
=>የትዳርን ችግር ለመቅረፍ🍂
=>ዝሙትን ለማጥፍት🍂
=>ወጣቱን ወደ ትዳር እንድገባ ለማድርግ🍂
የትዳር ኮርስ እንሠጣለን🍂
"ሼር ጆይን^
☞http://Telegram.me//ZewagSeid

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri








"ትዳር ከፈጣሪ የተቀደሰ ስጦታ ነው ከአንድ ይልቅ ሁለት ሆኖ መኖር የራሱ የሆነ ልዩ በረከት አለው"

   "የፍቅር ባለቤት አሏህ ነው እድትወድም እድትጠላም የሚያደርግህ አሏህ ነው
ፍቅር በልብ ውስጥ ይገኛል የልብ ባለቤት ደግሞ አሏህ ነው"

  => አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካትሁ ወድ እና የተከበራችሁ የዶክተር ዘይኔ ተማሪዎች የዘዋጅ ሰኢድ ቤተሰቦች እንዲሁም ይህ ፁሁፍ የሚደርሳችሁ በሙሉ እንደምን አላችሁ??

  => ምን አልባት የሰው ጉዳይ ምን አገባኝ ልንል እንችል ይሆናል ግን እንደ ሙስሊም ደግሞ የሙስሊም ችግር ችግራችን፣ጭንቀቱ ጭንቀታችን፣ደስታው ደስታችን ሊሆን ይገባል ነውም፣

  => ዛሬም እንደተለመደው በዕለተ እሁድ በኡኽት ሙሀመድ አማካኝነት ወደ ዘዋጅ ሰኢድ አባሎች ሲቀርብ የነበረውና ሁሉም ሃሳብ ከሰጠበት ቡኋላ መደምደሚያውን በዶክተር ዘይኔ የሚያገኘው መንታ መንገድ ፕሮግራማችን ዳግም ተመልሷል
ዛሬ አንድ ባስጨነቀኝ ሰላሜን በነሳኝ ነገር ላይ መጥቻለው ከአሏህ በታች የእናንተን ሃሳብ፣ዱዓ እገዛን እሻለሁ ትላለች በትዳሯ ላይ ፈተና የገጠማት አንዲት ሙስሊም እህታችን

  => ባለቤቴን በጣም እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ደግሞም የሚፈቀር የሚወደድም ባል ነው  2 ልጆችን ወልጄለታለሁ እኔ 2ተኛ ሚስቱ  ነኝ 4 ሚስቶች አሉት በአሁን ሰአት ደግሞ 3ተኛ ልጃችንን በሆዴ ይዣለሁ እሱ ብዙ ግዜ ዝምታን አፍቃሪ ነው እኔ ደግሞ በተቃራኒው ጨዋታን ወዳጅ መዝናናትን የምሻ ከባለቤቴ ጋር ትግልን የምወድ አይነት ነኝ ሆኖም ግን ይህን ሁሉ ባላገኝም ስለምወደው ስለማፈቅረው የሱን ፀባይ ተላብሼ የአብራኬን ክፋይ ምርጥ ልጆቼን ወልጃለሁ!
 
  => ከእለታት አንድ ቀን ቡና አፍልቼ እየተጫወትን ባለንበት ሰዓት ሳላስበው ግን እኮ አንቺ ቆንጆ አይደለሽም  ግን ቆንጆ ያልሆንሽው ለእኔ እንጄ ለሌሎች አልያም ተፈጥሮሽ ቆንጆ አይደለም ማለቴ አይደለም አለኝ ።

  => ደነገጥኩ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ በእጄ የያዝኩት ስኒ ወደቀ አለቀስኩ ሰውነቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ግን ለምን  እስከዛሬ 2 ልጆች እስክወልድ 3ተኛ እስክደግም ለምን አልነገርከኝም አልኩት ስለምታሳዝኒኝ እና ደግሞ ከአንች  በጣም የምወደው ነገር አለ እሱም

    1// በጣም ትወጅኛለሽ በተደጋጋሚ ነግረሽኛል እደዚህ እየወደድሽኝ  እንዴት ብየ ልንገርሽ??

    2// አልጋ ላይ በደንብ ትመችኛለሽ ከአንች ውጭ እኔን ማርካት የሚችል የለም!!

    3// በጣም ታሳዝኝኛለሽ በጣም ከምነግርሽ በላይ


=> ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ካሉ በቂ ነው በእዝነት ከያዝኩሽ ምን አልባት እኔ በመታገሴ ጀነትን አገኝ ይሆናል አልያም በቀስታ ፍቅር ይመጣ ይሆናል ሌላው  በስሜት ደረጃ በአንቺ ደስተኛ ከሆንኩ እና ከአንቺ እርካታን ካገኘሁ በቂ ነው  እርግጥ ልነግርሽ ፈልጌ አልነበረም በቃ አመለጠኝ ስለዚህ አሁን ሁሉንም እወቂው ሲል በደንብ አብራርቶ ነገረኝ!!

=> ከነገረኝ ሰአት ጀምሬ አሁን እስካለሁበት ቅፅበት ድረስ ከራሴ ጋር በፀብ ውስጥ ነኝ መፈታትን አስባለሁ ግን ደግሞ በጣም አወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ በዚያ ላይ የልጆቼ አባት ነው

    =>እሽ አብሬው በትዳር ብቀጥል ደግሞ እሱ አይወደኝም ስለሚያዝንልኝና እና ከእኔ እርካታን ስላገኘ ብቻ ከሱ ጋር ልቀጥል?? ያረህማን ከባድ ውዝግብ ላይ ነኝ ነኝ!

=> ወድ እህቶች በተለይ አንባቢያን በሙሉ እናንተ በእኔ ቦታ በትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?? አብራችሁ መኖር ወይስ መውጣት??  አብራችሁ ለመኖር ብትወስኑ ራሳችሁን እንዴት አድርጋችሁ ማሳመን ትችላላችሁ??? የሚገርመው እደዚያ እንኳ ብሎኝ ይበልጥ እየወደድኩት ነው የመጣሁት ታድያ እኔ ጤነኛ ነኝ ወይስ?? 

  => ወድ አንባቢያን ወይም ይሄን ታሪክ በድምፅም የምሰሙ በሙሉ ለዚህች እህታችን መልካም ሃሳባችሁን እደምትለግሷት ተስፋ ይኖረናል ኢን ሻ አሏህ


=> ህይወት እንደዚህ ነች ሁሌም ቢሆን እኛ በጠበቅናት መልኩ አታስተናግድም በተለይ ደግሞ በፍቅር ዙሪያ አንዱ አፍቃሪ ሌላው ተፈቃሪ በተለያየ መንገድ ይተላለፋሉ።


   ከታሪኩ ጋር የማይያያዝ  የፀሃፊዋ የኡኽት ሙሀመድ ሃሳብ

_


=>እንደ እኔ ሃሳብ እህቴ እድለኛ ነሽ ምክንያቱም በማፍቀር ውስጥ እርግጠኝነት አለ በመፈቀር ውስጥ ግን እርግጠኝነት የለም ስለዚህ አፍቃሪ ልብ ስለተሰጠሽ አሏሁ ሱብሃነሁ ተዓላ በሰፊው አመስግኝው

=> የምትወጅውንም ባልሽን አሏህ አንቺን እዲወድሽ፣በልቡ የሚስትነት ቦታን እዲሰጥ አጥብቀሽ ለምኝው መልእክቴ ነው ካፈቀርሽው ደግሞ ቢያንስ ስለምታሳዝኝው ብሎም ከአንቺ ብዙ ሰዎች ትዳራቸውን የሚበትኑበት የሆነውን የአልጋ ላይ ጉዳይ በአንቺ ደስተኛ ስለሆነ ይህም አንዱ የአሏህ ፀጋ ነው እና በዚህም ተፅናኝ አሏህንም አመስግኝው።

ፀሃፊ ኡኽት ሙሀመድ የዚዋጅ ሰኢድ አባልና የዶክተር ዘይኔ ተማሪ


Photo from Dc














Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish












https://vm.tiktok.com/ZMrQqyVCX/
https://vm.tiktok.com/ZMrQqyVCX/
https://vm.tiktok.com/ZMrQqyVCX/

መዲነተል ሙነዋራን /ሀረምን
ቁበተል ኸድራ
ረውዷን አሏህ ይወፍቀን

👌👌👌👌👌




ዓሹራ..
ዓሹራ ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

ኢስላም ውስጥ በየጊዜው ሙናሰባቶች(አጋጣሚዎች)  አሉ። ውስጣቸው ትልልቅ አስተምህሮዎች ያዘሉ.. ብዙ ዒብራዎች ያሏቸው.. ትሩፍቶቻቸው የበዙ አጋጣሚዎች ኢስላም ውስጥ በሽ ናቸው። እነዚህ ሙናሰባቶች እርስ በርስ ያላቸው ትስስር..  ሄዶ ሄዶ ሁሉንም የሚያገናኛቸው መስመር አንድነትና ታላቅነት የዲኑን ውበት የሚያጎላና የትኛውንም ሰው የሚማርክ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል።

የረመዳን ወር፣ የዙል ሂጃ ወር፣ የሙሃረም ወር ፣ የረቢእ ወር.. ሌሎቹም ውስጥ የተለያዮ ድንጋጌዎችና ትምህርቶችን ባዘሉ አጋጣሚዎች የተሞሉ ናቸው።

ያለንበት የሙሃረም ወር ብዙ significant የሆኑ ነገሮች የተፈፀመበት ወር ነው። ከነዛ መሃከል የዓሹራ ቀን አንዱ ነው። ዓሹራ ነብየላህ ሙሳ (ዓለይሂ ሰላም)ና ህዝቦቻቸው ከፊርዓውን ዘግናኝ አገዛዝ ነፃ የሆኑበት ቀን ነው።

ነቢየላህ ሙሳ ( ዓ.ሰ) ድንገት አይደለም ባህሩ ለሁለት ተሰንጥቆ ድል ያደረጉት። ወይም የአላህ ተኣምር ድንገት አይደለም የመጣቸው።

አላህ ፊርኣዉንን ሊያጠፋ ሲሻ ብዙ ዓመታትን የሚፈጅና ፅናትን የሚፈትን ትግል ውስጥ እንዲያልፉ አርጎ ነበር ለሙሳ (ዓ.ሰ) ኑቡዋ የሰጣቸው። የሚገርመው ፊርኣውን ከቤተ እስራኤላውያን የሚወለድ ልጅ ከንግስናው እንደሚያሰናብተው ትንቢት ከደረሰው ግዜ ጀምሮ ሴቶችን እየተወ ወንዶች ልጆችን ገና ከመወለዳቸው ይገ*ድል ነበር።  በኃላ አንድ አመት እያለፈ ቀጣይ አመት ላይ የሚወለዱትን መግ*ደል ጀመረ። አላህዬ የሻውን የሚያደርገው ጌታ ሙሳ(ዓ.ሰ) ልጆች በሚገደሉበት ዓመት ነበር እንዲወለዱ አደረገ ። እሱ ብቻ ዓይደለም ገና ጡት ሳይጥል በሰንዱቅ ሆኖ ጎጆው እንዲገባ ብሎም ፊርኣውን ቤት ውስጥ እንዲያድግ የርሱ መሻት ሆነ። አላህ ሲሻ ለምን ? እንዴት? ብሎ ነገር የለም። ሎጂክ የለ ዩኒቨርሳል ህግ .. አላህ ወሰነ ..ሆነ።

«የፈርዖን ቤተሰቦችም (መጨረሻው) ለእነርሱ ጠላት ኃዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት።» ቀሰስ: 8
ፈርዖን ሙሳን ለማንሳትና ለማሳደግ የመጨረሻው ሰው ነበር.. አላህ ስለሻው ብቻ ግን ማይመስል ነገር ነበር የሆነው..
መቼም እንደዚህ አይነት ተድቢር የትም አይተህ አታውቅም ☺️
«ባንተ ላይም ከእኔ የኾነን መወደድ ጣልኩብህ። (ልትወደድና) በእኔም ጥበቃ ታድግ ዘንድ። » ጣሃ ፥ 39  እንግዲህ በአላህ ጥበቃ ስር ያደገ ሰው ለምን ዓይነት ተልእኮ እንደታጨ ማሰብ ነው ። ስለዚህም ሙሳ (ዓ.ሰ) ፊርኣውንን ድል ያደረጉት ገና ሲወለዱ ነው ማለት ይቻላል። ፊርኣውን ካለማወቁ ጋ ጠላቱን ቤቱ ሲያስገባ ጌሙን ተበልቷል። ቀሪው ሁሉም ፕሮሰስ ነበር።

እዚህ ጋ አንዴ ቆም እንበልና አላህዬ ያላቃቸውን ሰዎች(ኻሰተን አንቢያኦችን)  በተለያየ መውቂፍ ውስጥ እንዴት እንደሚንከባከባቸው፣ እንዴት ተርቢያ እንደሚያደርጋቸው፣ ከፈተናም ጋ ቢሆን ልባቸው በሚሰበርበት ወቅት እንዴት ልባቸውን እንደሚጠግነው ልብ ብላችኃል?

የሙሳ (ዓ.ሰ) ታሪክ ቁርኣን በሰፊው ከዳሰሳቸው ታሪኮች ውስጥ ነው። ፊርኣውንም ቁርኣን ውስጥ በሰፊው የተዳሰሰ የመጥፎ ማሳያ የሆነ ሰው ነው። ሙሳ (ዓ.ሰ) "ከሊሙላህ" የተባሉ አላህን ያናገሩ ታላቅ ነብይ ናቸው .. ፊርኣውን ደሞ የአላህን ስልጣን ለመገዳደር የሞከረ ደፋርና በእብሪት ድንበር ያለፈ ሰው ነበር። እንድንወስድ  የተፈለገ ትምህርት ባይኖር በዛ ልክ አላህ ቦታ ባልሰጠው ነበር። ሙሳ (ዓ.ሰ) ከአላህ መልእክተኞች አንዱ ብቻ አልነበሩም ። ፊርኣውንም ተራ አንባገነንና በዳይ ሰው ብቻ   አልነበረም።
በሙሳ እናት ተወኩል ውስጥ እንማራለን። ፊርኣውን ቤት ከገቡበት ተኣምራዊ ክስተት ሚገርም አቂዳ እንማራለን። እዛ ካሳለፉት ኑሮና የህዝባቸውን ሰቆቃና በደል ከታገሉበት ታሪክ ብዙ ምንወስዳቸው ነገሮች አሉ። በህይወታቸው ከገጠማቸው ፈተና (ሰው መግ*ደል) ብሎም የስደት ታሪካቸው ብዙ እንማራለን። ከኑቡዋቸው ጅማሮና ሂደት ብዙዙ እንማራለን ( በተለይ የደእዋን መርሃላ፣ ሱሉክ፣ ቋንቋና ሌላም) .. ከፊርኣውን እብሪትና ትእቢትም ብዙ እንማራለን። የአላህ ትእግስትና ቻይነት ምን ድረስ እንደሆነ እናይበታለን። ከሳሂሮቹ ኢማን የተውሂድን ኃይልና የእምነትን አቅም እንማራለን ..

የሙሳ(ዓ.ሰ) ታሪክ በትምህርቶች የታጀበ ነው። ሱረቱል ቀሰስና ጠሃን አዘውትሮ የሚያነብና ከመልእክቱ የተቀራረበ ሰው ብዙ ይማራል። ራሱን ለማነፅ ብዙ አይቸገርም።
የአላህ መልእክተኛ የአሹራ ቀንን ለማሰብ « እኛ ከናንተ ለሙሳ ቅርብ ነን። በሙሳ እኛ ከናንተ የተገባን ነን» ሲሉ ከነዚህና ከመሰል ጉዳዮች ጋር በጥልቁ ስለምንቆራኝ ነው። የሙሳና የተከታዮቻቸው ሲፋ ለአማኞች ሲፋ የቀረበ ስለሆነ ነው። « ቀጥተኛውን መንገድ ምራን» « በጎ የዋልክላቸውን ሰዎች መንገድ» ብለን የሙሳን መሰል ነብያቶችን መንገድ እንዲመራን አላህን የምንጠይቀው እኛ ስለሆንን ነው። ሙሳ እጅ የሰጡ ሙስሊም ስለነበሩ ነው ። ፊርኣውንና ሰራዊቱ ከኃላ ባህሩ ደሞ ከፊት ሆኖ በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ ባሉበት ወቅት « ተያዝን! አለቀልን» ሲሏቸው

"(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» ሹዓራእ፥ 62  ይህንን ያሉት ሙሳ (ዓ.ሰ) በእምነት የሚቀርቡትና አንድ የሚሆኑት ቁረይሾችኮ ደረሱብን ሲባሉ « አትዘን! አላህ ከኛ ጋር ነው።» ካሉት የኛው ነብይ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጋር ስለሆነ ነው።

ፊርኣውን ደሞ በግብር የሚመስለው በዳዮችንና ከሃዲዎችን ነው። አላህን የማይፈሩ የህፃናት ነፍስ ቀርጣፊዎች የሆኑት አይሁዶች አባታቸው ነው ፊርኣውን። ቁድዋቸው ነው ፊርኣውን። ፅዮናውያን ፈለስጢን ላይ የሚሰሩትን ግፍ ለመስራት ፊርኣውን መሆንን ይጠይቃል። ፊርኣውንን የያዘው ስልጣንን የማጣት ፍርኃት ልጅ የተባለን በሙሉ እንዲ*ገል እንዳደረገው ሁሉ ፅዮናውያኑንም
«ነገ አድገው ይታገሉናል፣ ከአገራቸውም ያባሩናል » የሚለው ስጋት ፅዮናውያኑን ያለ ርኃራሄ የዘር ጭፍ*ጨፋ ለአመታት እንዲከዉኑት አርጓቸዋል። ከዛ ሁሉ ትግልና ፈተና በኃላ ፈርኦንና ጀሌዎቹን በውሃ ጠራርጎ ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያደረገ አላህ ፈለስጢንን ነፃ እንደሚያወጣት አንጠራጠርም። ዟሊምን የሚታገል ድል ያደረገው ፍርኃትን ገፎ መታገል የጀመረ ቀን ነውና አሹራን የፊታችን ማክሰኞ ስንፆም የፈለስጢንን የትግል ድል  እያሰብን ነው ኢን ሻ አላህ 😊♥️ ዓሹራ..
ዓሹራ ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

ኢስላም ውስጥ በየጊዜው ሙናሰባቶች(አጋጣሚዎች)  አሉ። ውስጣቸው ትልልቅ አስተምህሮዎች ያዘሉ.. ብዙ ዒብራዎች ያሏቸው.. ትሩፍቶቻቸው የበዙ አጋጣሚዎች ኢስላም ውስጥ በሽ ናቸው። እነዚህ ሙናሰባቶች እርስ በርስ ያላቸው ትስስር..  ሄዶ ሄዶ ሁሉንም የሚያገናኛቸው መስመር አንድነትና ታላቅነት የዲኑን ውበት የሚያጎላና የትኛውንም ሰው የሚማርክ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል።

የረመዳን ወር፣ የዙል ሂጃ ወር፣ የሙሃረም ወር ፣ የረቢእ ወር.. ሌሎቹም ውስጥ የተለያዮ ድንጋጌዎችና ትምህርቶችን ባዘሉ አጋጣሚዎች የተሞሉ ናቸው።

ያለንበት የሙሃረም ወር ብዙ significant የሆኑ ነገሮች የተፈፀመበት ወር ነው። ከነዛ መሃከል የዓሹራ ቀን አንዱ ነው። ዓሹራ ነብየላህ ሙሳ (ዓለይሂ ሰላም)ና ህዝቦቻቸው ከፊርዓውን ዘግናኝ አገዛዝ ነፃ የሆኑበት ቀን ነው።

ነቢየላህ ሙሳ ( ዓ.ሰ) ድንገት አይደለም ባህሩ ለሁለት ተሰንጥቆ ድል ያደረጉት። ወይም የአላህ ተኣምር ድንገት አይደለም የመጣቸው።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.