"ትዳር ከፈጣሪ የተቀደሰ ስጦታ ነው ከአንድ ይልቅ ሁለት ሆኖ መኖር የራሱ የሆነ ልዩ በረከት አለው"
"የፍቅር ባለቤት አሏህ ነው እድትወድም እድትጠላም የሚያደርግህ አሏህ ነው
ፍቅር በልብ ውስጥ ይገኛል የልብ ባለቤት ደግሞ አሏህ ነው"
=> አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካትሁ ወድ እና የተከበራችሁ የዶክተር ዘይኔ ተማሪዎች የዘዋጅ ሰኢድ ቤተሰቦች እንዲሁም ይህ ፁሁፍ የሚደርሳችሁ በሙሉ እንደምን አላችሁ??
=> ምን አልባት የሰው ጉዳይ ምን አገባኝ ልንል እንችል ይሆናል ግን እንደ ሙስሊም ደግሞ የሙስሊም ችግር ችግራችን፣ጭንቀቱ ጭንቀታችን፣ደስታው ደስታችን ሊሆን ይገባል ነውም፣
=> ዛሬም እንደተለመደው በዕለተ እሁድ በኡኽት ሙሀመድ አማካኝነት ወደ ዘዋጅ ሰኢድ አባሎች ሲቀርብ የነበረውና ሁሉም ሃሳብ ከሰጠበት ቡኋላ መደምደሚያውን በዶክተር ዘይኔ የሚያገኘው መንታ መንገድ ፕሮግራማችን ዳግም ተመልሷል
ዛሬ አንድ ባስጨነቀኝ ሰላሜን በነሳኝ ነገር ላይ መጥቻለው ከአሏህ በታች የእናንተን ሃሳብ፣ዱዓ እገዛን እሻለሁ ትላለች በትዳሯ ላይ ፈተና የገጠማት አንዲት ሙስሊም እህታችን
=> ባለቤቴን በጣም እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ደግሞም የሚፈቀር የሚወደድም ባል ነው 2 ልጆችን ወልጄለታለሁ እኔ 2ተኛ ሚስቱ ነኝ 4 ሚስቶች አሉት በአሁን ሰአት ደግሞ 3ተኛ ልጃችንን በሆዴ ይዣለሁ እሱ ብዙ ግዜ ዝምታን አፍቃሪ ነው እኔ ደግሞ በተቃራኒው ጨዋታን ወዳጅ መዝናናትን የምሻ ከባለቤቴ ጋር ትግልን የምወድ አይነት ነኝ ሆኖም ግን ይህን ሁሉ ባላገኝም ስለምወደው ስለማፈቅረው የሱን ፀባይ ተላብሼ የአብራኬን ክፋይ ምርጥ ልጆቼን ወልጃለሁ!
=> ከእለታት አንድ ቀን ቡና አፍልቼ እየተጫወትን ባለንበት ሰዓት ሳላስበው ግን እኮ አንቺ ቆንጆ አይደለሽም ግን ቆንጆ ያልሆንሽው ለእኔ እንጄ ለሌሎች አልያም ተፈጥሮሽ ቆንጆ አይደለም ማለቴ አይደለም አለኝ ።
=> ደነገጥኩ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ በእጄ የያዝኩት ስኒ ወደቀ አለቀስኩ ሰውነቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ግን ለምን እስከዛሬ 2 ልጆች እስክወልድ 3ተኛ እስክደግም ለምን አልነገርከኝም አልኩት ስለምታሳዝኒኝ እና ደግሞ ከአንች በጣም የምወደው ነገር አለ እሱም
1// በጣም ትወጅኛለሽ በተደጋጋሚ ነግረሽኛል እደዚህ እየወደድሽኝ እንዴት ብየ ልንገርሽ??
2// አልጋ ላይ በደንብ ትመችኛለሽ ከአንች ውጭ እኔን ማርካት የሚችል የለም!!
3// በጣም ታሳዝኝኛለሽ በጣም ከምነግርሽ በላይ
=> ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ካሉ በቂ ነው በእዝነት ከያዝኩሽ ምን አልባት እኔ በመታገሴ ጀነትን አገኝ ይሆናል አልያም በቀስታ ፍቅር ይመጣ ይሆናል ሌላው በስሜት ደረጃ በአንቺ ደስተኛ ከሆንኩ እና ከአንቺ እርካታን ካገኘሁ በቂ ነው እርግጥ ልነግርሽ ፈልጌ አልነበረም በቃ አመለጠኝ ስለዚህ አሁን ሁሉንም እወቂው ሲል በደንብ አብራርቶ ነገረኝ!!
=> ከነገረኝ ሰአት ጀምሬ አሁን እስካለሁበት ቅፅበት ድረስ ከራሴ ጋር በፀብ ውስጥ ነኝ መፈታትን አስባለሁ ግን ደግሞ በጣም አወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ በዚያ ላይ የልጆቼ አባት ነው
=>እሽ አብሬው በትዳር ብቀጥል ደግሞ እሱ አይወደኝም ስለሚያዝንልኝና እና ከእኔ እርካታን ስላገኘ ብቻ ከሱ ጋር ልቀጥል?? ያረህማን ከባድ ውዝግብ ላይ ነኝ ነኝ!
=> ወድ እህቶች በተለይ አንባቢያን በሙሉ እናንተ በእኔ ቦታ በትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?? አብራችሁ መኖር ወይስ መውጣት?? አብራችሁ ለመኖር ብትወስኑ ራሳችሁን እንዴት አድርጋችሁ ማሳመን ትችላላችሁ??? የሚገርመው እደዚያ እንኳ ብሎኝ ይበልጥ እየወደድኩት ነው የመጣሁት ታድያ እኔ ጤነኛ ነኝ ወይስ??
=> ወድ አንባቢያን ወይም ይሄን ታሪክ በድምፅም የምሰሙ በሙሉ ለዚህች እህታችን መልካም ሃሳባችሁን እደምትለግሷት ተስፋ ይኖረናል ኢን ሻ አሏህ
=> ህይወት እንደዚህ ነች ሁሌም ቢሆን እኛ በጠበቅናት መልኩ አታስተናግድም በተለይ ደግሞ በፍቅር ዙሪያ አንዱ አፍቃሪ ሌላው ተፈቃሪ በተለያየ መንገድ ይተላለፋሉ።
ከታሪኩ ጋር የማይያያዝ የፀሃፊዋ የኡኽት ሙሀመድ ሃሳብ
_
=>እንደ እኔ ሃሳብ እህቴ እድለኛ ነሽ ምክንያቱም በማፍቀር ውስጥ እርግጠኝነት አለ በመፈቀር ውስጥ ግን እርግጠኝነት የለም ስለዚህ አፍቃሪ ልብ ስለተሰጠሽ አሏሁ ሱብሃነሁ ተዓላ በሰፊው አመስግኝው
=> የምትወጅውንም ባልሽን አሏህ አንቺን እዲወድሽ፣በልቡ የሚስትነት ቦታን እዲሰጥ አጥብቀሽ ለምኝው መልእክቴ ነው ካፈቀርሽው ደግሞ ቢያንስ ስለምታሳዝኝው ብሎም ከአንቺ ብዙ ሰዎች ትዳራቸውን የሚበትኑበት የሆነውን የአልጋ ላይ ጉዳይ በአንቺ ደስተኛ ስለሆነ ይህም አንዱ የአሏህ ፀጋ ነው እና በዚህም ተፅናኝ አሏህንም አመስግኝው።
ፀሃፊ ኡኽት ሙሀመድ የዚዋጅ ሰኢድ አባልና የዶክተር ዘይኔ ተማሪ